2016-03-07 16:21:00

ሙሉ ውህደት ከመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ ጋር


በኡክራይን የግሪክ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ፍጻሜ የቤተ ክርስቲያናቱ ብፁዓን ጳጳሳት በአገረ ቫቲካን ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር የተገናኙ ሲሆን፡ በመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ መገኘታቸውም ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር ያላቸው ውህደትና ታዛዥነታቸውን ለመመስክር እዲሁም ቅዱስነታቸው የኡክራይንን ሕዝብ እንዲደግፉ አደራ ለማለት መሆኑ በኡክራይን የግሪክ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ሊቀ መበንበር አቢይ ሊቀ ጳጳሳት ብፅዕ አቡነ ስቪያቶስላቭ ሸቭቹክ ከግኑኝነቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ማድረጋቸው የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ ቅዱስ አባታችን ብፁዓን ጳጳሳቱን ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው ወቅታዊ ሁኔታ በማስደገፍ ያስደመጡት ንግግር በጥልቀት በማዳመጥ ምዕዳን መለገሳቸውንም ገልጦ፡ ቅዱስ አባታችን ስለ እውነት የሚናገሩ ግብረ ገባዊ ኃላፊነት የተካኑ መሆናቸው በኡክራይን መላ ሕዝብ የሚደነቁና ተሰሚነት ያላቸው ናቸው እንዳሉ ያመለክታል።

በኡክራይን የምትገኘው የግሪክ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለመላ የኡክራይን ሕዝብና አገር እርባና የምትቆምና የምታገለግል፡ ማንኛውን ዓይነት ወረራ የምትቃወም ስትሆን ከዚህ ጋር በማያያዝም በኡክራይን ሩሲያ የምታካሄደው 5 ሚሊዮን ሰዎች የሚመለከት ሁለት ሚሊዮን የሚገመቱ ዜጎች ቤትና ንብረታቸውን ጥለው በአገር ውስጥ ለመፈናቀል የሞትና የመቁሰል አደጋ ያስከተለው ጣልቃ ገብነት የምትቃወም መሆንዋ የገለጡት የቤተ ክርስቲያኒቱ ብፁዓን ጳጳሳት የበላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሸቭቹክ በማስከተል በዚህ የምህረት ዓመት በአገሪቱ ምኀአውርኝ ይቅር መባባል በሙላት ይኖር ዘንድ በዚህ አጋጣሚም ጥሪ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.