2016-03-10 16:35:00

ቅ. አ.ፍራንቼስኮ ምህረት አድራጊነት ለሰላም እና ለአንድነት መፈጠር ቁልፍ ሚና ይጫወታል።


በመጋቢት 7.2016 በሮም “የምህረት ልዑክ” በሚል አርስት ላይ ተመርኩዞ እየተካሄደ በሚገኝው አውደ ጥናት ላይ እንደተገለጸው ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ ምህረት አድራጊነት ለሰላም እና ለአንድነት መፈጠር ቁልፍ ሚና እንደምጫወት እና ሦስተኛ የዓለም ጦርነት እንድይነሳ የይቅር መባባል መንፈስ ከፍተኛ አስተውጾ እንደምያደርግ በተለያዩ አጋጣሚዎች መግለጻቸው  እሳቸው እየተጠቀሙበት ያለው ይህ ሓውሪያዊ  ዜዴ ከፍተኛ ውጤት እያስገኝ መጣቱን በማውሳት አውደ ጥናቱ ተጀምርኋል።

በሁለት እህታማች አብያተ ክርስቲያናት መካከል ለዓመታት የዘለቀው ውዝግብ፣ ቅዱስ አባታችን በኩባ ከሞስኮ እና ከጠቅላልው ሩሲያ ፓትሪያርክ ክሪል ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው በወያየት ለዓመታት የዘለቀውን ውጥረት ማርገባቸው፣ ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ በሚደርገው የስደተኞች ፍሰት ምክንያት ለብዙ ጊዜ መግባባት ላይ መድረስ ያቃታቸው በእነዚህ ሁለት ባላንጣ ሀገሮች ድንበር በምትገኘው ቹዳድ ሁኋሬዝ በትባል ከተማ ተገኝተው ስርዐተ-ቅዳሴ ማሳረጋቸው እና በዝያች ከተማ የሚታየውን ማህበራዊ ቀውስ ዓለም ትኩረት እንዲሰጠው በማስቻላቸው፣ በተጨማሪም ርእዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሆነው ከተመረጡ ቡኋል የመጀመሪያቸው በሆነው በነሐሴ 8,2013 ከሦስት ሺ በላይ የሚጠጉ ስደተኞች በባህር ላይ በተከሰተው አደጋ ሕይውታቸውን  ወደ አጡበት የጣሊያን የወደብ ከተማ ላፓዱዛን መጎብኘታቸው እና በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡት ነብሳቸውን በዚህ አሰቃቂ ሁኔታ በማጣታቸው ሀዘናቸውን ገልጸው ዓለም ለስደተኞች ትኩረት እንዲሰጥ ማድረጋቸው እና አንዲሁም የተረሱ የሕብረሰብ ክፍሎች ሁሉ ይታወሱ ዘንድ በሚያቀርቡት ጥሪ ምክንያት ጭምር ዓለም ውስጥ የወንድማማችነት መንፈስ እንዲኖር እያስቻሉ በመሆኑ “ምህረትን” እንደ አንድ ወጤታማ የፓሌቲካ ዘዴ መጠቀባቸውን ስለሚያሳይ፣ በፖሌቲካ ተግባር ለተሳተፉ ሰዎች ሁሉ ትልቅ አስተምሮን ያስተላለፈ እንደነበር በጉባሄው ወቅት መወሳቱን የካቶሊክ ስልጣኔ የተሰኘው ቢሮ አላፊ እና “የፍራንቼስኮ ዲፕሎማሲ” በሚል አርስት መጽሓፍ ያሳተሙ አባ አንቶኒዮ ስፓድሮ በጉባሄው ወቅት ገልጸዋል። 

መሰረታዊው የምህረት አድራጊነት ጽንስ አሳብ “መሸነፍ ወይም ማጣት” ተደርጎ መወሰድ የለበትም ያሉት የአውደ ጥናቱ አስተባባሪ አባ አንቶኒዮ፣ በአንጻሩ፣ ሊወሰድ የሚገባው በሀገራት መካከል ሰላም እንዲፈጠር እንዲሁም በማህበርሰብ ወስጥ በግልም ሆነ በቡድን በተሰሩ ስህተቶች ምክንያት ለተፈጠር ማንኛውም ዓይነት ቁርሾ ፈውስ የምያስገኝ ተደርጎ ልወሰድ ይገባል በለዋል።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ ብዙን ጊዜ  የጥል ግድግዳ ሊገረሰስ የሚችለው እና በአንጻሩም ሰላም ልፈጠር የሚችለው በይቅርታ ብቻ መሆኑን እዳስገነዘቡን፣ በተግባርም ለዓመታት የቆየውን በኩባ እና በአሜርካ መካከል የነበረውን አለመግባባት በይቅርታ መንፈስ በመገርሰሳቸው እና ተመሳስይ የሆኑ ይፋዊ እና የፋዊ ያልሆኑ ምህረት አድራጊነትን የተመረኮዙ ወጤታማ ተጋባራትን መፈጸማቸው የሚያሳየው ምህረት ማድረግ ከእግዚኣብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት የሚያጠናክር ቢቻ ሳይሆን እርስ በእርሳችን በሰለም እንድንኖር ጭምር የምያስችል ውጤታማ ዘዴ መሆኑም ተውስቱኋል።

እንደ ሚታወሰው ቅዱስ አባታችን በደቡብ ኮሪያ ካደረጉት ሐዋሪያዊ ጉብኝት ቡኋላ “በዓለም ውስጥ የሚታዩ አንደ እራስ ወዳድነት፣ ሰባዊ እሴቶችን የሚጋፉ ተግባራትን፣ በጣም እየተንሰራፋ የመጣውን ድህነት እና በአጠቃልይ በሰው ልጆች ተፈጥሮ ላይ የተቃጣ የመጣው አደጋ እስካልተወገዱ ድረስ ሦስተኛ የዓለም ጦርነት መነሳቱ አይቀርም” ማለታቸውን ያስታወሱት የጣሊያን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ፒየትሮ ግራሶ፣ ቅዱስ አባታች ፍራንቼስኮ የሚጠቀሙት ምህረትን መሰረት ያደረገ ዲፕሎማስያዊ ግንኙነታቸው ወጤታማ በመሆኑ በተለይም አሁን በምንገኝበት ጦርነት እና ሽብር በበዛበት ዓለማችን ሰላምን ማምጣት የሚቻለው ይቅር በመባባል ብቻ እና ቅዱስ አባታችን እንደገለጹት ግድግዳን በመገንባት ሳይሆን ችግሮች መፈታት ያለባቸው መሸጋገርያ የሆነውን የምህረት ድልድይ በመግንባት መሆኑን ገልጸው አውደ ጥናቱ ተጠናቁኋል።

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.