2016-02-11 11:05:00

የአርባ ቀን ጾም መሪ ቃል “ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለው” ማቴ. 9.13


እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በጥር 10.2016 ቅዱስ የምሕረት አመትን አስመልክቶና በዛሬ እለት እንደ ጎርጎሮሳዊያን የስራዓተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር “ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለው” በምለው ከማቴዎስ ወንጌል በምዕራፍ 9.13 በተጠቀሰው መሪ ቃል የተጀመረውን የህማማት ወይም የአርባ ቀን ጾም በዛሬው እለት ተጀምሩዋል።

ይህንንም ቅዱስ ወቅት ምክንያት በማድረግ ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ የምሕረት መልዕክተኞች እንድሆኑ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ አንድ ሺ ለሚሆኑ ካህናት “የምሕረት መልዕክተኞች” በቅድስት መንበር መንፈሳዊ ስልጣን ብቻ በተለየ ሁኔታ ይፈቱ የነበሩትን ሓጥያቶችን መፍታት እንድችሉ የምያስችላቸውን መንፈሳዊ አደራን በዛሬው ምሽት በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከምችቱ በምስት ሰዓት ተኩል ላይ ከቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ እንደተቀበሉ ታውቋል።

በዝህ መንፈሳዊ ሹመት ዝግጅት ላይ ተካፋይ ከነበሩትና የፍራንችስካዊያን ማህበር አባል ከሆኑ ወንድም ኤሚልያኖ አንቴኑቺ ጋር ጋዜጠኛችን ሞኒያ ፓሬንቴ ባደረገችው ቃለምልልስ መረዳት እንደተቻለው፣ ለዝህ ታላቅ መንፈሳዊ የምሕረት ተልዕኮ በመታጨታቸው ደስታና በተለይም ደግሞ ታላቅ አላፊነት የተሰማቸው መሆኑን ገልጸው ምሕረት የፍቀር ሁለተኛ ስሙ እንደምሆኑ መጠንና የእግዚአብሔር ህላዌ መገለጫ እንደመሆኑ፣ እኛ በተለየም ለሚስጢረ ንስሓ አላፊነት የተሰጠን ካህናት የእግዚአብሔር ህላዌ የሆነውን ምሕረት አዳራጊነትን በመተግበር በማስተማር ምዕመናን የእግዚአብሔር የምሕረት ፊትን እንዲመለከቱ ልናግዛቸው ይገባል ብለዋል።

የቅርታ አድራጊነት ከእግዚአብሔር የሚሰጥ መንፈሳዊ ስጦታ ነው በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ወንድም ኤሚልያኖ ይህንን በምስጢረ ክህነት የተሰጠንን ታላቅ መንፈሳዊ ስጦታ ሳንሰላች በታልቅ ጠበብና ጥንቃቄ ለምዕመናን የህንን አገልግሎት ልንሰጥ አደራ ተጥሎብናል ብለው ከሁሉም በላይ ደግሞ ትኩረት ልሰጠው የሚገባው ጉዳይ ሓጥያተኛው ሓጥያቱ ይቅር እንደተባለለት እንዲሰማው በማድረግና ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ምሕረት በእራሱ ሕይወት ውስጥ በመተግበር ለሎችንም ይቅር ማለት የምያስችል መንፈሳዊ ሀይልን በመፈጥር ዘላቂ የሆነ መንፈሳዊ አግለግሎትን ልናበርክት ይገባል ብለዋል።

በማስከተልም በተለይም በዝህ በያዝነው ልዩ ኢዩበልዩ የምሕረት አመት ከእኛ ካህናት የሚጠበቀ አላፊነት፣ ይቅርታ ማድረግ ማለት በመጀመሪያ ለሓጥያተኛው መልካም አቀባበልን በማድርግ ሳይፈራና ስይሸማቀቅ ሓጥያቱን እንዲናዘዝ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ማለት መሆኑን በመረዳትና በሓጥያተኛው ሕይወት ውስጥ መንፈሳዊ ለውጥ እንዲከስት በማድረግ ጭምር በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ፍትህን እንዲተገብር በማስተማር ጭምር መንፈሳዊ አገግልፍሎትን ተግተን ልንሰጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

በመጨረሻም እግዚአብሔር ሀጥያትን እንጂ ሀጥያተኞችን አይጠላም ብለው ምሕረት አድራጊነት ከፍተኛ መንፈሳዊ በረከትንና ደስታን በሕይወታችን ስለምያስከስት የይቅር ባይነትን ባሕሪ በመላበስ የሰማይ አባትችን ይቅር እንዳለን እኛም እርስ በእርሳችን ይቅር ልንባባል የጋባል በማለት አስተያየታቸውን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.