2016-02-12 08:52:00

“እጅን ወደ ኪስ የማይስከትት የህማማት ወቅት የህማም ወቅት ልባል አይገባውም”


በትላንትናው እለት ማለትም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በየካቲት 10.2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ አስተምሮ ለተገኙት ምዕመናንና የሀገር ጎብኚዎች በልማዳዊው የእለተ ረቡዕ አስተምሮዋቸው ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ ትኩረት ያደርጉት በእለቱ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የስርዓተ ሊጡርጊያ አቆጣጠር የተጀመረውን የህማማት ሳምንት ማዕከል ያደረገ እንደነበረ ጋዜጠኛችን አለክሳንድሮ ዲ ካሎስ ዘግቡዋል።

የህማማት ሳምንት በተለይም በዝህ በያዝነው ቅዱስ ልዩ የምህረት ኢዩቤልዩ አመት ትልቅ ትርጉም የምሰጠው ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ ሁሉንም የሰው ልጆች በእኩልነት የምናይበትና ወንድማማችነታችንን የምናጠናክርበት ልዩ ጊዜ ልሆን ይገባል ብለው በተልይም ደግሞ ከእግዚአብሔር የተሰጠንን ማንኛውንም ስጦታ በአግባቡ በመጠቀምና የተቸገሩትን የምናስብበት ልዩ ወቅት መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

ቅዱስ አባታችን አሳባቸውን ስያጠናክሩም “በዝህ በምሕረት አመት ቅዱስ በርን ማለፍ ብቻ ቅዱስ ልያደርገን አይችልም ካሉ ቡኋላ ትኩረት ልንሰጠው የምገባው ጉዳይ ልባችንን በማራራት ለተቸገሩት የምንጸውትበት ጊዜ እንድሆን ያስፈልጋል ብለዋል።

እኛ በምንኖርበት በአሁኑ ዘመን 80% የዓለም ሓብት በጥቂቶች ማለትም 20% በማይሞሉ ሰዎች ቁጥጥር ሥር መሆኑ የታወቃል ያሉት ቅዱስ አባታችን ሓብትን ማካበት በራሱ ሓጥያት ባይሆንም ከሌሎች በተለይም ከተቸገሩትና በጦርነት ከተጎሳቆሉ የምህበረሰብ ክፍሎች በማሰብ ካለን አንጡራ ሓብት ላይ መለገስን ልንለማመድና ክርስትያናዊ ግደታችንን ልንወጣ ያስፈልጋል ብለዋል።

“እጅን ወደ ኪስ የማይስከትት የህማማት ወቅት የህማም ወቅት ልባል አይገባውም” ያሉት ቅዱስ አባታችን “መጻሓፍ ቅዱሳችን እንድምያሳስበን የሰው ልጆች ሁሉ በአንድነትና በእኩልነት ነጻ በሆነ መልኩ የዓለም ሀብት ተጠቃሚ ልሆኑ ይገባል ብለው ከእግዛብሔር የተሰጠን በዓለም ወስጥ የምገኘው በረከት ጥቂቶች እንዲደሰቱበትና አብዛኛው የበይ ተመካች እንዲሆን ባለመሆኑ፣ ይህንን እውነታ በመረዳትና የእግዚአብሔርን ፈቃድ እውን ለማድረግ ለተቸገሩ የሰው ልጆች ሁሉ እንደየ አቅማችን ካለንን በማካፈል የምሕረት ኢዩቤሊዩን ለየት ባለ ሁኔታ ማክበር ይጠበቅብናል።

በመጨረሻም መንፈሳዊ ግደታችንን ለመወጣት አስራት መስጠት እንዳለብን የምያሳስበንን የመጻሓፈ ቅዱስን ቃል በተግባር ላይ ማዋል ይጠበቅብናል ብለው ይህንንም አስራት   ድኾችን፣ ወላጅ አልባ ልጆችንና መብለቶችን በአጠቃልይ በጦርነት እና በርሃብ የተጎሳቆሉትን በምርዳት ተግባራዊ በሆነ መልኩ ምሕረትን ማሳየት የጠበቅብናል ብለዋል።

በመጨረሻም በዝህ በህማማት ወቅት ምስጢረ ንስሓን በማዘውተር. እርስ በርሳችን ይቀር በመባባልና በመዋደድ ካለን በማካፈል የምገኘውን መንፈስዊ በረከት እና ፀጋ ከእግዚአብሔር የምንቀበልበት ቅዱስ ወቅት በመሆኑ እድሉን ልንጠቀምበት እና መንፈሳኢ ፍሬን ልናፈራ ይገባል በማለት ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.