2016-02-02 09:40:00

"ክርስትያን መሆን ማለት የክርስትያንን ተግባር በመፈጸም እምነታችንን በተግባር ማሳየት ማለት ነው"::


ዘወትር ረቡዕና እሁድ ምዕመናን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ለምሰጠው የጠቅላላ የወንጌል አስተምሮ ለመከታተል በርከት ያሉ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ምዕመናንና ሀገር ጎብኝዎች እንደሚገኙ ይታወቃል።

ከቫቲካን በተሰጠው መመሪያ መሰረት ልዩ የምሕረት አመት ኢዩቤልዩን አስመልክቶና ልዩ ትኩረት ለመስጠት ከተለመዱት የጠቅላላ የትምህርተ ወንጌል አስተምሮ ቀናት በተጨማሪ በዕለተ ቅድሜ የምሕረት አመትን አስመልክቶ ልዩ የትምህርተ ወንጌል አስተምሮን ለመሰጠት በማሰብ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በጥር 30.2016 በይፋ በቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮስ መሪነት ተጀምሩዋል።

በዝህ የመጀመሪያውና በቀጥይነት የምሕረት አመት እስክጠናቀቅ ድረስ ለምዘልቀው በቀጥይነት ዘውተር ቅዳሜ ለምደርገው የጠቅላላ የትምህርተ ወንጌል አስተምሮዋቸው ላይ ቅዱስ አባታችን እንደገለጹት “የእግዚአብሔር ምሕረት ሁሉን አቀፍ መሆኑን በመረዳት ሁላችንም ክርስትያኖች የክርስቶስ ምሕረትንና ደስታን አብሳሪዎች ልንሆን ይገባል” በለዋል ስል አሌክሳንድሮ ጂዞቲ ዘግቡዋል።

“ምሕረትን ከእግዚብሔር ሳንሰላች ሁል ጊዜ ልንጠይቅ ይገባል” በማለት አስተምሮዋቸውን የጀመሩት ቅዱስ አባታችን ምክንያቱንም ስያስረዱ “በድካማችን ሁሉ እግዚአብሔር ቀርቦ እንዲረዳንና እንዲያበረታታን በሕይወታችን ደስተኞች እንድንሆንና እምነታችን እንድጠነክር  የእግዚአብሔር ምሕረት አስፈላጊ ነው” ብለዋል።

ቅዱስ አባትችን በተጨማሪም የቅዱስ ዩሓንስ ጳውሎስ ሁልተኝን አስተምሮ በማስታወስ በምህረትና በመንፈሳዊ ተልዕኮ መካከል ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት እንዳለ በአጽኖት በመግለጽ “ሁሉም ክርስትያን ይህንን አብነት በመከተል በወንጌል አስተምሮ ላይ ተመስርተን የእግዚአብሔር ምሕረት በአለም ላይ እንድናውጅ የተሰጠንን መንፈሳዊ ተልዕኮ መወጣት ይኖርብናል” ብለዋል።

“የእግዚአብሔርን ምሕረት ማወጅ ሕይወታችንን በደስታና በበረከት ይሞላታል ያሉት ቅዱስ አባታችን እኛም የተቀበልነውን ደስታና በረከት ለሌሎች ወንድምና እህቶቻችን በማወጅ በእግዚአብሔር የሚገኘውን ደስታና በረከት እንዲቋደሱ ለማድርግ የግላችንን ጥረት ልናደርግ ያስፈልጋል” ብለዋል።

በማከልም “ምሕረት የግል መጽናኛ ቢቻ ተደርጎ ልቆጠር አይገባውም ያሉት አባታችን የእግዚአብሔር ምሕረት ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ ነጻ ስጦታ በመሆኑ ይህንን ታላቅ የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጫ የሆነውን ምሕረት ለሁልም ይዳረስ ዘንድ በርትተን የበኩላችንን ጥረት በማድረግ የክርስቶስን ምህረት እና ዘላቂ ደስታ በእርሱ ብቻ እንደሚገኝ በቀጣይነት ልናውጅ ይገባል” ብለዋል።

በመጨረሻም “ ክርስትያን መሆን ማለት የክርስትያንን ተግባር በመፈጸም እምነታችንን በተግባር ማሳየት ማለት ነው” ያሉት ቅዱስ አባታችን “እምነታችንን በተግባር ስንገልጽ ብቻ ነው የሌሎችን ልብ በመንካት ልባቸውን ለእግዚአብሔር ፍቅርና ምሕረት በመክፈት የበረከቱ ተካፋይ ማደረግ የምንችለው” ብለው “ህንን ለመፈጸም የምያስችለንን ፀጋ ከእግዚአብሔር በመለመን እምነታችንን በተግባር በማሳየት ሌሎችን መማረክ ይጠበቅብናል” ማለት አስተምሮዋቸውን አጠናቀዋል።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.