2016-03-21 16:25:00

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን በመቄዶኒያ


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን በመቂዶኒያ የሦስት ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት አከናውነው አገር ቫቲካን የገቢ ሲሆን። በዚህ በመቄዶኒያ እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 17 ቀን እስከ መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄዱት ጉብኝት በመቄዶኒያ ርእሰ ከተማ በአገሪቱ ለቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ቢሮ እንዲሁም የሐዋርያዊ ግብረኖልዎ ማእከል በማካተት የተገነባው አዲስ መንበረ ጳጳስ በመመረቅ ከአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳትና ውሉደ ክህነት ጋር የተገናኙ ሲሆን። በተለይ ደግሞ መቄዶኒያ ከግሪክ በሚያዋስናት ክልል የሰፈሩት ስደተኞችና ተፈናቃዮችን የጎበኙ መሆናቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኢቫ ሚሃይሎቫ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳ ተችለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ያካሄዱት ጉብኝት አጠናቀው አገረ ቫቲካን እንደገቡ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ የኤውሮጳው አቢዩ መለያዋ ሰብአዊነትዋ ነው። የተካሄዱት ሁለቱ አበይት ጦርነቶች ወዲህ ኤውሮጳ የሰብአዊነትና የሰው ልጅ ሰብኣዊ መብትና ክብር ማእከል እንዲትሆን አድርጓታል። ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት የሚታየው የስደተኛው ጸዓት ችኵል መልስ ሳይሆን ስደተኛውን በማስተናገድና በመቀበል በዓለማችን የሚታዩት የሰውን ልጅ ለተለያየ አደጋ የሚያጋልጡት ችግሮች መሠረታዊ መፍትሔ እንዲያገኙ በሚደረጉ ርብርቦሽ ተቀዳሚ ሆና መገኘት ይኖርባታል። ፖለቲካዊ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ታሪካዊ ግዴታዋም ነው ብለዋል።

በመቄዶኒይ ገቭገሊዣ የሚገኘውን እንዲሁም ኢዶመኒ መጠለያ ሠፈር ጭምር መጎብኘታቸው ገልጠው በመቄዶኒያ የሚገኘው በካሪታስ ለሚጠራው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር ቅርንጫፍ በጠቅላላ በሶሪያ ብጥብጥ ከተጀመረበት ቀን ወዲህ እስካሁን ድረስ ለ 170 ሺሕ ስደተኞች የሰብአዊ እርዳታ ማቅረቡንም ጠቅሰው፡ በስኮፕዠ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቡራኬንና ሰላታን ለመቄዶኒያና ለሕዝቧ ጭምር ማድረሳቸውና 20 ሺሕ ምእመናን ያሏትን ቤተ ክርስቲያን ብትሆንም በእምነት ብሩቱና በአገሪቱ በተለያየ መስክ አቢይ አገልግሎት የምትሰጥ መሆንዋ ቀርበው ለማረጋገጥ መቻላቸውና ከአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳትም ሆነ ከመንግስት አካላት ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት እንደተመሰከረላቸው ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.