2016-02-16 08:56:00

ሆስፒታሉ በዓመት እስከ 225,000 ህሙማን ሕፃናትን ተቀብሎ እንደ ምያም ታወቀ


በትላንትናው እለትም ማለትም አንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በየካቲት 14.2016 ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በሜክስኮ ከተማ የምገኘውን የሕጻናት ሆስፒታል መጎብኘታቸው ተገለጸ።

ይህ ከተለያዩ የሜክስኮ አከባቢዎች የምመጡትን በተለይም የድኽ ቤተሰብ ልጆችን ተቀብሎ አስፈላጊውን አገልግሎት የምሰጠው ሆስፒታል በዓመት እስከ ሁለት መቶ ሃያ አምስት ሺ (225,000) ህሙማን ሕፃናትን ተቀብሎ እንደ ምያክም በጉብኝቱ ወቅት ለመረዳት ተችሉዋል።

የቅዱስ አባታችን ግብኝት በሆስፒታሉ ለምሠሩ ሠራተኞች ትልቅ የሞራል ማነቃቅያ የሆናቸው እንደነበረ የሆስፒታሉ የበላይ አለቃ አስታውቀው፣ በተለይም በዝያ ለምገኙ ህሙማን ሕፃናት እና ቤተሰቦቻቸው መጽናኛና መንፈሳዊ በረከትን እንደምያጎናጽፍ በመታመኑ ጉብኝቱ በጣም አስደሳች እና አርኪ ነበረ በማልት ገልጸዋል።

ቅዱስ አባታችን ሆስፒታሉን መጎብኘት በጀመሩበት ወቅት በሰላሳ ስድስት ሕፃናት ታጅበው የነበረ ስሆን በተጨማሪም በሆስፒታሉ ውስጥም በመዘዋወር ሃያ አምስት በካንሰር ህመም የምሰቃዩ ሕፃናት በመጎብኘት ልባዊ ጸሎትን በማድርግና የነዝህን ህሙማን ሕጻናት ቤተሰቦች ታልቅ ትግስትን በማድነቅና በእምነታቸው ጸንተው ተስፋ ሳይቆርጡ በጸሎት የታገዘ ሕይወት እንዲኖራቸው አሳስበው ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.