2016-02-08 16:01:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ምድር ለሁሉም የተሰጠ ጸጋ ነው


በየወሩ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በቅዳሴ በአስተንትኖና በማኅበራዊና በግል ጸሎት እንዲያርግ የሚያቀርቡት የጸሎት ሃሳብ መሠረት በማድረግ በዚህ እ.ኤ.አ. የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት የድምጸ ምስል መልእክት፦ ተፈጥሮ ፍርያማ ለማድረግና እንድንከባከበውም የተሰጠ ጸጋ ነው የሚል ምኅዳር ማእከል ያደረገ የጸሎት ሃሳብ ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።

በተላለፈው የድምጸ ምስል መልእክት ቅዱስ አባታችን ያቀረቡት ሃሳብ  የሚታየው የተፈጥሮ ብከላ የሚገልጥ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ያካባቢ ብከላ አንድ ወጣት ባይስልክ እየነዳ ባንድ ባረንጓዴ የተፈጥሮ ሃብት በታደለ ክልል ሲጓዝ ሌላው በአየር ብከላ ምክንያት አፉን ከድኖ ሲጓዝ  ወንዶችና ሴቶች በእርሻ ክልል የመከር ምርት ሲሰበስቡ አንድ ወጣት የተጠቀመበት በፕላስቲክ የተሠራ ብርጭቆ በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦታ ሲያኖር ብዙ ሕዝብ ደግሞ አንገቱን ቀና በማድረግ የጸሐይ ብርኃንን ሲያተኵሩ በጠቅላላ የተፈጥሮ ወቅታዊ ሁኔታ በሚያወሱ ምስሎች የተሸኘ እንደነበር የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አክለው፦ ቅዱስ አባታችን አማኞችም ኢአማንያንም ሁሉ ተፈጥሮ የጋራ ሃብት መሆኑና ተፈጥሮ የሚያድለው ምርትና ያለው ሃብት ለሁሉ ጥቅም መሆኑ ይታመናሉ፣ ሆኖም በዓለም የሚታየው ድኽነትና በተፈጥሮ ላይ እየተከስተ ያለው ዘርፈ ብዙ ብከላ የምንከተለው የኤኮኖሚ ስልትና የልማት እቅድ ለየት ያለ ሌላ አዲስ የሕይወት ስልት እንድንክተል ግድ ይለናል እንዳሉ ገልጠው ሁሉም በጋራ የሚያቀፍ ኩላዊ ለውጥ ያስፈልጋል፣ ስለዚህ የጋራ ቤታችን የሆነውን ተፈጥሮ ለመንከባከብ ከፍጆታ ባርነት ነጻ መውጣት ያስፈልገናል በማለት እ.ኤ.አ. ለየካቲት ወር ያስተላልፉት የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሃሳብ ማጠቃለላቸው አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን ያስትላለፉት የድምጽ ምስል መልእክት በስፓንሽ ቋንቋ ሲሆን ቀጥሎም በተለያዩ 10 ቋንቋዎች ተተርጉሞ መሰራጨቱ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.