2016-01-27 16:18:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በክርስቲያኖች መካከል ስላለው መከፋፈል ምሕረት እንለምን


በየዓመቱ እንደሚደረገው ሁሉ ይኸው ዘንድሮ እ.ኤ.አ. ከጥር 18 ቀን እስከ ጥር 25 ቀን 2016 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓት የቅዱስ ጳውሎስ መለወጥ ዓመታዊ ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ የሚጠናቀቀው ስለ ክርስቲያኖች አንድነት የጸሎት ሳምንት መከናወኑ ሲገለጥ፣ ፣ ሮማ ፎሪ ለ ሙራ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከቀትር በኋላ 5 ሰዓት ተኩል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተገኝተው የሁሉም የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን መንፈሳውያን መሪዎችና ምእመናን በማሳተፍ ጸሎተ ዘሰርክ መርተው ስብከት መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ገለጡ።

አሁንም በክርስቶስ አካል ዘንድ ገና ያልዳነ ቁስል ሆኖ ያለው በክርስቲያኖች መካከል ስለ ተፈጠረው መከፋፈል ምክንያት የእግዚአብሔር ምሕረት እንለምን፣ እኛ ካቶሊካውያን በሌሎች ክርስቲያኖች ፊት የሳየነው ወንጌላዊ ያልሆነ ተግባር  ምክንያት ሁሉ የእግዚአብሔር ምህረት እንለምን።

በዚህ የኦርቶዶክስ የአንግሊካዊትና የሌሎች አቢያተ ክርስቲያን መንፈሳውያን መሪዎችና ውሉደ ክህነት ምእመናን ባሳተፈው የጋራ ጸሎተ ዘሰርክ፦ ቅዱስነታቸው በለገሱት ስብከት፣ ጳውሎስ ከጠላትነት ወደ ሐዋርያነት መለወጡ በእውነቱ ፍጹም የምህረተ አብነት ምን መሆኑ ያረጋግጥልናል። የጳውሎስ ዘጠርሰስ ጥላቻ አሳዳጅነት ወደ የክርስቶስ ፍቅር ተለወጦ የተቀበለው የተትረፈረፈ ጸጋ ወደ ምሉእ አንድነት እንድንደርስና የእግዚአብሔር ምህረት በእኛ ዘንድ የምህረት ጸጋ መሆኑ በመታመን ወደ ዓለም እንድናበስረው አመክንዮ ነው።

እግዚአብሔርን ማዳመጥ ወደ ውህደት መራመድ ነው

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጳውሎስ መለወጥ ከሚያወሳው ታሪክ በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ለአንድነት ታልሞ የሚደረገው የጋራው ግኑኝነት ጉዳይ ያለው አወንታዊ ተጽእኖ በመለየት፣ አሁንም አቢያተ ክርስቲያን ካላቸው ልዩነት ማዶ የእግዚአብሔር ጥሪ አለና፣ ጥሪው በማዳመጥም ወደ ውህደት መራመድ ነው። ተጨባጭ ወደ ሆነው ምሉእ ውህደት ታልሞ በሚደረገው ጉዞ ማደግ የሚቻል ነው፣ ስለዚህ እርስ በእርስ መቀራረብ በተለይ ደግሞ የእረሱ ሐዋርያት እንድንሆን ወደ ሚጠራው ጌታ ለመቅረብ በሚደረገው ጉዞ ማደግና መለወጥ ያስፈልጋል፣ የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን በጋራ ሆነው የጌታ ቃል ሲያዳምጡና የሰሙትን ቃል እግብር ላይ ሲያውሉ ወደ ውህደት በሚያደርጉት ጉዞ እጅግ የተዋጣለት እርምጃ ይከውናሉ።

የልዩነት ቁስልና ምሕረት

ክርስቲያን ለመሆን መጠራታችን ብቻ አይደለም አንድ የሚያደርገን፣ ከዚህ የጋራው ስም ሌላም የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራዎቹን እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ካል ምንም ፈረቃ ዘወትር ለመመስከርና ለማበሰርም ጭምር ነው። ለጋራ ታልሞ የሚደረገው የጋራው ጉዞ ጦቢያ አለ መሆኑም እየተኖረ ያለው ቅዱስ የምህረት ዓመት ያረጋግጥልናል።

ከሁሉም በፊት የመከፋፈሉ ሐጢአታችን ምክንያት ምሕረትን እንለምን፣ በእውነቱ ይኽ ክፍፍል ገና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አካል ዘንድ ፈውስ እንዳጣ ቁስል ነው። እንደ የሮማ ጳጳስ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን መጋቤ ወንጌላዊ ባልሆነ ተግባር ካቶሊካውያን በሌሎች አቢያተ ክርስቲያን ላይ ለተፈጸሙት እንቅፋት ሁሉ ከጌታ ምህረትን እማጠናለሁ።

ጥንታውያን ስህተቶችና አዲስ ግኑኝነት

የተጠየቀው ምህረት ሌላው በተራህ የምትሰጠው ነው። የተማረ ይምራል ያሉት ቅዱስ አባታችን አስከትለው ባለፈውም ይሁን በአሁኑ ወቅት ጭምር ካቶሊካውያን ወንድሞችና እህቶች ስለ ተፈጸመባቸው በደል ሳይቀር ካለ ምንም ማመንታት ምሕረት ይስጡ፣ መማማር ያስፈልጋል፣ ያለፈው ታሪክ መደለዝ አይቻልም ሆኖም ባለፈው ታሪክ የተፈጸመው በደል በሁሉም አቢያተ ክርስቲያን መካከል ያለው ግኑኝነት ሊያውክ አይገባውም።

ብቸኛይቱ በር

ባረገው ጸሎተ ዘሰርክ የቁስጥንጥንያ የውደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያ ፓትሪያርክ ወኪል ሜጥሮፖሊታ ገናዲዮስ፣ እንዲሁም የእንግሊካውያን አቢያተ ክርስቲያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካትነርበርይ ሊቀ ጳጳስ ልዩ ልኡክ ጸጋዊነታቸው ዳቪድ ሞክሶን የተገኙም ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ይላሉ ከእነዚህ መንፍሳውያን መሪዎች ጋር በመሆን በጋራ በቅዱስ በር መታለፉ አስታውሰው እዚህ የቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስ አጽም ባረፈበት ቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ በመላ ቅዱሳን ሰማእታት ድጋፍ ታምነን አብነታቸውን በማስተዋል ውህደታችን የደም ውህደት እናድርግ በማለት የለገሱት ሥልጣናዊ ስብከት እንዳጠቃለሉ ደ ካሮሊስ አስታውቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.