2016-03-10 14:44:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ በመጋቢት 13.2016 ርእዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሆነው የተመረጡበትን ሦስተኛ ዓመት ያከብራሉ።


 

በመጪው እሁድ ማለትም በመጋቢት 13.2016 ርእዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሆነው የተመረጡበትን ሦስተኛ ዓመት የሚያከብሩት ቅዱስ አባታችን ርእዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮን አስመልክቶ የበኩላቸውን አስየያየት  የሰጡት በቅድስት መነበር ፕሬስ ቢሮ ዳይሬክተር የሆኑት አባ ፌሬድርኮ ሎባርዲ እንደገለጹት ቅዱስ አባታችን በዓለም ላይ ምርጥ የሚባሉ መንፈሳዊ መሪ ናቸው ማለታቸውን ጋዜጠኛችን አሌሳድሮ ጂዞት ዘግቡኋል።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ በቤተ ክርስቲያን እና በዓልም ለሚኖሩ የሰውን ልጆች ሁሉ አስተማሪ ሆነው ይቀጥላሉ የሚል ግምት አለኝ ያሉት አባ ፈረድሪኮ ሎምባርዲ፣ ምክንያቱ ርእዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሆነው ከተመርጡ  ሦስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከኦቻይና አህጉር በስተቀር የተቀረውን የዓልም ክፍል መጎብኘታቸው እና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ስለ ሰዎች ሕይወት ክቡርነት፣ ስለ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል፣ ጦርነትን በማውገዝ ሰላም ይሰፍን ዘንድ በመማጸናቸው፣ አሁን ባለንበት ዘመን ስላለው የማህበራዊ ሁኔታ፣ እንዲሁም በዛሬ ዘመን ስለምትገኛው ቤተክርስቲያን ያላቸው ጠንካራ አቋም እና የመሳሰሉት ሁሉ በብዙዎቹ ዘንድ በተለይም በብዙኋኑ በድኽነት አረንቋ የሚማቅቁ የማህበረሰብ ክፍሎች  ዘንድ ተቀባይነትን እና አድናቆትን በማትረፉቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም አሁን  ባለንበት ዓለም ለሚነሱትን አንገብጋቢ ጥያቄዎች በተለይም ደግሞ አሁን ስላለው እና ስለ የወደፊቱ የማህበረሰብ ሁኔታን ከግምት ያስገባ ‘ላውዳቶ ሲ’ በሚል አርስት ያሳተሙት ሓዋሪያዊ መልዕክታቸው ከመላው ዓለም አድናቆትን ያስገኘላቸው እንደነበረ አባ ሎምባርዲ ገልጸው ‘በዚህ ወከባ እና ጥድፍያ በበዛበት ዓለማችን በዚህ ወከባ ሰለባ ይሆኑ የማህበረስብ ክፍሎችን ትክክለኛውን እና የእውነትን መንገድ ይከተሉ ዘንድ፣ በሕይወት መስክርነት የታጀበ አስተምሮ እና ምስክርነት በመስጠታቸው ጭምር ይብልጡኑ እንዲታመኑ እና እንዲወደዱ አደርጉኋቸውል ብለዋል።

በዓለማችን ላይ ብዙ መርጥ ሊባሉ የሚችሉ መሪዎች ቢኖሩም፣ እውነታው የሚያሳየው ግን እውነት ላይ ተመርኩዘው በሚያደርጉት አስተምሮ እና የሕይወት ምስክርነት፣ እንደ ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ ታማኝ መንፈስዊ እና ግብረገብን የተጎናጸፈ መሪ ማግኘት ያስቸግራል ያሉት አባ ፈሬድሪኮ ሎምባርዲ፣  በዚህ ምድር የሚገኙ ሀያላን መንግስታት ሳይቀሩ እርሳቸው የሚሉትን ማዳመጣቸው እና በተለይም ስለ ሰላም እና ስለፍትህ የሚያደርጉት ጥሪ ምርጥ መንፈሳዊ መሪ እዲሰኙ ካድርጉዋቸው ነግሮች መካከል ይጠቀሳሉ በለዋል።

በተለይም አሁን ባለንበት ወቅት ያወጁት ልዩ የምህረት ዓመት አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል እግዚኣብሔር ፍቅር እንደ ሆነ እንዲረዳ ያደረገና በተጨማሪም ብዙዎቹን ወደ ትክክለኛው መንገድ እንዲመለሱ ያገዘ ጭምር በመሆኑ ብዙሀኑን ከጥፋት መንገድ መታደጋቸውም ሊጠቀስ የሚገባው መልካም ተጋባራቸው መሆኑን አባ ፌረድሪኮ ሎምባርዲ ጨምረው ገልጸዋል።

በመጨረሻም ለድሀው የማህበረሰብ ክፍል እና በጦርነት ምክንያት በስደት ላይ ለሚገኙትን ሰዎች ሁሉ ትኩረት እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ጥሪ በማቅረባቸው፣ እንዲሁም በተለያዩ የዓልም ክፍሎች እየተከሰቱ የሚገኙትን ጦርነቶች ማብቅያ እንዲኖራቸው እና በጣም ጥቂት ሊባል የሚችለውን የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ያደረገ እና በአንጻሩም፣ አብዛኛውን የዓልም ማህበረሰብ በድኽነት አረንቍኋ እንዲማቅቅ ያደርገውን የአለማችን የኢኮኖም ርእዮተ ዓልም በተደጋጋሚ ማውገዛቸው ተኩረት እንዲያገኙ አስችሉኋቸዋል በማለት አስተያየታቸውን አጠቃልለዋል።

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.