2016-03-24 10:41:00

ቅ.አ. ፍራንቸስኮ በፀሎተ ሐሙስ ማታ የ12 ስደተኞችን እግር እንደ ምያጥቡ ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ  በዛሬው ዕለት ማለትም 24.03.2016 በሮም ከተማ በሚገኘው ካስተልኑዎቮ ዲ ፖርቶ በሚባል ስፍራ በመገኘት የአስራ ሁለት ስደተኞችን እግር እንደ ሚያጥቡ ተገለጸ።

እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በመጋቢት 27.2016 ከሚከበረው የፋሲካ በዓል በፊት፣ ኢየሱስ የሐዋሪያቱን እግር ያጠበበት፣ ቅዱስ ቁርባንን የመሰረተበት እና እንዲሁም የክህነትን ስልጣን ለሐዋሪያቶቹ የሰጠበት ቀን የሚዘከርበት የጸሎተ ሐሙስን በዓል ምክንያት በማድረግ፣ ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ ካስተልኑዎቮ ዲ ፖርቶ በሚባል ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞችን በምያስተናግደው ጽህፈት ቤት ተገኝተው የ12 ስደተኞችን እግር ማጠባቸው የሚያሳየው ለስደተኞች ያላቸውን አጋርነት ለመግለጽ መፈልጋቸውን መሆኑን  ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚኬላ መግለጻቸውን ጋዜጠኛችን አሌሳንድሮ ዲ ካርሎስ ዘግቧል።

ቅዱስነታቸው የ12 ስደተኞችን እግር ለማጠብ መወሰናቸው የሚያሳየው፣ ለስደተኞች፣ ለተቸገሩት እንዲሁም በጦርነት ለሚማቅቁ ሰዎች ያላቸውን አጋርነት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለዓልም በማሳየት፣ የዓልም ማህበረሰብ ለእነዚህ አስከፊ ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ ይሰጥ ዘንድ ለማስገንዘብ በመፈልጋቸው ጭምር መሆኑም ተገልጿል።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ምራባዊያን ሀብታም ሀገሮች በጦርነት እና በአንድ አንድ ማሕበርዊ አስገዳጅ ሁኔትዎች ምክንያት ለሚሰደዱት ሰዎች አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው በተደጋጋሚ እየተማጸኑ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ስሆን፣ ለስደተኞች ከሀገራቸው መፈናቀል  ምክንያት የሆነው በተለያዩ ሀገሮች እየተካሄዱ የሚገኙ ጦርነቶች እና ብዙኋኑን የዓለም ማህበረሰብ  ለድኽነት እየዳረገ ያለው ኢፍታዊ የኢኮኖሚ ስርዓት መቀየር እንዳለበት በተደጋጋሚ በዓለማቀፍ መድረኮች ማስገንዘባቸው የሚታወቅ ነው።

እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 6 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለመላዕከ እግዚአብሔር እና ለጠቅላላ አስተምሮ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ቅዱስነታቸው “ለስደተኞች ትኩረት ይሰጥ ዘንድ” የተምጽኖ ጥሪ ማድረጋቸው የሚታወቅ ስሆን፣ በተለይም ችግሩ በስፋት የሚታይባት እና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ወደ አውሮፓ ለሚጎርፉ ስደተኝች እንደ መግብያ በር እያገለገልች በምትገኘው  በጣሊያን ሀገር የሚገኙ ከ27 ሺ በላይ የሚሆኑ ቁምስናዎችን በማስተባበር በራቸውን ለስደተኞች እንዲከፍቱ እና ለስደተኞች ተጨባጭ ድጋፍ እንድያደርጉ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ከፍተኛ የሆነ ድጋፍ ለስደተኞች እየተደርገ መሆኑ የሚታወስ ነው።

ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚኬላ በተጨማሪም እንደገለጹት “ቅዱስ አባታችን የ12 ስደተኞች እግር ማጠባቸው ትህትናቸውን ቢቻ ሳይሆን የሚያሳየዉ አንደበተ ርቱዕ በመሆነ መልኩ ለስደተኞች እና እየተጋፈጡት ለምገኘው ችግር ዓለም ትኩረት ይሰጥ ዘንድ“ ለማስገንዘብ ጭምር መሆኑን ገልጸው በተለይም ደግሞ በያዝነው ቅዱስ የምሕረት ዓመት በተጠናከር መልኩ ለተቸገሩ ሰዎች የበኩላችንን ድጋፍ እንድናደርግ ለማስገንዘብ ጭምር መሆኑንም  አክለው ገልጸኋል።

በተመሳስይ መልኩ በአለፈው ዓመት ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ በሮም ከተማ በምገኝ አንድ ማረሚያ ቤት  ተገኝተው ከናይጄሪያ፣ ከኮንጎ፣ ከኤኳዶር እንዲሁም ከጣሊያን የተውጣጡ ታራሚዎችን እግር ማጠባቸው እና በዚህ ትህታና በተላበሰ ተግባራቸው የብዙ ሰዎችን ቀልብ ስበው እንደነበር የሚታወስ ነው።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.