2016-03-08 09:21:00

“መንፈሳዊ እውርነት መልካምን ነገር እንዳናከናውን በማድረግ፣ ፣ከእግዚአብሔር እና ከወንድሞቻችንም ጋር በሰላም እንዳንኖር ያደርጋናል”


እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በህዳር 4,2016 የዓብይ ጾምን እና የያዝነውን ቅዱስ የምህረት ዓመትን አስመልክቶ “24 ሰዓት ለእግዚኣብሔር” በሚል አርስት፣ ሚስጢረ ንስሓን ትኩረት በማድርገ እና ክርስቲያኖችን ወደ ንስሓ  እንዲመልሱ ለማስቻል በማሰብ በመላው ዓለም የተደረገው መንፈስዊ ዝግጅት አካል የሆነው በቅዱስ አባታች ፍራንቼስኮ መሪነት በቫቲካን በተካሄደው ዝግጅት ላይ እንደገለጹት “መንፈሳዊ እውርነት መልካምን ነገር እንዳናከናውን በማድረግ፣ አርቆ የማያስተውል ልብ በውስጣችን በመፍጠር፣ ከእግዚኣብሔር እና ከወንድሞቻችንም ጋር በሰላም እንዳንኖር ያደርጋናል” ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን በዝግጅቱ ወቅት  ለብዙ ምዕመናን የሚስጢረ ንስሓን አገልግሎት የሰጡ ሲሆን በተመሳስይ በሮም የሚገኙ አብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያነት ሌሊቱን በሙሉ በራቸውን ሚስጢረ ንስሓ ለሚፈልጉ መዕመናን ከፍት አድርገው እንደነበረ ለመረዳት ተችሉኋል።

“ሓጥያት መንፈሳዊ እውርነትን በማስከተል መልካም የሆኑ ነገሮችን እንዳንፈጽም ያግደናል ያሉት ያሉት ቅዱስ አባታችን፣ በተጨማሪም በሕይወታችን ወስጥ በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች እንዳንመለከት በማድረግ፣ ቀስ በቀስ ሕይወታችንን ወደ አዝቅት ወስጥ በመክተት፣ መልካም ለሆኑ ነገሮች ስሜት እንድናጣ ያደርገናል” ብለዋል።

“በሕያወታችን ወስጥ ብዙ ፈተናዎች አሉ” ያሉት ቅዱስ አባታችን እነዚህ ፈተናዎች ልባችንን በማጨለም እና ማስተዋል እንዳንችል በማድረግ፣ ሕይወታችን የሚለካው ባለን ንብረት ወይም ከሰዎች በምናገኘው ሙገሳ ላይ ብቻ እንደ ሆነ እንዲሰማን በማድረግ፣ በንግድ ሥራ የተመሰረቱትን ሰዎች ሁሉ ደግሞ ሰዎችን በመበደል በማንኛውም መንገድ ትርፍን ብቻ ማጋብስ አስፈላጊ መሆኑን በማሳመን፣ እንዲሁም ግለሰባዊ አመለካከት ከማህበርሰባዊ አመለካከት በላይ ጎልቶ እዲወጣ በማድረገ እና በተጨማሪም እራስ ወዳድ እንድንሆን በማድረግ የእራስችን ጥቅም ብቻ እያሳደድን እንድንኖር ያደርገናል ብለዋል።

በአንጻሩ ደግሞ የብርሃን መንገድ የሆነውን ኢየሱስን በምንመርጥበት ጊዜ፣ ልባችን ማስተዋል እንዲጎድለው ያደረገውን የጨለማ ሕይወት በማስወገድ፣ የጎደለን ነገር እንዳለን እንድንረዳ በማድረግ፣ ከዚህ የጨለማ ኑሮ እንድነውጣ የሚረዳንን የልባችንን ጨለማ ለማስወገድ የምያስችለንን ብርሃን በመስጠት ወደ እራሱ የጋብዘናል ብለዋል።

የኢየሱስ በሕይወታችን ውስጥ መገኘት ሕይወታችንን በደኋንነት፣ ልባችንን በመፈወስ በደስታ እንድንሞላ ያደረገናል ያሉት ቅዱስ አባታችን ሓጥያተኞች  እንደሆንን እንዲሰማን በማድረግ፣ የያዝነው የሓጥያት መነገድ በመቀየር ወደ እርሱ እንድንመለስ ጥሪ ያደርግልናል ብለዋል።

በተለይም ደግሞ በዚህ በያዝነው ቅዱስ የምሕረት ዓመት አጋጣሚወን ተጠቅመን እግዚኣብሔርን በሕይወታችን እንድናስገባው እና ከእርሱ ከማያልቀው የፍቅር መሀድ ተካፋይ እንዲያደርገን ወደ እርሱ በንስሓ መመለስ ይጠበቅብናል ያሉት ቅዱስ አባያችን ወደ እርሱ እንዳንቀርብ የሚያደርጉንን ነገሮች ሁሉ አውልቀን በመጣል፣ ያለ ምንም ፍረሃት እና ጥርጣሬ ምህረቱን እንዲሰጠን አጥብቀን የምንለምንበት ወቅት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በተለይም ደግሞ መልካም እረኛ እንዲሆኑ የተጠሩ ካህናት የእግዚኣብሔርን ምህረት በመሻት ጩኸታቸውን የምያሰሙትን ምዕመናን ማዳመጥ ይኖርባቸዋል ያሉት ቅዱስ አባታችን ሓጥያተኛው ወደ እግዚኣብሔር በንስሓ እንዳይመለስ እንቅፋት የሚሆኑትን ሰብዓዊ ደንቦችን  በማስወገድ ሓጥያተኛው ወደ እግዚኣብሔር እንዲመለስ ልናግዝ የገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን “እኛ ካህናት የተጠራነው ሰዎችን ወደ እግዚኣብሔር መነገድ እንዲመለሱ ለማድረግ እና እጁን ዘርግቶ በድስታ ወደ ሚጠብቀን ወደ እግዚኣብሔር መመራት መሆኑን በመረዳት ይህንን የተሰጠንን ከፍተኛ አላፊነት በመወጣት፣ የልባችንን ጨለማ በመገፈፍ ልባችን እንዲነካ የሚያደርገው አንዱ እግዚኣብሔር ብቻ መሆኑን ተረድተን፣ በትጨማሪም መንፈስዊ ለውጥ በሰው ሕይወት እንድናመጣ ብቻ ሳይሆን የተጠራንው ሁኔታዎችን በማመቻቸት ግለሰቦች እግዚኣብሔርን እንዲያገኙት በማድርግ መንፈስዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችለውን ፀጋ ከእግዚኣብሔር እንዲያገኙ መርዳት መሆኑን በመረዳት የመሪነቱን ሚና በአጋባቡ ልንወጣ ያስፈልጋል ብለዋል።

ወደ ንስሓ የሚመጡ ምዕመናን ሁሉ የሚፈልጉት ሓጥያታቸውን በሚገባ እንዲናዘዙ የሚረዳቸውን፣ የምያዳምጧኋቸውን፣ በፍቅር የሚቀበሉኋቸውን እንዲሁም ይቅር የሚሏኋቸውን ካህናት በመሆኑ፣ ኢየሱስ የመረጠንም ይህንን ዓይነት አገልግሎት እንድናከናውን መሆኑን ተርድተን ለተሰጠን ሐላፊነት ታማኝ በመሆን ምዕመናንን በንስሓ ሕይወታቸው ልናግዛቸው ይገባል በማለት አስተምሮኋችወን አጠቃልለዋል።

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.