2016-03-07 16:30:00

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊኒ፥ ጋዜጠኛነት ድምጽ ለሌለው ድምጽ መሆን


በኢጣኢያ ማተራ ከተማ የኢጣሊያ የካቶሊክ የመገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች ማኅበር በጠራው ዓውደ ጉባኤ የተገኙት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ባስደመጡት ንግግር፥ የመገናኛ ብዙኃንና ጋዜጠኞች ከማንኛውም ዓይነት መፈክራዊና ርእዮተ ዓለማዊ ምርጫ ተላቀው የሚያስተላልፉ ዜና ሰውን ማእከል ያድርግ አደራ እንዳሉ የቫቲካ ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለንሳንድሮ ጂሶቱ አስታወቁ።

የጋዜጠኝነት ተግዳሮች በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዘመን በሚል ርእስ ተመርቶ በመካሂድ ላይ ያለው ዓውደ ጉባኤ፥ የኢጣሊያ የካቶሊካውያን የመገናኛ ብዙሃን ማኅበር በሊቀ መንበርነት የመሩት ያገልግሎት ዓመታቸውን ያጠናቀቁትን የሚተኩ አዲስ ሊቀ መንበር እንደሚመረጡም የገለጡት ጂሶቲ በማያያዝ፥ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን መልካም ግብረ ገብና ሥነ ምግባር የተካነው የመገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኝነት ሁሉ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዓቢይ ድጋፍ መሆኑ በማብራራት፡ ካቶሊካውያን ጋዜጠኞች ድምጽ ለሌለው ተገፍቶ ለሚኖረው ሁሉ ድምጽ መሆንና ለዜጎች ሁሉ የሚያገልግሉ እምዲሆኑ ይጠበቅባቸዋል እንዳሉ አስታውቀዋል።

የሁነትና የክስተቶችን እውነት አገልግሉ። ድምጽ ለሌላው ድምጽ ሁኑ። እውነትን አለ ማስተጋባት ክዋኔዎችንና ክስተቶችንም መካድና እንዳሻህ ማጠማዘዝ እውነትና ሕዝብ መካድ ይሆናል። ስለዚህ የሚተላለፈው ቃል የሕዝብ አመለካከትና አተኵሮ የሚለይና የሚወስን በመሆኑ እውነት ላይ የጸና ሰዎችን የማያሳስት እንዲሆን አቢይ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው እንዳሉ ጂሶቲ ይጠቁማሉ።

የላቀውን የከበረውን የጋዜጠኝነት ተልእኮ ድምጽ ለሌለው ድምጽ መሆን ነው፡ መድብላዊነት የሕዝቦች የባህሎችና የሃይማኖቶች መቀራረብ ማነቃቃት ነው፡ ስለዚህ የጋዜጠኝነት ስነ ስበአዊ ገጽታው ማኅበራዊ አገልግሎት የሚል መሆኑ ብፅዕነታቸው በማብራራት፡ ዓለማውያን ምእመናን በጋዜጠኝነት ሙያቸው ያንን ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ያሳሰበው እርሱም ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮን ስልጣናዊ ትምርህት ሥር ጠቅሰው ጋዜጠኝነት ቀድሞና ፈጥኖ የሚደርስ ብቻ ሳይሆን በበለጠ ቀድሞ ፈጥኖ ደራሽ መሆን አለበት። ይህ ሲባል ደግሞ በበለጠ ለማገልገል ይጠበባቸዋ ማለት ነው፡ ዜናዎችና ሁኔታዎችን ገጠመኞችን ከማገናኘት በፊት ገዛ እራስ ማገናኘት ያስፈልጋ ብለው። ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያንና ዓለም የሚያገናኝ የእውነት መሣሪያ ይሁን እደራ እንዳሉ ጂሶቲ አመለከቱ።

ጋዜጠኝነትን ክርስቲያናዊ ራእይ አማክኝነት ማደስ

የካቶሊክ የመገናኛ ብዙኃን ዓላማ ጋዜጠኝነትን በክርስቲያናዊ ራእይ አማካኝነት ማደስ የሚል ነው ያሉት ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፥ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ እግዚአብሔርን የምታገለግሉ ዓለማዊ ምአመናን የመሆን ክርስቲያናዊ ጥሪኣችሁን ክብር የሚሰጡ ነጻ ጋዜጠኛ መሆን የሚል ነው። ኢየሱሳውያን ማኅበር ስለ መገናኛ ብዙሃን የሚያረማምዱት የእውነትና የሕዝብ አገልጋይ የመሆን ዓላማ የምትመሩ ናችሁ በዚሁ ጎዳና የመሩዋችሁ ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ሮበርቶ ቱቺ፡ ኣባ ባርቶለመዮ ሶርገ አባ ፓስኳለ ቦርጎመዮ እና ሌሎች የኢየሱሳውያን ማኅበር አባላት ሁሉ አደራ አስታውሱ እንዳሉ ጂስቲ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.