2016-02-19 15:54:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የመክሲኮ ሐዋርያዊ ጉብኝት መጠናቀቅ


ቅዱስ ኣአባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. መክሲኮ ከተማ ከሚገኘው በኒቶ ኹዋረዝ ዓለም አቀፍ ያየር ማረፊያ በመክሲኮ ሰዓት አቆጣጠር ልክ 7 ሰዓት ከ 15 ደቂቃ ተነስተው ሞረሊያ በሚገኘው ጀነራል ፍራንሲስኮ ሙጂካ አየር ማረፊያ እንደደረሱ በሞረሊያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አልበርቶ ሱዋረዝ ኢንዳ በክልሉ የመንግስት አካላትና ባለ ሥልጣናት አቀባበርል ተደርጎላቸዋል።

እንደ መርሃ ግብሩ መሠረትም በሞራሊያ ወደ ሚገኘው ቨኑስቲኣኖ ካራንዛ የስፖርት ሜዳ ተዛውረው እዛው ለመክሲኮ ውሉደ ክህነት የውፉይ ሕይወት አባላትና የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ያሳተፈ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው፦ እንዴት እንደምትጸልይ ንገረኝና እንዴት እንደምትኖር እነግርሃለሁ። እንዴት እንደምትኖር ንገረኝና እንዴት እንደምትጸልይ እነግርሃለሁ የሚል አባባል ጠቅሰው እንዴት እንደሚጸልይ ስንመሰክር ሕያው እግዚአብሔር ጋር እገናኛን፣ እንዴት እንደምኖር ስመሰክርም በምጸልየው እግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት እንመሰክራለን፣ ስለዚህ ሕይወታችን ስለ ጸሎት የሚናገርና ጸሎት ስለ ሕይወታችን የሚናገር ነው። መጸለይና ማዳመጥ መማር ያስፈልጋል፣ የጸሎት ትምህርት ቤት የሕይወት ትምህርት ቤት ነው፣ የሕይወት ትምህርት ቤት ደግሞም ጸሎት ትምህርት ቤት ነው። የውፉይ ሕይወት ትርጉም እርሱ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ለተከታዩ ጢሞቲዎስ እምነትን እንዲኖርው ሲያስተምረውና ሲመክረው እናትህና አያትህን አስታውስ ይለዋል፣ የዘርአ ክህነት ተማሪም እንዴትም መጸለይ እንደሚገባው ከቤተሰብ የተሰጠው የአብነት ሕንጸት መሠረት መሆኑ ማስተዋል ይጠበቅበታል፣ በጸሎት መንፈስ በማደግ መጸለይ መማር፣ ሕይወታችን ዘወትር የጸሎት ትምህርት ቤት ነው።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ ልጅ መሆን ትርጉሙን በዕለታዊ ሕይወቱ አስተምሮናል፣ በእርሱ ሕይወት አብን እንድንነካ ከአብ ጋራ እንድንገናኝ አድርጎናል፣ እርሱ የሚኖረው አባቴ ሆይ የሚል ሙሉ ሕይወት አባታችን ሆይ ብሎ አስተምሮናል፣ እየጸለይክ መኖርና እየኖርክ መጸለይን አስተማረን።

ቅዱስ ጳውሎስ ባልሰብክ ወዮልኝ ይላል፣ እኛ ጳጳሳት ካህናት የዘርአ ክህነት ተማሪዎች የውፉይ ሕይወት አባላት በጠቅላላ የተቀበልነው የብሥራት ቃል ካላካፈልን ወዮልን። ጸላይ ሕይወት ማለት እንደ የእግዚአብሔር ፍቃድ መኖርና በቃልና በሕይወት አባታችን ሆይ የሚል ሕይወት በመኖር መመስከር ማለት ነው።

ችግር እክል ሲያጋጥም ተስፋ ቆርጦ እጅ ሰጥቶ መኖር ምንም ማድረግ እልችልም የሚል ሕይወት ሸባ ያደርገናል፣ ሕይወታችን ጸሎት፣ ጸሎት ሕይወታችን ይሁን አደራ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ አጠናቀው በሰበካው ጳጳሳዊ ሕንፃ ምስ ተቋድሰው እንዳበቁም የሞረሊያ ካቴድራል ጎብኝተው፣ ኾሰ ማሪያ ሞረሎስ ይ ፓቮን የእግር ኳስ ሜዳ ከአገሪቱ ወጣቶች ጋር ለመገናኘት በጳጳሳዊ መኪና ተጉዘው ወጣቶች የአገራቸውን ባህል የሚያንጸባርቅ መንፈሳዊ መዝሙሮችን በማቅረብ ላደረጉላቸው የእንኳን ደህና መጡ መልእክት አመስግነው አንዳንድ ወጣቶች የአንድ አገርና ኅብረተሰብ ሞት የሚያደርገው አመጽ የአንደንዛዥ ዕጸዋት ዝውውር የወንጀል ቡድኖች የሚያስፋፉት ጸረ ሰብአዊ ተግባር ምግባረ ብልሽት የሥራ እጥነት ብሎም ሰብአዊነት ልክ የሌለው የሥነ ጾታዊ ትምህርት በተያያዘ መልኩም ሰብአውያን ግኑኝነቶች የሚያኮላሹ ተግባሮች ማእከል ያደረገ እዛው ከተገኙት ወጣቶች ያቀረቡላቸው ጥያቄ መሠረት በማድርግ በለገሱት ምዕዳን ተስፋችሁ ክርስቶስ ነው። ለብ ካለ ሕይወት ከፍርሃት ካስመሳይነት ላድር ባይ መሰረት ከሚያደርግ ሕይወት ነጻ የሚያወጣን ተስፋችን የሆነው ክርስቶስ ነው። ወደ ኋላ የሚጎትተን ሁሉ ለማሸነፍ ከፈለግን ወደ የከተሞቻችንና የሕልውና ጥጋ ጥግ ክልል እናቅና ከክርስቶስ ጋር እንገናኝ

ወጣት የአገር ሃብት ነው። ይኽ ሃብት ብዙውን ጊዜ በተፈጥሮ ሃብት ላይ እንደሚደረገው ለብዝበዛና ለግል ሃብት ማካበቻ መሣሪያ ሊሆን ይችላል፣ ወጣቱ ሃብት የመሆን ጸጋውን ለተገባ ነገር ማዋል ያስፈልጋል፣ ሃብት መሆናችሁ ክብር ካልሰጣችሁት ወጣትነት ለሚነጥቅ ሰብአዊ ልክነት ለሌለው ክብር ሰራዥ ለሆነው አመለካከት እጅ ለመስጠት ትገደዳላችሁ፣ ወጣትነታችሁ ሃብት ነውና አክብሩ ተስፋ መሆናችሁ እወቁ።

ድል ማድረግ ወደ ላይ መመንጠቅ ሳይሆን እውነተኛው ድል በወደቅክበት አለ መቅረት ነው ክርስቶስ ከወደቃችሁበት ያነሳችሁ ዘንድ ፍቀዱለት፣ እርሱ ወድቀን እንቀር ዘንድ አይፈቅድም፣ በወደቅንበት አንኑር አደራ ያሉት ቅዱስ አባታችን ወጣት የቤተ መቅደስ ገንቢና የአገርን የቤተሰብ መሠረት ነው በማለት፣ እንደ እባብ ብልሆች እንደ እርግብ የዋሆች፣ ቅዱስ ቤት እንጂ የሐሴት ቤት አትገንቡ፣ ያ ቀዳሚው የተካፍሎ መኖር የፍቅርና የመተሳሰብ ትምህርት ቤት የሆነውን ቤተሰብ የምትገነቡ ሁኑ ያሉት ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. የዕለተ ማክሰኞ መርሃ ግብራቸውን አጠናቀዋል።

ቅዱስ አባታችን የዕለተ ረቡዕ እ.ኤ.አ. የካቲት 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በመክሲኮ ሰዓት አቆጣጠር መክሲኮ ከተማ ከሚገኘው ከቅዱስት መንበር ሐዋርያዊ ልእክ ሕንጻ ከጠዋቱ ሰባት ሰዓት ተኩል ተሰናብተው ከበኒቶ ኹዋረዝ ዓለም አቀፍ ያየር ማረፊያ ተነስተው ሲዳድ ኺዋረዝ በሚገኘው አብራሃም ጎንዛለስ ያየር ማረፊያ ልክ ከጠዋቱ 10 ሰዓት እንደደረሱም በሰበካው ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኾሰ ጓዳሉፐ ቶረስ ካምፖስ የክልሉ የመንግሥት ተወካዮችና የምክር ቤት ተጠሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸው በከተማይቱ ወደ ሚገኘው ወህኒ ቤት በመኪና ተጉዘው፦ በወህኒ ቤቱ የጸሎት ቤት መንፈሳዊ መሪና በወህኒ ቤቱ የመስተዳድር አባላትና ዋና አስተዳዳሪ አቀባበል ተደርጎላቸው ከእስረኞች ጋር ተገናኝተዋል። እዛው ምዕዳን ሲለግሱ፦

የእግዚአብሔር ምሕረት ለሁሉም ነው

ብዙውን ጊዜ ጸጥታና ደህንነት በሚገባ ለማስከበርና ዋስትና ለመስጠት እየተባለ የመቅጫ ሕጎችን ማሳየልና የውህኒ ቤቶች ማስፋፋት ምርጫ ሲተገበር እናያለን፣ ጸጥታና ደህንነት ዋስትና የለመስጠት ሕግ ለመጣስ ወንጀል ለመፈጸም የሚዳርገው መዋቅራዊ ጉዳይ በሚገባ ገጥሞ መፍትሔ እንዲያገኝ ማድረግና የሕግ መጣስ ተግባር ከወዲሁ ለመከላከል የሚበጅ ባህልና አሠራር ማስፋፋት እንጂ የመቅጫ ሕግ ማሳየል መፍትሔ አይሆንም። ሁሉም ምህረት ያስፈልገዋል፣ ምህረት የማያስፈልገው ማንም ሰው የለም፣ ወህኒ ቤት ሌላውን ማግለልና እንደ ጥራጊ የማሰቡ ሌላውን ለገዛ እራስ የመተው ባህል መግለጫና ምልከት ነው። በወህኒ ቤት መተማመን አያስፈልግም፣ ሕግ ያስፈልጋል ነገር ግን መለኰታዊ ምህረት ከሁሉም በላይ ነው። የተገባው የምህረት ቅዱስ ዓመት ማናችንም ላለፈው ታሪክ ተገዥ ሳንሆን ካለፈው ታሪክ እንድንማር ያነቃቃናል ይኽ ደግሞ እንድንለወጥ ያደርገናል። የተሰጠንን ነጻነት በሚገባ መኖር እንድንችል ይመራናል ብለዋል።

ቅዱስ አባትችን ከወህኒ ቤቱ ተሰናብተው እንዳበቁም  በዚያኑ ዕለት በመክሲኮ ሰዓት አቆጣጠር ልክ እኩለ ቀን ከሠራተኛ ማኅበራት ጋር ተገናኝተው የመክሲኮ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሠራተኛና ሠራተኞች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልው ተንከባካቢ ድርገት ሊቀ መንበር የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ካስደመጡ በኋላ በመቀጠል ሥራ ያለው ክብር ካብራሩ በኋላ፣ ሥራ ብዝበዛ ማእከል ካደረገ የሰው ልጅ ክብር የሚጻረር ይሆናል፣ እንደ ቀን በእግዚአብሔር እንጠየቅበታል። ተቀባይነት ያለው የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ለማይጥስ ሥራ ነው የተጠራነው፣ የሥራ አጥነት ችግር ድኽነት የመሳሰሉትን የሰው ልጆ ለተለያየ ዘርፈ ብዙ ችግር የሚያጋልጠው ተግባር ለመቅረፍ ብቃት ያለው የሥራ ፖለቲካ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ሥራ የሰው ልጅ ቤተሰባዊ ሁነት ላደጋ የሚያጋልጥ ሳይሆን ቤተሰብ የሚደግፍ፣ የእግዚአብሔር ልጅ የመሆን ጥሪ የሚያከብር መሆን ይገባዋል ብለው ከሠራተኞች ጋር ያካሄዱት ግኑኝነት አጠናቀው ከተሰናበቱም በኋላ ልክ 4 ሰዓት በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር መክሲኮ ከተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ጋር በሚያዋስናት በሲዳድ ኹዋረዝ ከተማ በላቲን ሥርዓት የዓቢይ ፆም ቀዳሜ ዕለተ ረቡዕ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል፣ በዚያ በሚያዋስነት ክልል በተተከለው አቢይ መስቀል ፊት ጸሎት አቅርበዋል፣ በዚያ ክልል የሚታየው ስደትና መከራ፣ በተለይ ደግሞ ከድኽነትና በተለያየ ችግር ምክንያት ከመክሲኮም ይሁን ከሌሎች አገሮች ወደ ተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ለመሰደድ የሚታየው ጸዓት በስደት ጉዞ የሚያጋጥም ችግር ሁሉ በማሰብ አገናኝ ድልድይ እንጂ ለያይ ግንብ የችግር መፍሔ አይሆንም እንዳውም የግንብ አጠር ችግሮችን የሚያከር ተግባር ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር የሚያግድ ምንም ዓይነት ግንብ እንደምያኖር የተረጋገጠ ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን የመክሲኮ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ለማጠናቀቅ በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከምሽቱ 7 ሰዓት ተኩል በተባበሩት የመክሲኮ መንግሥታት ርእሰ ብሔር ኤንሪከ ፐኛ ኔየቶና ክብርት ባለ ቤታቸው በተገኙበት የመክሲኮና የአገረ ቫቲካን ብሔራዊ መዝሙሮች በተደመጠበት ሥነ ሥርዓ አሸኛኘት ተድርጎላቸው እ.ኤ.አ. የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጠር 15 ሰዓት ከሩብ ሃገረ ቫቲካን ገብተዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.