2016-03-14 16:01:00

ብፁዕ አቡነ ጋላገር፥ የኃይማኖት ነጻነት በዓለም ለከፋ አደጋ መጋለጥ


የሮማ ሰበካ በአቢያተ ክርስቲያን የወንጌላዊ ተልእኮ የትብብር ማኅበር “ቤተ ክርስቲያናችን የሰማዕታት ቤተ ክርስቲያን” በሚል ርእስ ሥር ባዘጋጀው ዓውደ ጥናት በክብር እንግድነት በመሳተፍ አስተምህሮ እንዲያቀርቡ ጥሪ የተደረገላቸው የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነ ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ፓውል ሪቻርድ ጋላገር፥ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በዓለም ለከፋ አደጋ እየተጋለ ያለው የሁሉም ሰብአዊ መብትና ክብር መሠረት የሆነው የኃይማኖት ነጻነት ዋስትና ለማሰጠት የተቻለው ሁሉ እንዲያደግ ጥሪ አዘል ንግግር በማሰማት፥

አድልዎ እየሰፋ ነውና ይኸንን አደጋ እንዲገታ የዓለም አቀፍ መንግሥታት ቁርጠኛ ተግባር

ከዚህ ቀደም ባልታየ ፍጥነትና ስፋት እየተዛመተ ላለው አድልዎ አለ መቀባበልና አለ መቻቻል አክራሪነትና ጸንፈኛነት የመሳሰሉት በተጨባጭ መልኩ የሃይማኖት ነጻነትና ባጠቃላይ ኅልውና ለአደጋ የሚያጋልጥ ተግባር ለዓለም አቢይ ተጋራጦ ነው። የሰው ልጅ መሠረታዊ መብትና ክብር ብሎም ባጠቃላይ የዴሞክራሲው ሥርዓትና የዓለም አቀፍ ጸጥታና ደህንነት ለማስከበር የዓለም አቀፍ መንግሥታ ተጨባጭ ተግባር እውን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ካጠናቀሩ ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

ለአክራሪነት መሠረት ኃይማኖ ማርከስ የሚመለከት የመቅጫ ሕግና የጦር መሳሪያ ንግድ

ብፁዕነታቸው ባስደመጡት ንግግር አክራሪነትና ጸንፈኝነት ርእስ ላይ በማተኰር የሃይማኖት አክራሪነት የሚያስፋፋው ሃይማኖት ማርከስ በሕግ የሚያስቀጣ እንዲሆን እየተባለ በመቅጫ ሕግ የማስፈሩ ውሳኔ ይኽ ደግም ካንተ የተለየው ኃይማኖት ተከታይ ተገቢው የሃይማኖት ነጻነት ለመርገጥ የሚገፋፋ የብዙሃኑ ኃይማኖ የህዳጣኑን ኃይማኖት አምባገነን እንዲሆን ተግባር በዓለም እያስከተለው ያለው አደጋ ምን ተመስሎውን በማብራራት የዓለም አቀፍ ሕግ የሚጻረር ሕገ ወጣዊ የጦር መሣሪያ ንግድ መሳፋፋት በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ግጭት እልባት እንዳያገኝ እያደረገም ነው እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ ገለጡ።

የክርስቲያኖች ነጻነትና የእኩልነት መብት ማረጋገጥ

እየተስፋፋ ያለው የክርስቲያኖች ጸዓት በፍላጎት ሳይሆን በተለያየ ምክንያት የተነቃቃ ነው፡ ከሶሪያ ባጠቃላይ ከመካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም ከሊቢያና ናይጀሪያ ከተለያዩ ሌሎች አገሮች ማኅበረ ክርስቲያን ለስደት የሚዳርጉ ጸረ ሰብአዊ ተግባሮች በመስፋፋት ላይ ናቸው። በምዕራቡ ዓለምም ቢሆን የዴሞክራሲ እሴቶች ለማስከበር በሚል ሰበብ ብዙን ጊዜ አድልዎ ሲፈጸም ይታያል ያሉት ብፁዕ አቡነ ጋላጋር፥

የሃይማኖት ነጻነት ማነቃቃት እንጂ መወሰን ይቅር

በአሁኑ ወቅት በዓለም በሃይማኖት ምክንያት የሚሰደዱት የሚገደሉት ባጠቃላይ ለተለያየ አደጋ በስፋት የሚጋለጠው ማኅበረ ክርስቲያን መሆኑ ለማንም የተሰወረ አይደለም። ቅድስት መንበር ይኸንን ጉዳይ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ድምጻዋን ከፍ በማድረግ ስታብራራ ቆይታለች። የሁሉም ሰብአዊ ክብርና መብት መሠረት የሆነውን የሃማኖት ነጻነት ለማስጠበቅ በምታካሂደው ጥሪ አማካኝነት የተለያዩ የውይይት መድረኮች እውን እንዲሆን እያደረገችም ነው። ይህ የምታካሂደው ጥሪ በዓለም አቀፍ መድረኰች ሁሉ ተደማጭነት እያገኘም መጥቷል እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አያይዘው፥

ድኽነት ማጥፋት መሃምነትን መዋጋት ውይይት ማነቃቃት

አክራሪነትና ጸንፈኛነት ከሥር መሰረቱ ለማጥፋ የሚቻለው አክራሪነትና ጸንፈኛነት እንዲቀሰቀስ ምክንያት የሆነውን ኢፍትሐዊነት ማኅበራዊ መሃይምነትና ድኽነት ቀድሞ መዋጋት ያለው አስፈላጊነት ያብራሩት ብፁዕ አቡነ ጋላገር በዚሁ ዘርፍ ቅድስት መንበር ድኽነት ለመቅረፍ መሃይምነት ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ሁሉ ቀዳሜ በመሆን በቃልና በተግባር አቢይ አስተዋጽኦ እየሰጠች መሆንዋ ለማንም የተሰወረ አይደለም እንዳሉ ገልጠዋል።

ብፁዕ አቡነ ጋላገር ያስደመጡት ንግግር፥ በጦርነትና በሃይማኖት ነጻነት ረገጣ ምክንያት ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ የሚጋለጡትን ለመደገፍ ሁሉም አቅሙና ኃይሉን በማስተባበር የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ እንዲስፋፋ በማደግ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ መንግሥታት አቢይ ጥረት በማድረግ ለሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቂ እንዲተባበሩ ጥሪ በማቅረብ ማጠቃለላቸው ፒሮ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.