2016-03-16 16:34:00

በምኅረት ዓመት ላይ ያተኮረ ዓውደ አስተንትኖ በጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ


በጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ ኢዮበልዩ የምኅረተ ዓመት ምክንያት በማድረግ እ.ኤ.አ. መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀትር በፊት በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ 11 ሰዓት ክሩብ የቦሰ ማኅበረሰብ መሥራችና የማኅበሩ አበምኒየት ኣባ ኢንዞ ቢያንኪ ከአቢይ ጾም ጋር በማያያዝ  የእግዚአብሔርን ምኅረት አበስሩ በሚል ርእስ ሥር አስተንትኖ እንደሚያቀርቡ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ምኅረት ሃይማታዊ ስሜት ከመሆኑ በፊት ሰብአዊ ስሜት ነው። ስለዚህ ይኽንን ሰብአዊ ስሜት ሕያው የሚያደርግ ኅብረተሰብ በሰላም የመኖና በፍትሕ ጎዳና የመጓዝ ክህሎት እንደሚኖረው የሚያረጋግጥ የምኅረት ሰብአዊ ማኅበራዊ ሃይማኖታዊ ገጽታው ሥር ሰፊ ትንተና እንደሚሰጡ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ፥

የአስተንትኖው ጉባኤ ንግግር በማሰማት የሚያስጀምሩት ዓውደ አስተንትኖውን ለሚያስተናግደው የጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ ዋና አስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ኤንሪኮ ዳል ኮቮሊ መሆናቸው ገልጦ፡ አባ ቢያንኪ በጋለ ስሜትና አመክንዮ እምነት መስካሪ ናቸው። በዚህ እምነት በዛለበ ተዛማጅነትና የሞት ባህል በተስፋፋበት ገዛ እራስ ዋቢ የሚያደርግ እኔ ባለቤትነት መመዘኛው የሚያደግ ሃይማኖት መሳይ ኢሃይማኖት ባህል እየተስፋፋ ባለበት ዓለም መለኰታዊ ምኅረት ዙሪያ የምኅረት ጥልቅ ትርጉም የሚያብራራ አስተንትኖ ማቅረብ እጅግ አስፈላጊ ነው እንዳሉ ያመለክታል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.