2016-02-15 16:18:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ የእግዚአብሔር ርህራሄ ብቻ ነው ልብን የሚማርክ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በመክሲኮ ርእሰ ከተማ በሚገኘው ፍልሰታ ለማርያም ካቴድራል የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጋር እ.ኤ.አ. ቅዳሜ የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከሰዓት በኋላ ስድስት ሰዓት ተኵል ተገናኝተው ሥልጣናዊ ምዕዳን መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብሬላ ቸራዞ ገለጡ።

የመክሲኮ ብፁዓን ጳጳሳት ስለ ወጣቶች የአገሪቱ ቀደምት ተወላጆች ማለትም ስለ አገሬዎችና ስለ ስደተኞችን እንዲቆረቆሩ ቅዱስ አባታችን በአደራ በማለት፣ ሁሉን የሚያስተባበር ጸረ የአደንዛዥ ዕጸዋት አንቀሳቃሽ የወንጀል ቡድኖች ላይ ያተኮረ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እንዲያረማምዱን በማሳሰብ፣ ቅዱስ አባታችን ወደ ካቴድራሉ ለመድረስ ባደረጉት የ 800  ሜትር ርቀት ጉዞ ሕዝብ የሻማ ብርኃን ከፍ በማድረግ በሞቀ ጭብጨባና በመዝሙር እንደሸኛቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አክለው፦ ወደ መንበረ ታቦት ቀረብ ብለው ተንበርክከው ጸሎት አሳርገው እንዳበቁም፦

የሰው ልጅ ልብ የሚማርከው ብቸኛው ኃይል የእግዚአብሔር ፍቅር ነው

ቅዱስ አባታችን በቅድስት ድንግል ማሪያም ዘጓዳሉፐ ተክለ ሰብነት ላይ በማተኮር ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ልብ ለእናንተ የሚፈሰው ፍቅር እርሷ ብትገልጥላችሁ እንዴት ደስ ባለኝ። ቅድስተ ማርያም ዘጓዳሉፐ ልብን የሚማርክ የእግዚአብሔር ፍቅር መሆኑ ታረጋግጥልናለች፣ አግርሞት የሚያሳድረው የሚማርከው ድል የሚነሳው የተዘጋ በር የሚከፍተው የጭቆና ሰንሰለት የሚፈታው የመሣሪያ ብርታት ወይንም የሕግ ክረት አይደለም፣ ያደካማ የሚመስለው ጎንበስ ብሎ የወደቀውን የሚያነሳው መለኮታዊ ፍቅር ነው፣ ያ መለኰታዊ ፍቅር ለመቋቋም የማይቻል ያ መልካምነትና የማይታበለው የምህረት ቃል ኪዳን ነው።

የክርስትና ማሕንጸት የሚያስተናግድ የሚያስታርቅና የሚያዋህድ ነው፣ በሕዝባችህ ጥልቅ መንፈስ ሥር ጎንበስ በሉ፣ የጠራ እይታ ያላችሁ፣ ግልጽነት የተካነ መንፈስ ያላችሁ የሚያበራ ፊት ይኑራችሁ፣ ግልጽነትን አትፍሩ፣ ቤተ ክርስቲያን ተልእኮዋ ለመፈጸም ስውርነት አያስፈልጋትም፣ በዓለማዊነት ደመና ያልተከደነ እይታ እንዲኖራችሁ ንቁ፣ በስውር ስምምነት በሚደረግበት የሚያነወልል ማራኪ በሆነው ቁሳዊነትና ዓለማዊነት አትሳቡ፣ በሕዝባችሁ ልብ የሚጮኸው ጥልቅ ጥያቄ የምትተነትኑ ነቢያት ሁኑ፣ እግዚአብሔር ኅልውና ቅርብ መሆኑ መስክሩ፣ እይታችሁ ኢየሱስን ያየና ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘታችሁ የሚያረጋግጥ ይሁን፣ እንዲህ ካልሆነ በድግግሞሽ የሚነገር ማራኪ ነገር ግን ባዶ ቃል ይሆናል፣ በኢየሱስ መቃብር ዙሪያ የቀረ አፉ የተዘጋ የተኮላተፈ ንግግር ሆኖ ይቀራል። ከኢየሱስ ጋር የተገናኘ እይታ ይኑራችሁ።

ጥንቁቅ እይታና ቅርብ

በወቅታዊው ዓለም የኢየሱስ ተከታዮች የሆኑትን የሚበረታታ የሚያሳድግ ጽኑ መለወጥን የሚነቃቃ ሐዋርያዊነት ያስፈልጋል፣ ስለዚህ የቅድት ማርያም ዘጓዳሉፐ ተክለ ሰብነት ጥንቁቅ እይታና ቅርበት የሚለውን ጠቅሰው እንዲህ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነች በሮቸዋን ለሚያንኳኩ ስለ እግዚአብሔር ለመናገር የሚቻላት። የቤተ ክርስቲያን በር የሚያንኳኩት ያለባቸው ስቃይ የማናስተውል ያለባቸው ጥልቅ ፍላጎት የማናነብ ከሆን ምንም ነገር ልናቀርብላቸው አንችልም፣ ስለዚህ አደራ ከፈሪሳዊ ክህነትና ከሥልጣን ወዳጅነት እንቆጠብ።

የመኳንንት ሳይሆን የጌታ መስካሪ ማኅበረሰብ ነው የሚያስፈልገው፣ ውህደት አንድነት የሚለው የቤተ ክርስቲያን ባህርይ የሚኖሩ እንዲሆኑ ለብፁዓን ጳጳሳቱ መክረው፣ የመክሲኮ ቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልጋት አገልጋይ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የጸና የቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚያቅብ በጌታ ቃልና ሥጋ የተገነባ በዚያ የቤተ ክርስቲያን እስትንፋስ በሆነው በጌታ መንፈስ የሚመራ ጳጳስ ነው።

ስለ ወጣቶች የሚያስብ ጸረ የአደንዛዥ ዕጸዋት ንግድና አንቀሳቓሾች የወንጀል ቡድኖች

ቅዱስ አባታችን በለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን ብፁዓን ጳጳሳት ለወንጌላዊ ልኡክነት ቀናተኞች፣ ለዓለማውያን ምእመናን ሕንጸት የሚያቀርቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለው፦ ወጣቶችን ለብፁዓን ጳጳሳት በአደራ አወክፈው በተለይ ደግሞ ለእነዚያ በገንዘብ የሚታመኑና ሞትን የሚቸረችሩ ያደንዛዥ ዕጸዋት አቅራቢ የወንጀል ቡድኖች በቀላሉ ለሚማረኩና ለአደጋ የሚጋለጡትን ለመቀበል የሚችል የእናት ማሕጸት እንዲኖራቸው መክረው፣ ቤተ ክርስቲያንና ኅብረተሰብ እነዚህ አደገኞች የሆኑት ሥነ ምግባራዊና ጸረ ሰብአዊነት ተግዳሮት በቀላሉ እንዳትመለከት አደራ፣ ከቤተሰብ ከከተሞቻችን ጥጋ ጥግ ክልሎች የሚጀምር አሳቢ ነቢይነት የተካነው የፖለቲካው ዓለም የሚያስተባብር ጥንቁቅ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ያስፈልጋል እንዳሉ ቸራዞ አስታውቀዋል።

ለአገሬዎች ጥንቁቅና ከፍተኛ ትኵረት የተካነው እይታ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለመክሲኮ ብፁዓን ጳጳሳት የመሲኮ መጻኢን አወክፈው እንደ እግዚአብሔር ትእግስተኞች ለአገሬዎች ጥንቁቅና ከፍተኛ ትኵረት የተካነው እይታ እንዲኖራችሁ አደራ፦

ስደተኞች ከድንበር ማዶ ቀርቦ መከታተል

በሚሊዮን የሚቆጠረው የሚሰደደው የመክሲኮ ዜጋ እንዳይረሳ፣ መሠረታቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ችላ እንዳይሉ ብፁዓን ጳጳስት ቅርብ በመሆን እንዲደግፏዋቸው አደራ ብለው፣ አለ ምንም የድንበር አጥር ቀርባችሁ የመልክአ ምድራዊ ስደት ከገዛ እራስ ፍልሰት እንዳይሆን ደግፏቸው፣ የቤተ ክርስቲያን አንድነት መስካሪያን በመሆን የዚያ በሰው ልጅ ውስጥ ያለው ሰብአዊ ውህደት መንከባከብ እንጂ ሰብአዊነት የሰው ኃይል በሚል የንግዳዊ አመለካከት ብቻ እንዳይለካ አደራ በማለት የለገሱት ምዕዳን ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.