2016-02-02 10:37:00

“ምህረትን የምያደርጉ ብፁዓን ናቸው ምሕረትን ያገኝሉና” ማቴ. 5፣7


እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር ከሓምሌ 26-31.2016 በየሁለት አመት አንድ ጊዜ  የምደረግው 31ኛው አለማቀፍ የውጣቶች ቀን በፖላንድ ሀገር በክራኮቪያ ከተማ ቅዱስ የምህረት አመትን ባማከለ መልኩ እንደምከበር የታወቀ ስሆን እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ከአምስት መቶ ሺ በላይ ወጣቶች ለመገኘት የተመዘገቡ መሆናቸውን የዝግጅቱ አላፊ የሆኑትን ካርዲናል ስታኒስላው ድዝዊዝን አነጋግራ ጋዜጠኛችን  ሮበርታ ባርቢ ዘግባለች።

በ2011 እስፔን ዋና ከተማ በማድሪድ በተደረግው 29ኛው የአለም ወጣቶች ቀን ቡኋል እድሉ በቀጣይነት ለእኛ እንደምሰጠን ታሳቢ በማድረግ ከሦስት አመት በፊት ዝግጅት ማድረግ እንደጀመሩ የገለጹት ብፁ ካርዲናል ስታኒስላው፣ በ2013 በብራዚል በተደረገው 30ኛ የወጣቶች ቀን ላይ በይፋ እንድናዘጋጅ ከተፈቀድለን ቡኋላ ዝግጅቱን በተቀላጠፈ መልኩ እየተካሄደ  መሆኑን ገልጸዋል።

31ኛው የአለም ወጣቶች ቀን የምከበረው ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ በመረጡት ከማቴዎስ ወንጌል 5፣7 ላይ የተወሰደው “ምህረትን የምያደርጉ ብፁዓን ናቸው ምሕረትን ያገኝሉና” በምለው መሪ ቃል ላይ ተመስርቶ መሆኑን ገልፀው ከዝህ በፊት በነበሩ ር.ሊ. ጳጳሳትም ጭምር ትኩረት ተሰጥቶት የነበረውና በተለይም ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ ይህንን አመት ልዮ የምሕረት አመት ብሎ በመሰየማቸው አጋጣሚውን ተጠቅመው በተለይም ወጣቱ ወደ እግዚአብሔር በንስሓ በመመለስ ያገኘውን መንፈስዊ ፀጋ ወደ መጣበት ቦታ ሁሉ ይዞ እንድመለስ አጋጣሚውን የምፈጥር ቀን ይሆናል ብለን ገምተናል ብለዋል።

በተለይም አሉ ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላው ንግግራችወን በመቀጠል “በዝህ የአለም ሰላም አስጊ ሁኔታ ላይ በሆነበትና አለም በተለይም አውሮፓ በተለያዩ የምህበራዊ ቀውስ ውስጥ በምትገኝበት በአሁኑ ዘመን የዝህ በዓል መከበር ወቅታዊ ምላሽና ማስገንዘቢያ በወጥቱ ውስጥ ይፈጥራል ብለን እናስባለን ብለው ልክ ሲስተር ፋውስትና እንደተናገርችው “በእግዚአብሔር ምሕረት እስካልታቀፍን ድረስ አለም ሰላም ልያገኝ አይችልም” እናዳለችው የወጣቱን ልብ ወደ ንስሓ በመሳብ በእግዚአብሔር ምሕረት እንዲመላለስ በማድረግ ለአለም ሰላም ወጣቱ የበኩሉን አስተዋጾ እንድያደርግ ለማስቻል የበኩላችንን ጥረት እያደርግን እንገኛለን ብለዋል።

በመጨረሻም የምፈለገውን መንፈስዊ ለውጥ ለማምጣትና የውጣቶችን ልብ በመክፈት የእግዚአብሔርን ምሕረት እንድለማመመዱ መንገድ መክፈት፣ የምወሰነው በበዓሉ ቅድመ ዝግጅት ላይ በመሆኑ በተለይም ደግሞ መንፈሳዊና ግብረ ገባዊ ተግባራትን  ትኩረት ያደርጉ መንፈስዊ ተግባራትን ለመፍጸም የምያስችል በቂ ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን በአጽኖት ገልጸው በዝህ በዓል ላይም ከ150 ሀገራት የተውጣጡ ከ600-700 ሺ ወጣቶች ይገኛሉ ብለን እንጠብቃልን በማለት መግለጫቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.