2016-03-14 15:58:00

ቅዱስ አባታችን በክራኮቪያ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 27 ቀን እስከ ሐምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም.


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 27 ቀን እስከ ሐምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገረ ፖላንድ ክራኮቪያ ከተማ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት “ምሕረትን የሚያደርጉ ምሕረትን ስለሚያገኙ ደስ ይበላቸው” (ማቴ. 5,7) በሚል ወንጌላዊ ቃል ሥር ተመርቶ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እንዲገኙ የአገሪቱ አበይት የመንግሥት አካላትና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጥሪ እንደተደረገላቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይፋ አደረገ።

ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. መስከረም ወር 2015 ዓ.ም. ለዚያ በክራኮቪያ ሊካሄደው ስለወሰኑት ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት የእግዚአብሔ የላቀው ደስታ መርሐሪነቱ ነው። ምሕረት ወይንም ይቅር ባይነት ተራ መልካምነት መኖር ወይንም ስሜታዊ ተግባር አይደለም ምክንያቱም የእግዚአብሔር መሐሪነት ፍትህ ነው፡ የክፋትን መንፈስ በሙላት ለማሸነፍ ብቸኛው መንገድ ምሕረት ነው፡ ፍትሕ አስፈላጊ ነው፡ ሆኖም ለብቻው በቂ አይደለም ይህ ማለት ደግሞ ፍትህና ምሕረት ባንድ ላይ መጓዝ ስላለባቸው ነውና። የሚል ጥልቅ ሃሳብ እንዳሰመሩበት ያስታወሰው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ይኽ በክራኮቪያ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቅድስና ከታወጀላቸው ወዲህ የመጀመሪያ መሆኑ በማስታወስ ሲያመለክት፡ ይኽ በእንዲህ እንዳለም እንደ መርሐ ግብሩ መሠረት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. በ 2016 ዓ.ም. በክራኮቪያ በሚካሄደው 31ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶ ቀን ምክንያት እ.ኤ.አ. ሐምሌ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ክራኮቪያ ይገባሉ። እዛው ከአገሪቱ ርእሰ ብሔርና በፖላንድ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓ ጳጳሳ ምክር ቤት ጋር ይገናኛሉ። በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ወደ ምሽቱም በክራኮቪያ ከሚገኘው ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለወጣቶች ሰላምታቸውን ያቀርቡበት ከነበረው ጳጳሳዊ ሕንጻ ካለው መስኮት ሆነው ለ31ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተሳታፊያንን ሁሉ ሰላምታን ያቀርባሉ።

እ.ኤ.አ. ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ ክዞስቶቾዋ በመጓዝ በቅድስተ ማርያም ቅዱስ ምስል ፊት ጸሎት አሳርገው አገረ ፖላንድ ጸጋ ጥምቀት የተቀበለችበት 1 ሺሕ 50 ዓመት ምክንያት መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጉሉ።

አርብ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. የእልቂት ሰፈር አውሽዊዝና ቢርከናውን ከጎበኙ በኋላ በክራኮቪያ የፍኖተ መስቀል ሥነ ስርዓት ይመራሉ።

ቅዳሜ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በላጋይዊኪ የሚገኘው የመለኰታዊ ምኅረት ቅዱስ ሥፍራ ይጎበኛሉ። በዚያ ቅዱስ ሥፍራም ቅዱስ አባታችን በቅዱስ በር በማለፍ ቅድስት ፋውስቲና ኮዋስካ ቅዱስ አጽም ወዳረፈበት ቤተ ጽሎት መንፈሳዊ ንግደ ያከናውናሉ። ከፖላንድ ለካህናትና ለገዳማውያንና ለዘርአ ክህነት ተማሪዎች በአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ታጅበው መሥዋዕተ ቅዳሴ ያቀርባሉ፡ እዛው የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ፍጻሜ ዋዜማ በሚከናወነው የጸሎት ሥነ ስርዓት በመሳተፍ ላንዳንድ ወጣቶች ምስጢረ ንስሐ ይሠራሉ።

እሁድ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. ለዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መዝጊያ የሚያርገው መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው መሪ ቃል ለግሰው ለወጣቶች የምሕረት መስካሪያን እንዲሆኑ የምሕረት ልኡካን በማረግ የተልእኮ ኃላፊነት ካስረከቡ በኋላ ከሰዓት በኋላ በዚያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በተለያየ መስክ በበጎ አድራጎት ተሰማርተው ካገለገሉት ወጣቶች ጋር ከተገናኙ በኋላ የሽኝት ሥነ ስርዓት ተድርጎላቸው ወደ አገረ ቫቲካን እንደሚነሱ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.