2016-03-19 16:18:00

የአይቮርይ ኮስት ብፁዓን ጳጳሳት መልእክት


እ.ኤ.አ. መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም. በአይቨርይኮስት አክራሪው እስላማዊ ያሸባሪያን ኃይሎች አቢጃን አቅራቢያ ባለው ታዋቂው የባህር ዳርጃ ክልል በሚገኘው መዝናኛ ሥፍራ በጣሉት ጥቃት ሳቢያ 18 ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን፡ ይኸንን አሰቃቂው በአገሪቱ አሸባሪያን ለመጀመሪያ ጊዜ የተጣለው የሽበራ ጥቃት በማስመልከት የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት “መረጋጋትና ሰላማዊ የጋራ ጥምረት” አደራ እንዳይዳከም የሚማጸን ሐዋርያዊ መልእክት ማስተላለፋቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የሞት አደጋ ስላጋጠማቸው መጸለይ፡ ሰላምን ላደጋ ስለ ሚይጋልጡት ለውጥ መጸለይ

የአግቦዊለ ጳጳስ የአይቨርይኮስት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አለክሲስ ቱአብሊ ዩሎ ፊርማ የተኖርበት የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ያስተላለፈው ሐዋርያዊ መልእክት የሽበራው ጥቃት በተጣለበት ክልል በመረባረብ የተጎዳውን ለመርዳት የሟቾችን ቤተሰብ ለማጽናናት ህዝብ ያሳየው መልካም ተግባር የሚደነቅ ነው በማለት ሁሉንም በዚህ ግብረ ሰናይ የተሳተፉትን አመስግነው በተለይ ደግሞ ልዩ የጸጥታ ኃይሎችን አመስግነው የሞቱት ሁሉ እግዚአብሔር በመንግሥቱ እንዲቀበላቸው የሟቾችን ቤተሰቦች መጽናናቱን እንዲያወርድላቸው እንጸለይ አደራ በማለትን ለሁሉም በአገሪቱ የምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጸሎት በማረጋገጥ ሰላምን የሚያናጉ ማኅበራዊ ብጥብጥ የሚሹትን ሁሉ እንዲለወጡ የክፋት ኃይላቸው ለመካም አገልግሎት ያውሉት ዘንድ ስለ እነርሱ እንዲጸለይ ጥሪ በማስተላለፍ ሰላምና ጸጥታ ዋስትና ለማሰጠትት በሚያደርገው ጥረት ሁሉም ዜጋ ኃላፊነቱን በመወጣት እንዲተባበር እደራ እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አመለከተ።

ብፁዕ አቡነ ቱአብሊ፥ ሸበራና ምስልምና በእኩሉ አለ ማስቀመጥ

የአገሪቱ ብፁዓ ጳጳሳ ባስተላለፈው መልእክት በተለያየ ክልል እክራሪያን ምስሊሞች አሸባሪያን የሚጥሉት ያጥፍተህ ጥፋ ጥቃት ሳቢያ የሚፈጽሙት ቅትለ ከምስልምና ሃማኖት ጋር በማዛመድ ምስላምና ሽብርተኝነት አንድ አድርጎ ለመመከት ፈተና እንዳይዳርግ አደራ። በማሊ በቱኒሲያ በናይጀሪያ ቡርኪናፋሶ እና በሌሎች የአፍሪቃ አገሮ አሸባሪያኑ የፈጸሙት ግብረ ሽበራ ከምስልምና ሃይማኖት ጋር በማመሳሰል አንድ አድርጎ ከመመልከት አደራ መቆጠብ ያስፈልጋል፡ ሆኖም የክልሉ ሙስሊሞች የተጣለው የሽበራ ተግባር ከሁሉም ከተለያዩ ሃይማኖቶችና ዜጎች ጎን በመሆኑ ሊወግዙት ያስፈልጋል እንዳለ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.