2016-01-20 16:46:00

ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ፦ አስፍሆተ ወንጌልና ውይይት


እ.ኤ.አ. ከጥር 24 ቀን እስከ ጥር 31 ቀን 2016 ዓ.ም. በፊሊፒንስ ሰቡ ከተማ “በእናንተ ውስጥ ያለው ክርስቶስ የክብር ተስፋ ነው” (ቈላስይስ ምዕ. 1, 27) በሚል ርእስ ሥር  ሊካሄድ በተወሰነው 51ኛው ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ልዩ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ልኡክነት ማእርግ የሚሳተፉት በቢርማኒያ የያንጎን ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ቻርለስ ማኡንግ ቦ አፍስፍሆተ ወንጌል ከተለያዩ ሃይማኖቶች ባህሎችና ሕዝቦች መካከል የጋራው ውይይት የወቅታዊው ዓለም ተጋርጦ መሆኑ እስያ ኔው የዜና አገልግሎት ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ እስያ የተለያዩ ኃይማኖቶች የሚገናኙበት መስቀለኛ ክፍለ ዓለም ነው፣ ስለዚህ አሁንም ቢሆን እንደ ምዕራቡ ዓለም ኢሃይማኖተኛነት ባህል ብዙ ያልተቀበለ ክፍለ ዓለም ነው እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አታወቀ።

ቅዱስ ቁርባን ክርስቲያኖችን ወደ ማኅበራዊ ተልእኮ ያነቃቃል

በዚህ እየተኖረ ባለው የምህረት ዓመት የሚካሄደው የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ በክርስቲያን ልብ ውስጥ ምህረት የሚዘራና ቅዱስ ቁርባን ለመንፈሳዊ ባህል ምንጭ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት በሚገባ እንዲስተዋል የሚደገፍ መሆኑ የሚመሰክር ነው። ስለዚህ ቅዱስ ቁርባን ርእስ ዙሪያ መወያየት ማለት የምንኖርበት ዓለም በምልአት በመመልከት የሚታየው ኤኮኖሚያዊና ምኅዳራዊ ኢፍትሃዊነት እንዲቀረፍ መሪ ሃሳብ የሚያመነጭም ነው፣ ጉባኤው የሚያመለክታቸው ሦስት አቅጣጫዎች አሉ አንዱ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የጋራ ውይይት ከባህሎችና እንዲሁም ከድኾች ጋር ውይይት ያለው አስፈላጊነት የሚያመለክት ነው።

ድኽነት መዋጋት

በአሁኑ ሰዓት ጸረ ድኽነት የሚደረገው ርብርቦሽ ለገዛ እራሱ ሃይማኖት ተመስሎአል፣ በእስያ ስለ ድኾች የማሰቡ ግፊት መንፈሳዊነት ምንጭ ያለው ነው፣ በተለያዩ ባህሎች መካከል የጋራው ውይይት ላለው አስፈላጊነት እስያ አብነት ነች፣ በዓለማችን ድኽነት መዋጋት ቃል ብቻ እይሆነ መጥተዋል፣ ሰብአዊነት የሚጎዱ የተለያዩ ጸረ ሰብአዊ መብትና ክብር ተግባሮች ይታያሉ፣ ቅዱስ ቁርባን ሰብአዊነት መለያውና ጥልቅ ትርጉሙ ይገልጥልናል፣ ስለዚህ ጉባኤ በቅዱስ ቁርባን ውስጥ ያለው የሕይወትና የታሪክ ፍጻሜ ትርጉም የሚያብራራ ነው እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.