በኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት ዘ አኽሱም ወ እጨገ ተክለሃይማኖት ኦርቶዶስክ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ለመጀመርያ ግዜ በሮም የአራት ቀናት ጐብኝት አድርገዋል ።ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ በሮም ቆይታቸው በቅዱስ ጰጥሮስ ካተድራል የሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ መቃብር ፡ በቅድስት መንበር የክርስትያኖች አንድነት ጳጳሳዊ ምክር ቤት እና ቫቲካን እምብርት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ጳጳሳዊ ኮለጅ ጐብኝተዋል።
ኮለጁ በጐበኙበት ግዜ የኮለጁ ካህናት የምስራቃውያን አብያተ ክርስትያናት ማሕበር የበላይ ሐላፊ ብጹዕ ካርዲናል ለኦናርዶ ሳንድሪ በፍረንሳይ እና ቫቲካን የኢትዮጵያ መንግስት አምባሳደር ነጋ ጸጋዪ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንጎዶች ደማቅ አቀባበል አድርግውላቸዋል ።
እንዲሁም ሮም በሚገኘው ኡርባንያን ጳጳሳዊ ኮለጅ ውስጥ በሚገኘው ቤተ ጸሎት በሮም እና አከባቢ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማሕበረ ሰብ አባላት በተገኙበት ሥርዓተ ቅዳሴ አሳርገዋል ።
ዛሬ ረፋድ ላይ በቫቲካን ሐዋርያዊ አዳራሽ ውስጥ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል ።
በሮማዊት ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እና በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን መካከል የቆየ መልካም ግንኙነት እንዳለ በቫቲካን የተሰጠ መግለጫ ጠቁሞ የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርትያን ፓትርያሪክ ብጹዕ ወ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እንደ ጎርዮስ አቆጣጠር በ1993 ቫቲካን በይፋ መገብኘታቸው እና በወቅቱ ከነበሩ ነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መገናኘታቸው ቀጥሎም ፡ በ2009 ይሄም ጎርዮሳዊ የቀን ቀመር ከቀድሞ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቱስ 16ኛ ጋር መገናኘታቸው ጠቅሶ በሮማዊት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እና በኢዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን መካከል መልካም ግንኙነት እንዳለ ዘግበዋል።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ወርሀ ነሐሰ 2012 ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በየካቲት 28 2013 የኢትዮጵያ ስድስተኛ ፓትርያሪክ በመሆን በመንበረ ጻባዖት ቅድስት ሥላሴ ካተድራል አዲስ አበባ ላይ ሢመተ ፕትርክናቸው መፈጸሙ የሚታወስ ነው ።
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አማርኛ ትግርኛ እንግልዝኛ ግሪክኛ ኤብራይስጥኛ እና አረብኛ አቀላጥፎው እንደሚናገሩ ይታወቃል ። ኢትዮጵያዊ ፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በጥቅምት ወር 2009 በቫቲካን ውስጥ ይካሄድ ለነበረው የአፍሪቃ ብጹዓን ጳጳሳት ሁለተኛ ልዩ ሲኖዶስ የአፍሪቃ አህጉር ወቅታዊ ሁኔታ እና የአፍሪቃ ህዝቦች ለሚገጥምዋቸው ፍልምያዎች የመቋቋም ክህሎት ትኩረት ሰጥተው ንግግር እንድያደርጉ የቀድሞ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቱስ ፓትርያሪኩን መጋበዛቸው በቫቲካን የተሰጠ መግለጫ አስገንዝበዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©. |