2016-03-02 16:18:00

የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት፥ ወጣቱ ትውልድ ተስፋውን እንዳያጨልም


አለ መረጋት አሸባሪነት የክርስቲያን ስደት ጸአት ምግባረ ብልሽት ሙስና የመልካም መስተዳዳር መጓደል ሕገ መንግሥት ሥልጣል በሚለውና ሥልጣን ለማራዘም በሚራወጠው የፖለቲካ አካልና በሚከተለው ፖሊቲካው አመለካከት ሥር ማጠማዘዝና መቆጣጠር ከሚከተለው ጸረ ሕገ መንግሥታዊ ሂደት የተሰኙት አንገብጋቢ ነጥቦች የለየ የምዕራብ አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳስት ምክር ቤት በጋና ርእሰ ከተማ አክራ የተካሄደው ሁለተኛው ጠቅላይ ጉባኤ ጉባኤ መጠናቀቁ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የምዕራብ አፍሪቃ ችግሮች

ብፁዓን ጳጳሳቱ ባካሄዱት ጉባኤ የምዕራብ አፍሪቃ ችግሮችን በመለየት በዚያ ክልል እተጋባ ያለው አሸባሪነትና የሽበራ ጥቃት ኒጀሪያን ማሊን ቡርኪናፋሶ ካሜሩንና ጫድን ያጠቃውን ሁሉ በመጥቀስ ይኽ የሽበራው ጥቃት ጸረ ክርስትናና ጸረ ክርስቲያን ያለመ የሃይማኖት ነጻነት የሚጥስ መግሥት ከሃይማኖ ነጻ የሚለው ሕገ መግሥታዊ ሥርዓት የሚቃወም ከመሆኑ ባሻገር በእያንዳንዱ ሰው ልጅ በኑባሬ ያለው የነጻነት አስተንፍሶ የሚቀናቀን ነው፡ ይኽ ችግር የክልሉ ወጣት ትውልድ አገሩና አካባቢውን ቤተሰቡንም ጥሎ ወዳልተረጋገጠ ሕይወት ለሞት በሚያጋልጠው ጎዳና ሁሉ እንዲሰደድ እያስገደደው መሆኑ ጉባኤው ባወጣው መግለጫ በማብራራት የመልካም መስተዳዳር መጓደል ሙስና ምግባረ ብልሽት ማኅበራዊ ኢፍትሓዊነትና እነዚህ አሉታዊ ተግባሮች የመሳሰሉት ሁሉ የተወሳሰበ ዘርፈ ብዙ ችግር እያጋባ መሆኑም እንዳስገነዘቡ ፊደስ የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።

ለቤተሰብ ለተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት ሥጋት ለስራ አጥነትና ለድኽነት ችግር የሚያጋልጥ ሁሉ በምዕራብ አፍሪቃ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለምትወጥነው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተግዳሮት መሆኑና በተያያዥ መልኩም እየተስፋፋ ያለው የሞት ባህል በሕይወት ላይ የሚፈጸም ሽበራዊ ጥቃት ብዝበዛ በንግዱ ዓለም ብዝበዛ በተፈጥሮ ሃብት ሥራ አጥነትና ክልሎች አለ ሕዝብ እንዲቀሩ የሚያስገድዱ ጸረ ሰብአውያን ድርጊቶች ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተጋርጦ መሆኑ ብፁዓን ጳጳሳቱ እንዳሰመሩበት ፊደስ የዜና አገልግሎት ይፋ አደረገ።

በእምነት መጽናት

ብፁዓን ጳጳሳቱ ባወጡት የፍጻሜ ሰነድ አማንያን በዚህ በክልሉ ተከስቶ ባለው ተጋርጦ ሳይደናገጡ በእምነት ጸንቶ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያግዘው ኃይል ከእምነት በማግኘት የሰላም የእኩልነት መሣሪያ ሆኖ መልካም መስተዳዳ እኩልነት የአገር ኃብት ለሁሉም የተሰኙትን እሴቶች እንዲያነቃቃና ወጣት ትውልድ ተስፋ ሳይቆርጥ ጥሪው በአገሩ ውስጥ ለማረገጥ እንደሚችል ታምኖ በእምነት እንዲጸናና በዚሁ ጎዳናም እንዲደገፍ እደራ እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።   








All the contents on this site are copyrighted ©.