2016-01-27 16:26:00

በሮማ የሥነ አመሪካ አገሮች የጥናት ማእከል


ሮማ የሚግኘው የሥነ አመሪካ አገሮች የጥናት ማእከል በዚህ እ.ኤ.አ. በተገባው 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና የቅድስት መንበር ሚና በሚል ርእስ ሥር ልዩ የጥናት ዘርፍ እንደሚኖረው የተቋሙ ዋና አስተዳዳሪ ፓውሎ መሳ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።

ጥናቱም እ.ኤ.አ. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሜክሲኮ ሊያካሂዱት በእቅድ ስለ ተያዘው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ጋር በማያያዝ በሜክሲኮ የሃይማኖት ነጻነት ርእስ ዙሪያ በማተኵር የሚጀመር ሲሆን ባጠቃላይ ቅዱስት መንበር በተለያዩ አገሮች በሚገኙት ሐዋርያዊ ልኡካንዋ አማካኝነት በዓለም አቀፍና በብሔራዊ አቀፍ ፖለቲካ ዘርፍ ያላት ሚና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ትምህርት የሚያጎላ ነው። ስለዚህ ይኽ ሚና ልዩ ጥናትና ግንዛቤ የሚጠይቅ በመሆኑም የሥነ አመሪካ አገሮች ማእከል አቢይ ግምት በመስጠት ያወጣው መርሃ ግብር መሆኑ መሳ አስታውቀዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአመሪካዎች ያካሄዱት ጉብኝት ለምሳሌ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የሕዝብ ተወካዎች ምክር ቤት ፊት ተገኝተው ያስደመጡት ንግግር በጥልቀት ትንታኔ የሚሰጥ እቅድ ነው። በዚህ ብቻ ሳይታጠርም ቅድስት መንበር በአመሪካዎች ያላት ሚና ላይ በማተኮር ቅዉም ሃሳቡንም ለይቶ የሚያቀርብና የሚያብራራ የጥናት ዘርፍ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.