2016-03-21 16:28:00

ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ፤ በሶሪያ ሰላም እንዲረጋገጥ የጀነቭ የውይይት መድርክ


በላቲን ሥርዓት የተገባው ወደ በዓለ ፋሲካ በሚያሸጋግረው ዓቢይ ጾም የመጨረሻው ቅዱስ ሳምንት ባለው ዓርብ  ስቅልት ወቅት በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የሚሰበሰበው ምጽዋት በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ግጭትና ውትረት ሳቢያ ለስደት የሚዳረገው የሚገፋው ተሳዶ ለሚያጋጥመው ማኅበረ ክርስቲያን መርጃ እንዲውል የምስራቅ አቢያተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ይኸንን ያነቃቃው እቅድ በማስደገፍ እ.ኤ.አ. መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ መርሃ ግብሩን በማደገፍ በሰጠው መግለጫ ይፋ እንዳደረገ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሪና ታማሮ ገለጡ።

የሚሰቃዩት ለስደት የሚዳረጉትን በእምነታቸው ምክንያት ለተለያየ ኢፍትሓዊ አደጋ የሚጋለጡት ወንድሞቻችን ሁሉ ለመርዳት በሚደረገው ግብር ሰናይ ሁሉም እንዲተባበር ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ስለ መርሐ ግብሩ በማስመልከት ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የምስራቅ አቢያተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ሊዮናርዶ ሳንድሪ ጥሪ በማቅረብ፡ በእውነቱ መካከለኛው ምስራቅ አለ ማኅበረ ክርስቲያን በዚያ ክልል የተወለደው የክርስትና እውነተኛው ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ የተወለደበት ታሪካዊና ቅዱስ ሥፍራ በጠቅላላ ቅዱሳት ሥፍራዎች የመጽሓፍ ቅዱስ ታሪክ የሚያወሳው ቅዱስ ሥፍራ ሁሉ ቤተ መዘክር ሆኖ ይቀራል። ይኽ እንዳይሆንም በተለያዩ አገሮች የሚገኙት ማኅበረ ክርስቲያን በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኘው ለተለያየ ችግርና አደጋ ለተጋለጠው ማኅበረ ክርስቲያን ለዚያ ክልል ነዋሪ ሕዝብ ድጋፍ ሊያቀርብ ይገባዋል፡ እኔ እንደ ወደክዋችሁ እርስ በእርሳችሁ ተወደዱ ነውና ትእዛዙ ብለዋል።

በሶሪያ ያለው ሁከት ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያገኝ በጀነቨ የተካሄደው የሚካሄደው በጠቅላላ በተለያዩ የዓለምችን ክልል የሚታዩት ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እልባት እንዲያገኙ የሚካሄዱት የሰላም ድርድሮች ሁሉ አመርቂ ውጤት እንዲኖራቸው በዚህ የጌታችን ሕማማት ሳምንት መላ ማኅበረ ክርስቲያን  እግዚአብሔርን ይለም በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.