2016-03-28 15:08:00

አርጀንቲና፥ ዓለም አቀፋዊ የተለያዩ ባሎችና ሃይማኖቶች የጋራ ጉባኤ


አብሮ መጓዝ ለሰላም በሚል ርእስ ሥር የሚመራ የተለያዩ ባህሎችና ሃይማኖቶች የጋራ ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 12 ቀን እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም. በአርጀቲና ርእሰ ከተማ ቦኖስ አይረስ እንደሚካሄድ ባለፈው ማክሰኞ እ.ኤ.አ. መጋቢ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. የአርጀንቲና ብፁዓ ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኾሰ ማሪያ አራንሰዶ በላቲን አመሪካ የአይሁድ ሃይማኖት መምህራንና መሪዎች የማሰልጠኛ ማርሻል ማየር የተሰየመው መንበረ ጥበብ ዋና አስተዳዳሪ የአይሁድ ሃይማኖት የበላይ መንፈሳዊ መሪ አብራሃም ስኮርካና በላቲን አመሪካ የምስልምና ለሰላም ተቋም ሊቀ መንበር ሱመር ኑፉሪና የአርጀንቲና የባህል ጉዳይ ሚኒ. ፓዉል አቨሉቶ በጋራ በሰጡት ጋዚጣዊ መግለጫ ማሳወቃቸው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ እ.ኤ.አ. መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው ሕትመቱ አስታወቀ።

ውይይት ማለት ሰላማዊ የጋራ ኑሮ ማለት ነው

በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኑፉሪ ፥ የዚህ ዓይነት ዓውደ ጉባኤ ዘወትር አስፈላጊና በተለይ ደግሞ በዚህ በአሁኑ ወቅት የወንጀል ቡድኖች እያስፋፉት ያለው ሰላማዊ የጋራ ኑሮ የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች ያብሮ መኖር ጥሪ የሚያናጋው ጸረ ሰላም ባህል ከምን ጊዜም በበለጠ ለመዋጋት የሚደገፍ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በተለያዩ አገሮች በሚካሄዱት ሕዝባዊ ምርጫዎች በእጩነት ለመቅርብ በሚደረገው ፖለቲካዊ የምረጡኝ ውደራና ቅስቀሳ ያሸባሪያኑ ጸያፍ ተግባር እንደ መሣሪያ በመጥቀም በሕዝቦችና በሰዎች መካከል ግጭትና መለያየት የሚያስከለው የዘረኝነት ቅስቀሳ ለገዛ እርሱ ለአብሮ መኖር አደጋ ነው፡ ሆኖም ይኽ ሁሉ ስጋት ለጋራ ውይይት ግፊት መሆን አለበት እንዳሉ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ ዕለታዊ ጋዜጣ ይጠቁማል።

የአይሁድ ሃይማኖት መምህር ስኮርካ በበኩላቸውም ኑፉሪ ያሉን በማስተጋባት በእስላምና በክርስትናው እምነት መካከል የቆየው የጋራው ውይይትና ግኑኝነት አቢይ አብነት ነው። ስለዚሁ በቦኖስ አይረስ ሊካሄድ ስለ ተወሰነው ዓውደ ጉባኤ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንዳሳወቁና ቅዱስነታቸውም ይኸንን እንደሰሙ የተቀደሰ የሚደገፍና በርታ ሊባል የሚገባው ዓላማ ነው በማለት እንደመለሱላቸውም ገልጠው ምንም’ኳ እቅዱ ሰፊና አቢይ ራእይ ያለው ቢሆንም ቅሉ በዕለታዊ ሕይወት መጀመር የሚገባው ጉዳይ ነው፡ ቅዱስ አባታችን ዓውደ ጉባኤው የተዋጣለት እንዲሆን የሁሉም ጸሎት ያስፈጋል እንዳሉዋቸውም ገልጠዋል ሲል ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ ያመለክታል።

ሰላም የሚቻል እንጂ ሊረጋግጥ የማይቻል ሃሳብ አይደለም

ብፁዕ አቡነ አራንሰዶ በበኩላቸውም ሊካሄድ የተወጠነው ዓውደ ጉባኤ ለመላ አርጀንቲና አዲስ ብሥራት ነው፡ በዚህ በባህሎችና በሃይማኖቶች መካከል ያለው ልዩነት ምክንያት በዓለም ጥላቻና ግጭት መራራቅና እርስ በእርስ መጠራጠር እየተስፋፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት የጋራ ውይይትና የጋራ ግኑኝነት የሚቻል መሆኑ የሚመሰክር መርሃ ግብር ነው፡ የሃይማኖት ልዩነት በሰላም ለመኖር እንቅፋት ሳይሆን በአንድ አባት ሥር ለሰላማዊ የጋራ ኑሮ መረጋገጥ የሁሉም ትጋጥ የሚጠይቅ ውሉዳዊ ጥሪ ነው፡ ሰለዚህ ሰላማዊ የጋራው ኑሮ የማይጨበጥ ሃሳብ ሳይሆን የሚከወን ሁነት ነው እንዳሉ ሎሶርቫቶረ ሮማኖ ገለጠ።








All the contents on this site are copyrighted ©.