2016-02-11 11:12:00

17% ወጣቶች በቀን አብዛኛውን ጊዜያቸውን የምያጠፍት በማህበራዊ ድህረግጽ ላይ ነው።


በጣልያን ሀገር በሮም ከተማ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ወጣቶችን አስመልክቶ የተካሄደው ጥናት እንድምያሳየው 17% ወጣቶች በቀን አብዛኛውን ጊዜያቸውን የምያጠፍት በማህበራዊ ድህረግጽ ላይ መሆኑን የደረሰብት ስሆን አብዛኞቹ ተጠቃሚዎች ደግሞ ከማህበራዊ ድህረገጽ ተለይቶ መዋል እንድማይችሉ ጥናቱ አመልክቶ ይህም አሀዝ የምያሳየው በጣልያን የሚገኙ ከ4 ወጣቶች አንዱ በቀን አብዛኛውን ጊዜውን የምያጠፋው በምህበራዊ ድህረ ገጽ ላይ መሆኑን አውደጥናቱን የተከታተል ጋዜጠኛችን አለክስአንድሮ ፊሊፔሊ አስታውቋል።

“የድህረ ገጽን አገልግሎት ባግባቡ ለማስከሄድ የራስህን ድርሻ አበርክት” በሚል መሪ ቃል የተካሄደ የነበረው የ2016 የዓለም የድህረ ገጽ አገልግሎት ጥንቃቄ አውደጥናት ላይ እንደተገለፀው በተለይ ወጣቶች የዝህ ማህበራዊ ድረ ገጽ ለተገባው ጉዳይ ብቻ ማዋል ባለመቻላቸው ለተለያዩ የማህበራዊ ቀውሶች እየተዳረጉ መሆናቸው ተወስቷል።

በጣሊያነኛ ቋንቋ “ቴሌፎኖ አዙሮ” ወይም በአማሪኛ በግርድፉ ስተረጎም “ሰማያዊ ስልክ” የተባል ድርጅት ባካሄድው ጥናት ለማወቅ እንደተቻለው 45% ወጣቶች አብዛኛውን ጊዜያቸውን የምያጠፍት በምሕበራዊ ድህረ ገጽ ላይ መሆኑን አምለክቶ ከነዝህም ውስጥ ከአምስት ወጣቶች አራቱ ያላማቋርጥ መልዕክቶችን በማህበራዊ ገጽ ላይ በሚገኘው በፌስ ቡክና ተመሳስይ አፕልኬሽኖችን በመጠቀም የሚላላኩ ስሆን ሃያአንድ (21%) ወጣቶች ደግሞ በምሽት ከእንቅልፋቸው በመንቃት መልዕልት መላክና አለማላኩን በእጅ ስላካቸው ላይ እንደምያረጋግጡ ታውቋል።

ኤርኔስቶ ካፎ የተባለ የዝህ ጥናት መሪ እንደገለጸው “በጣናታችን ያገኘነው እና በጣም አሳሳቢ የሆነ ጉዳይ ብኖር በአብዛኛው ከ6-7 የእድሜ ክልል ውስጥ የምገኙ ወጣቶች አንዳንድ ጌዜም በአራት እና በአምስት የእድሜ ክልል ውስጥ የምገኙ ሕጻናት እንኳን ሳይቀር የማህበራዊ ድህረ ገጽ ተጠቃሚዎች እየሆኑ መምጣታቸው እንድምያሳስባቸው ገልጿል።

“ምንም የጊዜ ገደብ ሳይደርግባቸው በቀን ከስምንት ሰአት በላይ፣ በማህበራዊ ገጽ ላይ አንድ ሕጻን ልጅ ይህንን ያህል ጌዜ ማጥፋቱ አሳሳቢ ጉዳይ ነው ብሎ በተለይም ደግሞ ምን አይነት ፕሮግራሞችን እየተከታተል መሆኑንና የምከታተላቸውም የኦንልይን (የቀጥታ) ፕሮግራሞች ከእድሜው ጋር መሄድ ወይም አለመሄዱን ጠቃሚ ወይም ጎጅ መሆናቸውን ወላጆች ማርጋጋግጥ አለማቻላቸው ድግሞ ጉዳዩን የበለጠ አሳሳቢ ያደርገዋል ብለዋል።

በተጨማሪም መጣቶቹ በትምህርት ቤት በትምሕርት ገበታ ላይ በምገኙበት ወቅት በአብዛኛው ከኢንትርኔት ጋር የተገናኙ በመሆናቸው በክፍል ውስጥ ለምሰጠው አስተምሮ ትኩረት ለምሰጠት እንደምቸገሩ ገልጸው እንዝህን ችግሮች ለምቅረፍ እንድንችል የትምህርት ተቋማትና የምመለከታቸው ድርጅቶች ሁል የጋር መግባባት በምፍጠር በልጆቻችን ላይ እየደረሰ የምገኘውን ከፍተኛ አደጋ በጋር ልንዋጋና ልጆቻችንን በተገቢው መንገድ እንድጓዙ ልንረዳቸው ያስፈልጋል በላዋል።

በአውደ ጥናቱ ልይ የተሳተፉት የቫቲካን ኢንተርነት አገልግሎትና የኮሚንኬሽን ሓላፊ የሆኑት አቡነ ሉችዮ አድሪአና ሩኢዝ በበኩላቸው እንደገለጹት “በየጊዜው በተክኖሎጂ የለውጥ ጎዳና ላይ የምትገኘው አለማችን ያስተዋወቀውን የኢንቴርነት አገልግሎት፣ መልካም የግንኙነት አጋጣሚን በመጠቀም፣ ለተሻለና ለመልካም አገልግሎት ልናውለው እንደ ሚገባ ገልጸው፣ አሁን በጥናቱ እንደተጠቀስው የምታዩትን ችግሮች አላፊነት በተሞላው መልኩ ሁላችንም በተለይም ድግሞ ወላጆች፣ ኢንቴርነት ብዙ መልካም ነገሮችን በተለይም ደግሞ መልዕክቶችን በፍጥነት ወደ አለም በማሰራጨት አለማችን አንድ መንደር እንድትሆን ያበረከትውን አስተዋጾ ከግምት በማስገባት፣ ይህንን ተክኖሎጂ በአግባቡ ልንጠቀምበት እንድምገባና በተለይም ደግሞ ለእድሜ ያልደርሱ ልጆች ያለ አግባብ እንዳይጠቀሙ ልመክሩ እና ልያስተምሩ ይገባል በማለት በአውደጥናቱ ማጠቃለያ ላይ አሳስበዋል።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.