2016-02-08 16:08:00

ቫቲካን፦ የሃገረ ቫቲካን ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሥራ መባቻ ሥነ ሥርዓት


የሃገረ ቫቲካን የፍርድ ቤት ዓመታዊ የሥራ መባቻ ሥነ ሥርዓት ምክንያት በቅድስት መንበር የሕግና ፍትሕ ጉዳይ ሕንጻ  በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ እ.ኤ.አ. የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ዓውደ ጉባኤ መካሄዱና በዚህ በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የሃገረ ቫቲካን ፍርድ ቤት ፍትህ ለሚያነቃቃው ቢሮ ተጠሪ ጠበቃ ጃን ፒየሮ ሚላኖ በቅርቡ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ውሳኔ መሠረት የተደረሰው የቤተ ክርስቲያን ምሉእ ኅዳሴ ላይ በማተኮር ንግግር ማስደመጣቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ ገለጡ።

የሃገረ ቫቲካን ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሥራ መባቻ ሥነ ሥርዓት ምክንያት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን አገረ ቫቲካን የሃገረ ቫቲካን አስተዳዳሪ ሕንጻ በሚገኘው ቅድስት ማሪያን የቤተሰብ እናት በተሰየመው ቤተ ጸሎት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ የተጀመረ መሆኑ ሎሞናኮ ገልጠው፦ በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ከቅድስት መንበር በሥውር የወጡ ሰነዶች ቫቲ ሊክስ በሚል መጠሪያ በማጠቃለል በቅጥፈትና በሥውር የወጡ ሰነዶችና የሰነዱ ጥልቅ ሃሳብ በማስታወስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራችስኮ ያነቃቁት ህዳሴ በጠቅላላ የመላ ሃገረ ቫቲካን የሥራ ሂደት እንዲሁም የሃገረ ቫቲካን ፍርድ ቤት ጉዳይ ያጠቃለለ የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮና ቅዋሜዎችዋ የሚመለከት መሆኑ አብራርተው፣ የቅዱስ አባታችን ኅዳሴ ዓበይት መሰናክሎች መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው እንዳሉ ሎሞናኰ አስታወቁ።

የሕግና ፍትሕ ጉዳይ ግለ ሰብ ብቻ ሳይሆን ማኅበረሰብ የሚመለከት ጭምር ነው። ይኽ ደግሞ ወዳጅን ማፍቀር ሰላም ፍጥረትንና ተፈጥሮን መንከባከብ እኩልነት ማረጋገጥ እውነትና ፍቅር የተሰኙት እሴቶች ማእከል ያደረገ ነው እንዳሉ ሎሞናኮ አስታውቀዋል።

የዘንድሮው የአገረ ቫቲካን 87 ኛው ዓመታዊ የሥራ መባቻ ሥነ ሥርዓት ኩላዊት ቤተ ክርስቲያን እየኖረችው ካለው የምኅረት ዓመት ጋር የተሳሰረ በመሆኑም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደሚሉትም ሕግ ለብቻው በቂ አይደለም፣ እንዲህ በመሆኑም እግዚአብሔር ከሕግ ማዶ ምኅረትንና ይቅርታን ያስቀድማል። ሕግ ለምድራዊ ሕይወት አስፈላጊ ነው። ሆኖም ምኅረትንና ይቅር ባይነትን የሚያካትት እንዲሆን ጥበብ ያስፈልጋል እንዳሉ የገለጡት ሎሞናኰ አያይዘው፦ ጠበቃ ሚላኖ የቤተ ክርስቲያን ሕገ ቀኖና ታሪክና ዓላማውንም ለይተው በማስታወስ በቤተ ክርስቲያን ሕገ ቀኖና ታሪክ ዘንድ በዓለም የሚታዩት ለውጦች ግምት በመስጠት የተከናወኑት ህዳሴዎች ለይተውና ከዚህ ጋር በማያያዝም ቤተ ክርስቲያን በተለያየ የውስጥ መዋቅሮችዋና የመስተዳድር ቢሮዎቿ ዘንድ እየተረጋገጠ ያለው ህዳሴ ምን ተመስለው በጥልቀት ማብራራታቸው ገልጠዋል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.