2016-03-12 11:11:00

በትዳር ውስጥ ብዙ ችግሮች የሚታዩ ቢሆንም እነዚህ ችግሮች ግን በትዳር ዋንኛ እሴት ላይ አደጋ ሊደቅኑ አይገባም ።


በመጋቢት 11.2016 ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ እና ሌሎች ጳጳስት በተገኙበት በአውሮፓዊያን የስርዓተ ሊጡርጊያ አቆጣተር አራተኛውን የዓብይ ጾምን ሳማንትን አስመልክትው በቫቲካን የጳጳስ ቤት ሰባኪ የሆኑት አባ ራኔሮ ካንታላሜሳ ትኩረታቸውን በቫቲካን ሁለተኛ ጉባሄ   ሰአነድ ጋውዲዩም ሄት ስፔስ ወይም (ድስታ እና ተስፋ) በሚልው ሰንድ ላይ በመመርኮዝ ጋብቻን እና ቤተስብን ያማከለ ስብከት ማድረጋቸው ተገለጸ።

አሁን ባለንበት ወቅት በትዳር ውስጥ ብዙ ችግሮች የሚታዩ ቢሆንም እነዚህ ችግሮች ግን በትዳር ዋንኛ እሴት ላይ አደጋ ሊደቅኑ አይገባም ያሉት አባ ራኔሮ ካንታላሜሳ አሁን ባለንበት ዓለም እግዚአብሔር የሚፈልገው፣ ቅዱስ ወንጌላችን በምያዘው እንዲሁም የሰው ልጅ ተፈጥሮ በምያስተምረን መልኩ ሳይሆን ጋብቻ እየተከናወነ የሚገኘው በብዙ ቦታዎች የጋብቻ ጽንሰ ሐሳብ እየተለወጠ መምጣቱ አሳሳቢ መሁኑን ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት ባለንበት ዘመናዊ ዓለም የቤተሰብ ህልውና አደጋ ላይ እየወደቀ ይገኛል ብለው እኛ ክርስቲያኖች ግን ይህንን አደጋ ላይ የሚገኘውን የጋብቻ ህልውና የመታደግ መንፈሳዊ ግዴታ እንዳልን በማወቅ የሰው ልጅ ተፈጥሮ በምያዘው መልኩ እና እግዚአብሔር የሚፈለገውን ዓይነት ጋብቻ በሕይወታችንም ጭምር ለዓልም መመስከር እንድሚገባ አበክረው ገልጸኋል።

አባ ካንታላመሳ በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንዳሳሰቡት ጋብቻ ቅዱስ የሆነ የቤተሰብ መመስረቻ ቁልፍ መሆኑን ገልጸው በምንኩስና የሚኖሩ ወንዶች እና ሴቶች ሁሉ ትክክለኛውን የጋብቻ መንፈስ ለምዕመናኖቻቸው ማስተማር ይጠበቅባቸዋል ብለው ክርስቲያኖችም ምንም ዓይነት ፈተና በትዳራቸው ውስጥ ቢፈጠርም በትዕግስት እና በእግዚአብሔር  ቃል ላይ ተመርኩዘው ግጭቶችን በማርገብ ለልጆቻቸውም ትክክለኛዉን የትዳር ትርጉም በማስተማር ዘመናዊነት በትዳር ላይ በደቀነው አደጋ ሳይሸበሩ እና የዚህ አፍራሽ ርዕዮተ አለም አስተሳሰብ ሳያሰናክላቸው ክርስቲያናዊ መንፈሳቸውን ጠብቀው ይጉዙ ዘንድ ማስተማር ይጠበቅባቸዋል ብለው ስብከታቸውን አጠቃልለዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.