2016-03-05 16:23:00

ቫቲካን፥ የሕንጸት መርሃ ግብር በጳጳሳዊ ቤተ ኑዛዜ


በየዓመቱ እንደሚከናወነው ሁሉ ይኸው ጳጳሳዊ ቤተ ኑዛዜ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው መራሔ መንግሥት ተብሎ በሚጠራው ሕንፃ ባለው የጉባኤ አዳራሽ በሚሥጢረ ንስኃ ዙሪያ እንዲመክር ያሰናዳው እ.ኤ.አ. የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. የተጀመረው የሕንጸት መርሐ ግብር እ.ኤ.አ. መጋቢት 4 ቀን ተጋባእያኑ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ ጋር ተገናኝተው መሪ ቃል በመቀበል መጠናቀቁ የቫቲካ ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፋቢዮ ኮላግራንደ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፡ ከ 170 ኣገሮች የተወጣጡ 450 ተጋባእያንን በማሳተፍ ስለ ተካሄደው 27ኛው የውስጠ ሕንጸት መርሃ ግብር ጉዳይ አስመልክተው የጳጳሳዊ ቤተ ኑዛዜ አሥተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ክርዝይስቶፍ ንይካል ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ አበ ነፍስ ወይንም አናዣዥ ካህን ተናዛዡ ምእመን በምሥጢረ ንስኃ አማካኝነት የእግዚአብሔር ምኅረት እንዲነካ ማድረግ ይጠበቅበታል። ጳጳሳዊ ቤተ ኑዛዜ፡ ካህናት በተለይ ደግሞ አዳዲስ ካህናት የምስጢረ ንስኃ ጥልቅ ቲዮሎጊያዊ መጽሓፍ ቅዱሳዊና ትውፊታዊ ሐዋርያዊ ግብረ ኖላዊና ሕጋዊ ትርጉሙን ጠንቅቀው እንዲገነዘቡ መደገፍ ይኖርባቸዋል። ካህን የእግዚአብሔር ምኅረት የሚኖር መሆን ይጠበቅበታል፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደሚሉትም በሚሥጢረ ንስኃ አማካኝነት ምእመን ያንን ውስጣዊ ሰላም የሚጸግወው የእግዚአብሔር ምኅረት እንዲነካ መታገዝ አለበት። ከዚህ አንጻር ሲታይ አናዛዡ ካኅን የእግዚአብሔር ምኅረት በሕይወቱ የሚነካ መሆን አለበት ብለዋል።

ሁሉም ካህን የማናዘዝ ክህነታዊ ተልእኮና ሥልጣን አለው ይኸንን ኃላፊነትም የሚቀበለው በቤተ ክርስቲያን አማካኝነት ከኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እግዚአብሔር አባትነቱ መኃሪነቱ የሚገልጥበት ምሥጢር ነው። ሁሉም ካህን የነፍሰ አባት ይሆናል ማለት አይደለም። አበ ነፍስ በአጋጣሚ የሚኮን አለ መሆኑ ለይቶ ያሚያብራራ አገላለጥም ነው፡ የንስኃ ምሥጢር ከክርስቶ ጋር የሚያገናኝ ልዩ ሥፍራ ነው፡ የእግዚአብሔር ምኅረት ከማንኛውም ዓይነት ኃጢአት የላቀ ነው፡ ህያውና ሕይወት ከሆነው ክርስቶስ ጋር የሚያገናኝ ጸጋ ነው፡ በመሆኑም እምነት ይጠይቃል። ጥልቅ እምነት ያስፈልጋል፡ አናዥ ካኅን ያለበት ኃላፊነት ቀላል አለ መሆኑ ከዚሁ ለመገንዘብ እንችላለን ብለዋል።

ለሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አቢይ ተግዳሮት ምእመናን የእግዚአብሔር ፍቅር ታላቅነቱን ዳግም እንዲገነዘቡ ማድረግ የሚል ነው፡ በዚህ እግዚአብሔር እምብዛም ይሁን በትንሹ አያስፈልገኝም የሚል ባህልና የተዛማችነት ባህል፡ ሰው በገዛ እራስ ዋቢነት የመኖር አዝማሚያ የሚያነቃቃ ባህል ግለኝነት እራስ ወዳድነት ስግብግብነት እየተስፋፋ ባለበት ዓለም የሰው ልጅ የሚሥጢረ ንስኃ የላቀው ክብር ዳግም እዲያስተውል ማድረግ ቀላል አይደለም። ስለዚህ ከዚህ አኳያ የአናዛዥ ካህን ያለው አስፈላጊነትና ሊኖረው የሚገባው ቅድመ ዝግጅት ቀላል አለመሆኑ ለመረዳቱ አያዳግትም ብለዋል።

የዘንድሮው ዓውደ ሕንጸ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት ሁሉ ለየት የሚያደርገውም የተገባው የምኅረት ዓመት ነው፡ የሕንጸቱ ማእከል የንስኃ ምስጢር ነው፡ ንስኃ የዕርቅ ምስጢር ነው፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የምኅረት ገጽ በሚል ርእስ ሥር የምኅረት ዓመት ለማወጅ ባወጡት ሰነድ ላይ እዳሰመሩበት ምኅረት ሁሉን ነገር የሚፈርድ ለቤተ ክርስቲያን ለአያንዳንዱ ሰው ፍርድ ነው። የንስኃ ሚሥጢር የክርስቶስ ቀጣይ ኅላዌ መዚህ ምድር የሚያረጋጥ ነው። ይኽ ቤተ ክርስቲያን የምታውጀው ምኅረት በንስኃ ከእግዚአብሔ ጋር ከባለንጀራ ጋር ከገዛ እራስ ጋር የሚያስታርቀው ቅዱስ ሚሥጢር ያንን ጥንታዊው እባብ ለለቀቀው መርዝ ፍቱን መድሂት ነው፡ በሚሥጢረ ንስኃ አማካኝነት የክርስቶስ ድል አድራጊነትን እንመሰክራለን ሲሉ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.