2016-02-15 16:22:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለመክሲኮ የፖለቲካ አካላት፦ የጋራ እንጂ ለግል ጥቅል አለ ማሰብ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ እ.ኤ.አ. የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም. መክሲኮ እንደገቡ በአገርቱ ርእስ ብሔር ኤንሪከ ፐኛ ነቶ ከክብር ባለ ቤታቸው ጋር በመሆን አቀባበል ካደረጉላቸው በኋላ ለአገረ መክሲኮ ክብር ወደ ርእሰ ብሔር ሕንፃ በመሄድ እዛው ከርእሰ ብሔሩ ጋር ዳግም በመገናኘት ገጸ በረከት ከተለዋወጡ በኋላ በአገሪቱ ሰዓታ አቆጣጠር አምስት ሰዓት ከአሥራ አምስት ደቂቃ በአገሪቱ የሕገ መንግሥት የጉባኤ አደራሽ የመክሲኮ የመንግሥትና የፖለቲካ አካላት እንዲሁም በአገሪቱ የሚገኙት የተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት በተገኙበት ጉባኤ ፊት ለክብራቸው የእንኳን ደህና መጡ የርእሰ ብሔር ንግግር በመቀጠል ባስደመጡት ቃል፦

ለጥቂቱ ልዩ መብት ሳይሆን ለጋራ ጥቅም መትጋት

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስደመጡት ቃል በዚያ ከመላ የመክሲኮ ሕዝብ ብዛት ውስጥ ግማሹን ለሚሸፍነው ወጣት ትውልድ እንዲተኮር፣ ምክንያቱም የወጣት ክብር አገርን የሚያድስና የሚለውጥ ኃይል ነው። ስለዚህ ለእዚህ የአገር መጻኢ ማሰብ ለአገር ዋስትና መስጠት ይሆናል። በመሆኑም ለጋራ ጥቅም መትጋት ወሳኝ ነው።

ሌላውን የማግለል እንደ ጥራጊ የሚመለከት ባህል ማሸነፍ

የመክሲኮ ሉእል እሴት የአገሪቱ ኅብረ ባህል ምንጭ ያለው፣ ይኽ ደግሞ የአገር ትልቅ ኃብት ነው፣ ይኸንን ኅብርአዊነት መንከባከብና ተገቢው ክብር በመስጠት ለጋራ ጥቅም መትጋት ያስፈልጋል። የተለያዩ የአገሪቱ የፖለቲካ አካላት የማኅበራዊ አካላት ለአገር ጥቅም መተባበር ይኖርባቸዋል። ስለዚህ ይኽ ለጋራ ጥቅም ላይ ያነጠጠረው ስምምነት ሌላውን የሚያገል እንደ ጥራቂ የሚመለከተውን ባህል ለማሸነፍና የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ለመንከባከብ መሠረት ነው።

የመንግሥት የፖለቲካ የማኅበራዊና የባህል አካላት ለሁሉ የአገሪቱ ዜጋ በሚበጅ ፍላጎት ላይ በማተኵር ቤተሰብ ተፈጥሮ ለመንከባከብ በድኽነት የሚኖሩትን ከወድቁበት ችግር ለማላቀቅ ሁሉም በአገር ኃብት ላይ ሱታፌ እንዲኖረውና የአገር ሃብት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያበቃው የእኩልነት መንገድ በመገንባቱ ረገድ ተግተው፣ ፍትህ ሰላም እንዲያነቃቁ አደራ እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፦ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅድስት ድንግል ማርያም ዘጓዳሉፐ ቅንስላዊ የስእል ንድፍ ገጸ በርከት እንዳቀረቡላቸውና የመክሲኮ ሕዝብ ቅዱስነታቸውን ለመቀበል ያሳየው የሞቀ ሃሴት የተካነው ውሉዳዊ መንፈስ ርእሰ ብሔሩ ባስደመጡት ንግግር የራሳቸው በማድረግ መክሲኮ ቅዱስነታቸውን ስታስተናግድ ትልቅ እንድል ነው እንዳሉ ያመለክታል።    








All the contents on this site are copyrighted ©.