2016-03-07 16:27:00

አባ ሮንኪ፥ መንፈሳዊ ሱባኤ የወንጌል ውበት ለመኖር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንስቸኮና የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የሮማዊት ቤተ ክርስቲያን ምክር ቤቶችና ቅዱሳት ማኅበራ ተጠሪዎች የበላይ ብፁዓን ካዲናሎችና ብፁዓን ጳጳሳት በዓቢይ ጾም ምክንያት መንፈሳዊ ሱባኤ ለማካኤድ በላዚዮ ክፍለ ሃገር ወደ ምትገኘው የአሪቻ ከተማ እ.ኤ.አ. መጋቢ 6 ቀን 2016 ዓ.ም. መሄዳቸው የቫቲካን ርዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።

ሱባኤውን በሰባኪነት እንዲመሩ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የማርያም አገልጋዮች ማኅበር አባል አባ ኤርነስ ሮንኪ እንዲሆኑ ጥሪ እንዳቀረቡላቸውም ቸንቶፋንቲ አስታውሰው፣ ቅዱስ አባታችንና ብፁዓን ካርዲናሎችን ያሳፈረው አውቶቡስ እ.ኤ.አ. መጋቢ 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ አራት ሰዓት ላይ ከአገረ ቫቲካን መነሳቱና ሱባኤው ልክ ስድስት ሰዓት ላይ በቅዱስ ቁርባን ፊት ስግደትና አስተትኖ በማስቀደም መጀመሩም ገልጠዋል።

የሱባኤው ርእሰ ጉዳይ የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 1 ቍ. 38 “ኢየሱስ መለስ ብሎ ሲከተሉት አየና፡ ‘ምን ትፈልጋላችሁ?’ አላቸው” የሚለው ቃል እንደሚሆንም ስባኤውን እንዲመሩ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ስልክ ደውለው የጠየቁዋችው ካህን አባ ሮንኪ ከቫቲካ ረዲዮ ጋር ለሱባኤው ከመነሳታቸው ቀደም በማድረግ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልጠው፡ ሱባኤው በዘጠኝ አስተንትኖ የተከፋፈለ እንደሚሆን ነው ብለው የአስተንትኖው ማእከል ቃለ ወንጌል ነው፡ ሱባኤው የማሪያም ተስፋ የሚከተል ነው፡ ምክንያቱም ቅድስት ማርያም ቀዳሜ የኢየሱስ ተከታይ ነችና፡ ስለዚህ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የሚያቀርብላቸው ጥያቄና እነርሱም የሚሰጡት መልስ በመለየት በዚሁ በኢየሱስና በደቀ መዛሙርት መካከል ያለው ውይይት የሚያብራራ ይሆናል፡ ካሉ በኋላ የወጌል ውበትና ውህበት ያለው ኃይል ላይ ያተኰረ ሱባኤ ይሆናል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.