2016-03-05 16:27:00

የማሮናዊ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት


እ.ኤ.አ. የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. በሃገረ ኩባ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና በሞስኮና የመላ ሩሲያ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ኪሪል መካከል የተካሄደው ታሪካዊ ግኑኝነትና ፊርማቸው በማኖር ያጸደቁት የጋራ ሰነድና በተናጥል የሰጡት መግለጫ ዙሪያ በመጥቀስ የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መሪዎች ካላቸው አቢይ የጋራ ኃላፊነትና የተሰጣቸው የኃላፊነት ትርጉም ተገፋፍተው ያረጋገጡት መርሃ ግብር መሆኑ በማሮናዊ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያ ብፁዓ ጳጳሳት በፓሪያርክ ብፁዕ ካርዲናል በቻራ ቡትሮስ ራይ ፓትሪያርካዊ መንበር ባካሄዱት ወርሃዊ ጉባኤ እንዳሰመሩበት ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የማሮናዊ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት የሮማ ጳጳስ በማለት ገዛ እራሳቸውን የሚገልጡት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮን ይኽ ግኑኝነት እንዲረጋገጥ ለሰጡት አስተዋጽኦና ላሳዩት ትህትና ከልብ በማመስገን በመካከለኛው ምሥራቅ የተለያዩ ኃይማኖቶች ተገናኝተው ሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ለመገንባት በሚያደርጉት የጋራ ጥረት የሚያበረታታ ነው እንዳሉ የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት አክሎ፥ ለተፈናቃዮችና ስደተኞች የቤተ ክርስቲያን ፍቅርና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቅርበት ለመመስከር በፊሊፒንስ የማኒላ ሊቀ ጳጳሳት የተለያዩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሰብአዊ እርዳታ ማኅበራት ለሚያጠራንፍ የካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ልዊስ አንቶኒዮ ታግለ ሊባኖስ የስደተኞችና ተፈናቃዮች መጠለያ ሠፈር እየጎበኙ ባሉበት በዚህ አጋጣሚም የማሮናዊ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ባካሄዱት ወርሃዊ ስብሰባ ተገኝተው ባስደመጡት ንግግር፥ በመካከለኛው ምስራቅ እየተስፋፋ በመሄድ ላይ ያለው በሺዒዎችና ሱኒዎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት አሳሳቢ ነው ብለው፥ በክልሉ የሚታየው ግጭት ማኅበረ ክርስቲያንና ሕዝቦች ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ እያጋለጠ ያለው ውጥረት እልባት እንዲያገኝ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ሰላም ለማረጋገጥና የሰው ልጅ ሕይወት ጥበቃ የሕዝቦች የጋራ ኑሮ ዋስትና ለማሰጠት ይረባረብም ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.