2016-01-18 16:14:00

ቅዱስ አባታችን፦ የሕንጸት መርሃ ግብር የግኑኝነት ባህል የሚያነቃቃና የሚደግፍ ይሁን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በብራዚል እ.ኤ.አ. ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ ተከፈተው የመላ ላቲን አመሪካ አገሮች የካቶሊክ ሕንጸት ዓውደ ጉባኤ ባስተላለፉት የድምጸ ምስል መልእክት፦ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ሕንጸት ሰውን ሳይሆን ፍርሃት ማእከል ያደረገ በመሆኑ በሕዝቦች በጎሳዎችና በሃይማኖቶች መካከል የእርስ በእርስ መጠራጠር የሚያነቃቃ ነው፣ ነገር ግን ሕንጸት ሰውን ማእከል ያደረገ ሲሆን የግኑኝነት ባህል የሚያረማምድ የሚደግፍ ይሆናል ስለዚህ

ይኸንን ዓይነት ሕንጸት እናነቃቃ፣ ይኽ ግኑኝነት በሕዝቦች በባህሎችና በሃይማኖቶች መካከል የሚኖር ሲሆን ሰው ማእከል ሆኗል ማለት ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን አያይዘው የአርጀንቲና የአብያተ ትምህርት ድራዊ ግኑኝነት ማኅበር እንደ አብነት ጠቅሰው በስፖርት በስነ ጥበብ በስነ ምርምር በሁሉም መስክ በወጣቶች ባጠቃላይ በመላ ዓለም በሚገኙት አቢያተ ትምህርት መካከል ግኑኝነት በማረጋገጥ የምንኖርበት ዓለም የግኑኝነት እንጂ የልዩነት ቤት እናድርግ ብለው በሕግና በሥርዓት ላይ ብቻ ከሚጸናው የሕንጸት መርሃ ግብር እንጠንቀቅ አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.