2016-02-16 09:20:00

ቅ.አ. በሴቶች ላይ የምፈጽሙትን አስከፊ እና አሰቃቂ ደርጊት አውግዘዋል።


እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በየካቲት 14.2016 ቅዱስ አባታች ፍራንቸስኮ በድኽነትና ከአደንዛዥ እፅ ስርጭት ጋር የተያያዘ ብጥብጥ እና ህውከት ወደ አልተለያት በሜክስኮ የምትገኘውን ኤካትፔክ ከተማ መጎብኘታቸው እና በዝያውም በእፅ አዛዋዋሪዎች የተገደሉትን ዘጎች ለማስታወስ መገኘታቸው ታወቀ።

ቅዱስነታቸው በዝህች በብጥበጥና በስርዓት አልበኝነት የተጎሳቆለችውን ከተማ መጎብኘታቸው በዝያ የምገኙትን በአብዛኛው በድኸነት ለተጎሳቆሉ የምህበረሰብ ከፍሎች ትልቅ ተስፋን የጫረባቸው እንድሆነ ለማዎቅ ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው ርዕሰ ሊቃነ ፓፓስ ሆነው ከተመረጡ ቡኋል ለድኾችና በጉስቁልና የምኖሩ የምሕበረሰብ ክፍሎች ተገቢውን እንክብካቤ እድደረግላቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች ለዓለም ሕዝብ የተማጽኖ ንግግር በማድረጋቸውና ተጨባጭ የለውጥ እርምጃ እንድወሰድ የበኩላቸውን ጥረት በማድረጋቸው የብዙኻኑን በድኽነት የምኖረውን የማሕበረሰብ ክፍል ድምጽ ለአልም እያስሙ መሆናቸው ልዩ ያደርጋቸዋል።

በትላንትናው እለትም በዝችሁ ከተማ ቅዱስነታቸው ባሳረጉት ስራተ ቅዳሴ ላይ ከ300,000 በላይ ምዕመናን የተገኙ ስሆን በስራዓተ ቅዳሴያቸው ላይ “የሞት መልዕክተኞች” ያሉዋቸውን የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪውችን በተለይም በሴቶች ላይ የምፈጽሙትን አስከፊ እና አሰቃቂ ደርጊት አውግዘዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው “በጎርጎሮሳዊያን የስርዓተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር፣ የአርባ ቀን ፆም ባለፈው ረቡዕ መጀመሩን አስታውሰው በዝህ በሕማማት ወቅት ቤተ ክርስትያን ከፈተኛ መንፈስዊ ዝግጅት እንድናደርግ ስለምትጋብዘን፣ ሓጥያት በምንሰራበት ወቅት ያጣነውን በእግዚአብሔር የምገኘውን ደስታና ፀጋ መልሰን ይምናገኝበት ጊዜ መሆኑን በመረዳት አግባብ ያለው መንፈስዊ ዝግጅት ልናደርግ ይገባል” በለዋል።

የሕማማት ወቅት መንፈስዊ ለውጥ የማምጫ ወቅት ነው በማለት ቃለ ወንጌላቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባታችን፣ በየቀኑ ሕይወታችንን የምፈታተኑና ከእግዚአብሔር መንገድ በመራቅ እርስ በእርሳችን እንድንጋጭ እና እንድንከፋፈል የምያደርጉንን የሰይጣን ፈተናዎችን ማለፍ የምያስችለንን ፀጋ የምናካብትበት ወቅት ልሆን ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም “የሕማማት ወቅት ውስጣዊ ስሜቶቻችንን በመመርመር በያለንበት ቦታ የምፈጸሙትን ኢፍታዊ ድርጊቶችን የምንቃወምበት ወቅትና ማንኛውንም ከእግዚአብሔር እቅድ ውጭ የሆኑትን ድርጊቶች የምናውግዝበት ወቅት መሆን እንዳለበት” አሳስበዋል።

በእለቱ የወንጌል ቃል ማለትም በሉቃስ ወንጌል 4፣1-4 እንደተገለጸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ጊዜ በስይጣን መፈተኑን የምያብራራ መሆኑን ገልጸው እንዝህ ፈተናዎችም በእኛ በክርስታያኖች ሕይወት ውስጥም የምጸባርቁና እኛን ከእግዚአብሔር ለማለያየትና ለተጠራንበት ዓላም ታማኝ እንዳንሆን የምያደርጉን አደገኛ እንቅፋቶች ናቸው በለዋል።

ለሁልም የማህበረሰብ ክፍል መሆን የምገባውን ሀብት ለግል ጥቅም ብቻ ማካባት ከፍተኛ የሆነ አደጋ በዓለማችን ላይ እየደቀነ የመጣና በክርስትያኖች ሕይወት ወስጥ የምታይና ትልቅ ፈተና እየደቀነ መሆኑን ገልጽው የሌላውን እንጀራ ንጥቆ እንድራቡና እንድጠሙ በተጨማሪም ብዙሃኑ መራር ሕይወት  እንዲኖር ማድርገ በመሆኑ ከዝህ መሰሉ ድርጊት ክርስትያኖች ሁሉ መቆጠብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ትምክተኝነት ሌላኛው የክርስትያን ፈተና ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን ይህም ሌሎችን ይቅር እንዳንል ልባችን በማደንደን ለራሳችን ዝና ብቻ እንድኖኖር እና  በማን አላብኝነት ሌሎችን በመጨቆን የምቃወመን ከተገኘ ድግሞ ከመንገዳችን እንድናስወግደው ክፉ መንፈስን የምፈጥር በመሆኑ በዝህ በሕማማት ወቅት ትምክተኛነትን ልናስወግድ እንደ ምገባ አሳስበዋል።

በሦስተኛ ደረጃ ላይ የምገኘው የክርስታያኖችን ፈተና “ኩራት ነው” ያሉት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ይህ ደግሞ እራሳችንን ከምገባን በላይ ከፍ በማድረግ ከሰዎች ሁሉ በላይ እንደሆንን እንድስማን ከማድርጉም በላይ እንድንመጻደቅ የምገፋፋን በመሆኑ የዝህ ዓይነት ፈተና በሕይወታችን የምጸባረቅ ከሆነ በእግዚአብሔር እዳታ ላናስወግድ እንድምገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን እንዳሳሰቡት እንዝህ ከላይ የተጠቀሱት ሦስቱን ፈተናዎች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እደተወጣቸው ሁሉ፣ እኛም ክርስትያኖች በየቀኑ የምያጋጥሙን ፈተናዎች በሆናቸውና ሕይወታችንን በማበላሸት ከወንጌል አስተምሮ ውጭ የምያደርጉ በመሆናቸው ይህንን የጥፋት ጎዳና ትተን በትክክለኛው የእግዚአብሔር መንገድ ላይ መጓዝ የምያስችለንን ፀጋ የምለምነበትና ለሰራናቸው ሓጥያቶች ይቅርታ የምንጠይቅበት ቅዱስ ወቅት ልሆን ይገባዋል በማለት ስብከተ ወንጌላቸውን አጠናቅቀዋል።

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.