2016-03-17 08:42:00

የኢትዮጲያ የካቶሊካዊያን ጳጳሳት አጠቃላይ ጽዕፈት ቤት;- የቅዱስ ልዩ የምህረት ዓመትን መልዕክት በመላው ሀገሪቱ ሬዲዮን ተጠቅሞ ለማስተላለፍ ወሰነ።


 

የኢትዮጲያ የካቶሊካዊያን ጳጳሳት አጠቃላይ ጽዕፈት ቤት በቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ የታወጀውን ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት ኢዩበሊዩ በሀገሪቷ ለሚገኙ ምዕመናን ሁሉ የቦታ እርቀት ሳያገደው ለማውጅ ሁሉንም የመገናኛ ዘዴዎችን ለመጠቀም በወሰነው መሰረት የተለያዩ ዋና ዋና የሚባሉ የሬዲዮ ጣቢያዎችን በመጠቀም በአማሪኛ ቋንቋ በሀግሪቷ ውስጥ ለማስተላለፍ መወሰኑ የጽዕፈት ቤቱ ቃል አቃባይ የሆነችው ማክዳ ዩሓንስ ማሳወቋ ተገለጸ።

 

“ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በአወጁት ቅዱስ የምህረት ዓመትን ምክንያት እኛም ይህንን የምህረት ጥሪ ለካቶሊክ እምነት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ለመላው የሀግሪቱ ሕዝብ ለማስተላለፍ ያስችለን ዘንድ ውጤታማ የሆነውን የሬድዮ የመገናኛ ዘዴ” መመርጡን የገለጸችው የጽዕፈት ቤቱ ቃል አቃባይ ማክዳ ዩሐንስ በሀገሪቷ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ከሀገር ውጭ ለሚገኙ ሁሉ   ኢንተርኔት በመጠቀም የቀጥታ አገልግሎት ማግኘት እንድሚችሉ ገልጻለች።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ ያወጁትን ቅዱስ የምህረት ዓመት እንደ ኢትዮጲያ ባሉ ከ10 ሰዎች መካከል 9ኙ ሰዎች የተሌቪዥን እና ዕለታዊ ጋዜጣ በማያገኝበት ሰፊ ሀገር፣ በአካል ተግኝቶ መመስከር አስቸጋሪ መሆኑን የገለጹት ቃል አቃባዩዋ በገጠራማ የሀገሪቷ ክሎች ድረስ የምህረት ዓመት ምልዕኩት ይዳረስ ዘንድ የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በተለይም ወጤታማ የሆነውን የሬድዮ ተክኖሎጂ መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን በማውሳት ይህ የሬድዮ አገልግሎት በቀላሉ በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ቅዱስ ልዩ የምህረት ዓመትን መልዕክት ለማወጅ አስፈላጊ የሆነውን ዝግጅት ሁሉ ማከናወናቸው ጨምሮ ተገልጿል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.