2016-01-29 16:31:00

ማራከሽ፦ ለሃይማኖት ነጻነት መከበር


እ.ኤ.አ. ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም. የሞሮኮ የድጋፍና የምስልምና ሃይማኖት ጉዳይ ሚኒ.ና የአገሪቱ በምስልምና ሃይማኖት ተከታይ ማኅበርሰብ ለሰላም የተሰየመው ዋና መቀመጫው በተባበሩት የኤመሪት አረብ አገሮች የሆነው ማኅበር በጋራ በማራከሽ የዜግነት መብት በምስልምናው ሃይማኖት አመለካከትና ሕግ በሚል ርእስ ሥር ባዘጋጁት ዓውደ ጉባኤ የተሳተፉት 250 አበይት የስነ ምርምር ሊቃውንት የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮች፦ የሁሉም የሃይማኖት ነጻነት ጥበቃ በዓለም ዋስትና እንዲኖረው በማለት የጋራ ጥሪ ማስተላለፋቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የማራከሹ የስምምነት ውል የመዲና የስምመት ውል የሚከተል ነው

ፊደስ የዜና አገልግሎት እንደጠቆመው የማራከሽ ውል ያንን እ.ኤ.አ. ዘንድሮ በ2016 ዓ.ም. 1,400 ዓመት እያስቆጠረ ያለው በመሐመድ ነቢይና በመዲና ሕዝብ መካከል የተደረሰው በሜድና ውል የሚጠራው ስምምነት የሁሉም ሰው ልጅ ከሚከተለው እምነት ውጭ የሃይማኖት ነጻነት  ማክበር የሚለው ማእከላዊ ሃሳብ መሠረት ያደረገ መሆኑ ሲታወቅ፦

ማንኛውም ለጠብ ጫሪነትና ላክራሪነት የሚወተውት አመለካከት ማግለል

ምሁራኑ በፊርማቸው ያጸደቁት በማራከሽ ውል በሚጠራው ሰነድ እንዳመለከቱትም የሃይማኖት ነጻነት አክብሮት ከሚለው ሐሳብ በተጨማሪም በምስልምና ሥርዓተ ሕግ ዜግነት የሚለው ፅንሰ ሐሳብ በጥልቀት በማጥናትና በማሻሻል በትምህርትና ሕንጸት ዘርፍ አማካኝነት ወደ ጦርነትና ግጭት የሚመራው ለጠብ ጫሪነት ላክራሪነት የሚወተውተው አመለካከት ሁሉ ለማስወገድ አቢይ ጥረተ እንዲደረግና ሁሉም ሃይማኖቶች ከጥንት ጀምረው በምንኖርባት ምድር አብረው የሚኖሩ ናቸው ስለዚህ በጋራ ከእርስ በእርስ መጥላላት ነጻ ሆነው በመከባበር ተቀባብለው ለመኖር የተጠሩ ናቸው የሚል ሃሳብ እንዳሰፈሩበት ፊደስ የዜና አገልግሎት አመለከተ።

ሃይማኖት የውሁዳን ሃይማኖት ተከታዮች ሰብአዊ መብትና ክብር ረገጣ መሣሪያ አለ ማድረግ

250 ምሁራን የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የተደረሰው የስምምነቱን ውል ሙስሊም በሆኑት አገሮችና ብዙንሃ የምስልምና ሃይማኖት ተከታይ በሚኖሩባቸው አገሮች የውሁዳን ሃይማኖት ተከታይ ዜጋ ሰብአዊ መብትና ክብር መጠበቅና የብዙሃኑ ሃይማኖት የውሁዳኑ ሃይማኖት አምባገነን መሆን የለበትም በማለት የሁሉም የሃይማኖት ነጻነት ጥበቃ ማረጋገጥ ያስፈልጋል በሚል ሃሳብ ማጠቃለላቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.