2016-03-29 11:12:00

ቅ. አ.የፋሲካን በዓል አስመልክተው የሰጡት "Urbi et Orbis" ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም ያስተላለፉት መልዕክት


እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በመጋቢት 27.2016 በተከበረው የፋሲካ በዓል ዕለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገረ ጎብኝዎች ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ መንፈሳዊ በዓላትን አስመልክቶ በምያስተላልፉት “Urbi et Orbi” በአማርኛው ለከተማው (ለሮም) እና ለመላው ዓለም  በተሰኘው ልማዳዊ በሆነው  መልዕክታቸው “የዓለማችን ቁስል” በማለት የገለጹትን በዓለም ዙሪያ የምታየውን በአካል እና በመንፈስ መከራ የምሰቃዩትን ሰዎች ትኩረት አድረገው መናገራቸው ታውቁኋል።

ቅዱስ አባታችን በመልዕክታቸው በተለይም ከመጋረጃ ጀርባ በስውር ስለምፈጸሙ አሰቃቂ ወንጀሎች እና ብዙኋኑን የማሕበረሰብ ክፍል ለአሰቃቂ መከራ እና ስደት እስከዳረገው በመሳርያ ድጋፍ በግልጽ እስከ ምካሄደው ጦርነት ድርስ ያለውን ግጭት በማውሳት፣ በተለይም ደግሞ በአስከፊ ጦርነት እና አሸባሪዎች እያደርሱት ባለው አደጋ  እየተሰቃዩ የምገኙትን የማሕበርሰብ ክፍሎችን ትኩረት ባደረገው ንግግራቸው እየደረሰ ላለው መከራ እና ስቃይ የምመለከታቸው የማሕበረሰብ ክፍሎች ለችግሩ መፍትሄ እንድያበጁ ጥሪ አድርገዋል።

“ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ተነስቱኋል። ከሞት በመነሳቱም የጥልን ግድግዳ አፍርሱኋል፣ ሕይወት ሞትን አሸንፉኋል፣ ብርሃን ጨላማን አጥፍቱኋል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆች ሁሉ ተስፋ መሆኑን ገልጸው ‘በሰዎች ልብ ወስጥ የምገኘውን የጥል እና የሞት መንስሄ የሆነውን ሥነ-ምግባራዊ እና መንፈሳዊ ጉድለቶችን በምሕረቱ መሙላት የምችለው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑንም አበክረው ገልጸኋል።

ከአምስት ዓመታት በፊት የተጀመረው እና የብዙ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው፣ ብዙዎችን ደግሞ ለስደት በዳረገው፣ አውዳሚውን የሶርያ ጦርነት በመጥቀስ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባታችን “ተሰቅሎ የሞተው ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሳቱ ለሰው ልጆች ሁሉ ርኅራኄ እና ምህረቱን፣ በተለይም ለተራቡት እና ለተጠሙት፣ ለባእዳን እና ለታሰሩት፣ ለተገለሉት እና ለተናቁት እንዲሁም የበደል እና የጥቃት ሰላባ ለሆኑት ሰዎች ሁሉ ምሕረትን እና ሰላምን ያመጣ ዘንድ ልንጸልይ ይገባል ብለኋል።

በረጅም እና አሰቃቂ ብዙዎችንም ለአስከፊ ሞት እና አሸባሪነት አደጋ የዳረገው እና የብዙኋኑን ሕይወት በቀጠፈው፣ ገሚሱን ሕዝብ ደግሞ ለስደት ባጋለጠው በእርስ በእርስ ጦርነት እየማቀቀች ባለችው ሶርያ የክርስቶስ ከሙታን መነሳቱ ከፍተኛ የሆነ የሰላምን ተስፋ ያመጣ መሆኑን የገለጹት ቅዱስ አባታችን ሞትን ድል አድርጎ በተነሳው ክርስቶስ ስም የምመለከታቸው፣ በጦርነቱ ላይ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የተሳተፉ ሁሉ ነፍጣቸውን አስቀምጠው  ለሰላም እና ለእርቅ ከፍተኛ ጥረት እንድያደርጉ እና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የሰላምን ፍሬ እንድያጣጥሙ እና የወንድማችነት መንፈስ እንዲዳብር ሁሉም በሰላም እና በአንድነት የምኖሩበት ማህበረሰብ ይመሰረት ዘንድ ጥረት እንድያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመቀጠልም በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም ይመጣ ዘንድ የተማጽኖ ጥሪያቸውን ያቀረቡት ቅዱስ አባታችን “ኢየሱስ ተቀብሮ በነበረበት ቦታ የነበረውን የመቃብር ክዳን መላዕከ እግዚአብሔር እንደከፈተው ሁሉ፣ የጥል እና የክርክር መንስሄ የሆነውን የደነደነ እና የድንጋይን ልብ እግዚአብሔር ይከፍት እና ያለሰልስ ዘንድ ልንጸልይ ይገባል ብለኋል።

በሜድትራንያን እና በሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢዎች በተለይም በኢራቅ፣ በየመን እና በሊብያ ሕዝቦችና ባህሎች መካከል ፍሬያማ የሆነ ሰላም እና መረጋጋት የመጣ ዘንድ ጥረት ልደረገ እንደ ምገባም ቅዱስነታቸው ጥሪ አድርገኋል።

በመቀጠልም ቅዱስ አባታችን በንግግራቸው “የኢየሱስ ሀገር” በማለት በጠቀሱኋት ቅድስትቱኋ ሀገር፣ በእስራኤል እና በፍልስጤማዊያን መካከል ቀጣይነት ያለው  ሰላም እንዲመጣ እና ሁሉም በወንድማማችነት መንፈስ  ተቻችለው እንዲኖሩ ጥሪ አድርገኋል።

ቅዱስነታቸው በማስከተልም “Urbi et Orbi” በአማርኛው ለከተማው (ሮም) እና ለመላው ዓለም በትሰኘው መልዕክታቸው በዩክሬይን እየታየ ያለው ውጥረት ተወግዶ ሰላም ይመጣ ዘንድ የምመለከታቸው ሁሉ የበኩላቸውን ድጋፍ ያደርጉ ዘንድ ተማጽነው፣ በግጭቱ ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉ ሁሉ ሰባዊ እርዳት እንዲደረገም ጥሪ አቅርበዋል።

በማስከተልም “ጭፍን ጥቃት” በማለት የጠሩትን በቅርቡ በአውሮፓ እና በአንድ አንድ ሀገራት ላይ የተቃጣውን እና የብዙዎችን ንጹኋን ሕይወት የቀጠፈውን የአሸባሪዎች ጥቃት አውግዘው እና የጥቃቱን ሰለባዎችን በፀሎት ያስታወሱት ቅዱስነታቸው “ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን በመነሳቱ ክፋትን እና ሐጥያትን ሁል ደምስሶ ሰላምን እንዳመጣልን ሁሉ፣  ይህ ጭፍን እና የብዙኋኑን ሰላማዊ ሰዎች ሕይወት እየቀጠፈ ያለው የአሸባሪዎች ጥቃት ተወግዶ፣ ይህን መሰል የአሸባሪነት ጥቃት እየተካሄደባቸው በምገኝባቸው በቤልጄም፣ በቱርክ፣ በናይጄርያ፣ በቻድ፣ በካሜሩን፣ በአይቮሪ ኮስት እና በኢራቅ ሰላም ይመጣ ዘንድ ጥሪ አቅርበኋል።

በመቀጠልም “የተስፋ እና የእድገት ጭላንጭል ይታይበታል”  ባሉት የአፍሪካ አሀጉር ይህንን ተስፋ እና እድገት የምያጨልም ድርጊት እየተፈጸመባቸው በምገኝባቸው በቡሩንዲ፣ በሞዛንቢክ፣ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ እና በደቡብ ሱዳን የምታዩት የፖሌቲካ እና የማሕበራዊ ውጥረቶች በውይይት መፈታት እንዳለባቸው እና በአፍሪካ አሀጉር የተጀመረው የእድገት እና የለውጥ ጎዳና እንዲቀጥልም ጥሪ አድርገኋል።

በመቀጠልም ቅዱስነታቸው በ “Urbi et Orbi” በአማርኛው ለከተማው (ለሮም) እና ለመላው ዓለም በተሰኘው መልዕክታቸው የዳሰሱኋት የላቲን አሜሪካዋን ሀገር ቬኑዝዌላን ስሆን ሁሉም የማሕበረሰብ ክፍሎች ለጋራ ጥቅም ይሰሩ ዘንድ ጥሪ አቅርበው፣ ኢየሱስ ለሁሉም የከፈተውን የምሕረት በርን ተጠቅመው አሁን በሀገሪቷ ያለው እና ብዙዎቹን የበይ ተመልካች ያደርገው የኢኮኖሚ ሥርዓት ተወግዶ፣ በአንጻሩም ሁሉንም የምሕበርሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የምያደርግ ሥርዓት ይዘረጋ ዘንድ ጥሪ አቅርበኋል። 

በማስከተልም የስደተኞች ሁኔታ መረሳት የለበትም ያሉት ቅዱስ አባታችን ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ እንደ ምያሳስበን ጦርነትን እና ብጥብጥን በመሸሽ ሀገራቸውን ጥለው የተሰደዱትን ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች፣ በተለይም ሕጻናት ትኩረት እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርበኋል።

ኢየሱስ ከሙታን በተነሳበት በዛሬው ዕለት ምድር በደስታ ተሞልታለች ያሉት ቅዱስ አባታችን አሁን ባለንበት ወቅት ትርፍን ብቻ ለማጋበስ በማሰብ ምድራችን ያለ አግባቡ እየተበዘበዘች እና እየተበከለች እንደ ምትገኝ አበክረው ገልጸው፣ ይህንን ድርጊት የምፈጽሙ ሁሉ ይህ ዓለማችንን ከምያወድም ድርጊት ተቆጥበው ሁሉም በሰላም እና በጤና፣ ንጹህ አየርን እየተነፈሰ የምኖርባት ምድር እንድትሆን ምድራችንን ከብክለት መጠበቅ እንዳለብን ጥሪ አድርገኋል።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን  በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ አሳሰቡት ከእግዚአብሔር እና እርስ በእርሳችን ልንታረቅ ይገባል ብለው፣ በተለይም ደግሞ ለእምነታቸው እና ለክርስቶስ ስም ታማኝ በመሆናቸው ብቻ ለመከራ እና ለስደት እየተዳረጉ የምገኙ ብዙ የምሕበርሰብ ክፍሎች እንዳሉ አውስተው፣ ኢየሱስ ከሙታን በተነሳበት ወቅት “ አትፍሩ ምክንያቱም ሞትን ድል አድርግያለው እና” በማለቱ በዝህ በኢየሱስ ቃል በመታገዝ ያለምንም ፍርሀት በታልቅ ተስፋ የጥልን ግድግዳ በማፍረስ እርስ በእርሳችን እና ከእግዚአብሔር ጋር ልንታረቅ ያስፈልጋል በማለት መልዕካትቸውን አጠቃልለዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.