2016-01-25 16:18:00

ቅዱስ አባታችን ለመገናኛ ብዙኃን አርአያ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “የመገናኛ ብዙኃንና ምኅረት፣ ለፍርያማ ግኑኝነት” በሚል ርእስ ሥር ለሚመራው ዝክረ 50ኛው ዓመት የመገናኛ ብዙኃን ቀን ምክንያት ያስተላለፉት መልእክት ዙሪያ ሥር ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ የቅዱስ መስቀል መንበረ ጥበብ አስተማሪ የሥነ መገናኛ ብዙኃን ሊቀ ፕሮፈሰር አባ ማርክ ኮራጆ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የሚለያይ ግንብ ሳይሆን የሚያገናኝ ድልድይ በመገንባት የሰውን ልጅ ልብ መንካት እውነት በፍቅር ማካፍፈልና ማገናኘት የተሰኙት እሴቶች የሚያጎላ ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት  ለሁሉም የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞችና ጋዜጠኞች አርአያ መሆናቸው ያረጋግጥልናል፣ ስለዚህ የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ሠራተኞችና ጋዜጠኞች ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ ሁሉም በቤተሰብ ጭምር ሳይቀር መልእክቱ መነበብ በሚገባው ስለ ግኑኝነት ጥልቅ ትርጉም የሚናገር ነው። መልእክቱ የመገናኛ ብዙኃን ማኅበራዊ ሰብአዊ ገጽታው የሚብራራና አገናኝ ድልድይ በመገንባት ማገናኘትና መገናኘት የሚለው የመገናኛ ብዙኃን ሚና ለይቶ የሚያብራራና አገናኝ ድልድይ ለመሆን ምን መደረገ እንዳለበትም መንገዱን የሚያመላክት መልእክት ነው ብለዋል።

የመገናኛ ብዙኃን የሚጠቀሙባቸው ቃላቶች አገናኝ ድልድይ ለመገንባት የሚያግዙ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ስለዚህ የምንጠቀምበት ቃላት ለይቶ ማወቅና የሚያስከትለው ውጤት አሉታዊ ወይንም አወንታዊ መሆን ቀድሞ ማመዛዘን ያስፍልጋል። የመገናኛ ብዙኃን የሚፈጽሙት ግኑኝነት ለውጥና የበለጠውን ጉዳይ ለማረጋገጥ የሚያነቃቃ መሆን አለበት፣ ግኑኝነት ለበለጥ ለውጥና ኅዳሴ ካልሆነ ግኑኝነት ሳይሆን ለያይ ይሆናል። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ባከበሩት የሕማማት ሳምንት ወቅት የሕጽበተ እግር ሥነ ሥርዓት ለመፈጸም በመረጡት ሮማ በሚገኘው በታዳጊ ወጣት የማረሚያ ወህኒ ተገኝተው እዛው ሕጽበተ እግር ፈጽመው ካበቁ በኋላም ከወጣቱ እስረኞች ጋር ሲገናኙ በቅዱስነታቸው እግራቸው ከታጠቡት 12 ወጣቶች ውስጥ አንዱ ቀረብ ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ መፈቀሬን ለማጣጣም ችያለሁ ሲሉ እንደተናገራቸው ፕሮፈሰር ካሮጆ አስታውሰው፣ ይኽ ነው እውነተኛው የግኑኝነት ባህርይ፣ የመገናኛ ብዙኃን ሲባል ሕዝቦች የሚያገኛ ማለት ነው፣ ስለዚህ የሚለያይ ሲሆን መገናኛ ሊባል አይችልም፣ በሌላ መልኩም ድልድይ ማለት ነው። ድልድይ ያገናኛል የማያገናኝ ሲሆን ለያይ የግንብ አጥር ሆኖ ይቀራል የግኑኝነቱን ድልድይ የሚያፈርሱ የማያገናኙ ጠብ ጭሪ ቃላቶች አሉ ከዚህ አንጻር ቅዱስ አባታች ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት የመገናኛ ብዙኃን ሲባል ምን ማለት መሆኑ ጥልቅ ትርጉሙን በመተንተን ገልጠዉታል። አባትና እናት ከልጆቻቸው ጋር ያላቸው ግኑኝነት ልጆች ከወላጆቻቸው ጋር የሚኖራቸው ግኑኝነት ምንና እንዴት መሆን እንዳለበትም ጭምር የሚያብራራና አዲሱ የግኑኝነት መሠረት ምኅረት የሚል ቃልና ተግባር መሆን እንዳለበት የሚያመላክት ነው። ይኽ ማለት ደግሞ ልክ ኢየሱስ በመስቀል ላይ እንደተዘረጉ እጆቹ ዓለም በሞላ እንደሚያቅፍና የእግዚአብሔር ምሕረት ለሁሉም እንደሚያገናኝ ሁሉ የመገናኛ ብዙኃን እንዲህ ባለ መልኩ ሁሉም የሚያቅፍና የሚያገናኝ መሆን አለበት፣ ክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን የሚሰጡት አገልግሎት ከጸሎት የመነጨ በምኅረት በእውነትና በፍቅር የተመራ በመሆን እውነትና ፍቅር ላይ የጸና ግኑኝነት እንዲረጋገጥ የሚደገፉ ሆነው መገኘት እንደሚኖርባቸው የሚያነቃቃ መልእክት ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.