2016-03-23 16:23:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት ስብከቶች


እ.ኤ.አ. መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ብላ የመረጠቻቸው የቦኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ቦርጎሊዮ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መጋቢት 19 ቀን የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ዮሴፍ ዓመታዊ በዓል በምታከብርበ ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ የተከታይነት ሥልጣናቸውን ከውስጥና ከውጭ የመጡ በብዙ ሺህ የሚገመቱ ምእመናን የተለያዩ አገሮች መሪዎችና ልኡካን የተለያዩ ሃይማኖቶች የበላይ መንፈሳዊ መሪዎች በተገኙበት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ እንዳስጀመሩ የሚታወስ ሲሆን። ለመኖሪያ በመረጡት በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ተራ በሆነው በቅድስት ማርታ ሕንጻ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ሁሌ ማለዳ የተለያዩ ምእመናን የሚያሳትፍ መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. መጋቢት 22 ቀን 2013 ዓ.ም. የጀመረ ሲሆን።  ይኸ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መርሐ ግብር እ.ኤ.አ. መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ሦስተኛ ዓመቱን አስቆጥረዋል።

ስለዚሁ ጉዳይ በማስመልከትም ለአርጀንቲናው ላ ናሲዮን ለተሰየመው ዕለታዊ ጋዜጣ ጋዜጠኛ የሥነ ቫቲካን ሊቅ የቅዱስነታቸው ሕይወት ታሪክ ዘጋቢ አርጀንቲናዊት ኤሊዛበታ ፒኩዌ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ያንን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅድስት ማርታ ሕንጻ የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ወንጌል ለሁሉም ማድረስ የሚል ትርጉም ያለው መሆኑ ገልጠው፡ የቅዱስ አባታችን ታላቅና ታዋቂነት ካላቸው ስልጣን የመነጨ ሳይሆን እግዚአብሔር የሰጣቸው ሥልጣን የሚኖሩበት ሕይወት ነው። ሥልጣን አገልግሎት ነው ብለው የሚያምኑ፡ አገልግሎት ማለት መሆኑም በቃልና በሕይወት የሚገልጡ በመሆናቸውና እንዲሁም የሚሉት የሚናገሩት የሚሰጡት ትምህርት ሁሉ ጥልቅና ሁሉም ሊረዳው በሚቻለው ዘይቤ የሚያቀርቡ በመሆናቸውም ነው፡ ወንጌል በመኖር እንዲኖር የሚደግፉ ቃለ እግዚአብሔር ተራ በሆነ አነጋገር በማቅረብ ቤተ ክርስቲያን ቃለ እግዚአብሔር የመኖር ጥሪዋን የሚያነቃቁ በመሆናቸውም ነው ብለዋል።

ወደ ዋናው መሠረታዊ ወደ ሆነው ሥርወ እምነት በኅዳሴ አማካኝነት ለመመለስ የሚመራ እርሱም የክርስትናው አንኳር የሚያስገነዝቡበት የቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት የሚያቀርቡት ስብከቶቻቸው በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉመው ታትመው ለንብባ ቀርበዋል፡ እነዚህ ስብከቶቻቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ሥልጣናችው የሚከተለው ሐዋያዊ መርሐ ግብር በጠቅላላ የሚተነንም ነው፡ በሥነ አኃዝ ተራቆ እየመጠቀ በመሄድ ላይ ባለው የመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት በማሕበራውያን ድረ ገጾች ሁሉም ሳይቀር የሚተላለፍ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ መልእክት ሆነዋል። ገና በአርጀቲን እያሉ በቅርቡ እንደሚያውቁዋቸውና ክህነታዊና ኢየሱሳዊ ጥሪያቸውን ቃለ ወንጌል በማበሰር የሚኖሩ እንደነበሩና ይኽ የጥሪያቸው መግለጫ የሆነው ሰባኬ ወንጌል መለያው አሁንም በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ደረጃ እየኖሩት ነው፡ ቃለ እግዚአሔርን በማበሰር የወንጌል ሃሴት መስካሪ ናቸው፡ ወንጌላዊ ሓሴት ርእስ ሥር የደረሱት ሐዋርይዊ ምዕዳን ወንጌላዊ ሕይወታቸው ምን ተመስልዎውን ያረጋግጥልናል፡ ካህን እያሉ በአርጀቲና ቅድስት ፈ ከተማ በሚገኘው ንጽሕት ቅድስተ ማርያም መንበረ ጥበብ የሥነ ጽሑፍና ሥነ ድርሰት እንዲሁም የሥነ ልቦና መምህር ሆነው በማገልገል ላይ እያሉም ሳይቀር ጥልቅ የሆነው ሥነ ምርምርም የሚጠይቀውን ጥናት እንድታስብ በሚያደርግ ሥልት አማካኝነት ሁሉም ሊረዳው በሚችል ቃል የሚያቀርቡና እውቀት እንድትቀስም ብቻ ሳይሆን የማሰብ ችሎታ ለማሳደግ የሚያበቃ ጥበብ የሚያስተምሩ ጸላይ የቅዱስ መንፈስ አስተንፍሶ የሚኖሩ ወደ ሁሉም ሰው ልጅ ልብ የሚደርሱ ናቸው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.