2016-01-18 16:03:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሮማ የአይሁድ ሙክራብ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራችነስኮ ያንን ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ 1986 ከዛም እ.ኤ.አ. በ 2010 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በሮማ በሚገኘው በአይሁድ ሙክራብ አካሂደዉት የነበረው ታሪካዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ይኸው እ.ኤ.አ. ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በሙክራቡ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ በአይሁድና በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል ያለው ወንድማዊ ቅርበትና ግኑኝነት ዳግም እንዳረጋገጡ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብሪኤላ ቸራዞ ገለጡ።

እኚህ ገና የቦኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት እያሉ ከአይሁድ እምነት ተከታዮችና የበላይ አስተማሪዎች ጋር ጥብቅና ወዳጅነት የተካነው ግኑኝነት የነበራቸው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ዳግም ሮማ የሚገኘውን የአይሁድ ሙክራብ ጎብኘተው ባሰሙት ንግግር በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ሕያው መሆኑ ያሰመሩበት ቃል በሁሉም ልብ ታትሞ እንደሚቀር እዛው የተገኙት የአይሁድ እምነት ተከታይ ዜጎች የሮማው ሙክራብ አቢይ መምህር ሪካርዶ ሰኚ ባስደመጡት ንግግር መስክረዉታል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እዛው በአይሁድ ሙክራብ እንደደረሱ በሮማው ሙክራብ አቢይ መምህር ሪካርዶ ሰኚና የአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮች አማካኝነት አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ የሮማ የአይሁድ ማኅበረሰብ ሊቀ መንበር ሩት ዱረገሎ ባስደመጡት የእንኳን ደሃና መጡ መልእክት አማካኝነት ያንን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በሮማው ሙክራብ ታሪካዊ ጉብኝት ዛሬም በአዲስ ምዕራፍ ታድሰዋል ብለው በዚህ አክራሪነትና ሃይማኖት ተገን ያደረገ ግብረ ሽበራ በሚታይበት ዓለም ከምን ግዜም በበለጠ በሃይማኖቶች መካከል የጋር ውይይት እጅግ አንገብጋቢ ነው፣ በዚህ በመታየት ላይ ባለው የሃይማኖት አድልዎ ስደት ፊት ግድ የለሽነትንት መኖር አይገባም፣ አዲስ ሰላም የተካነው የጋራ ያብሮ መኖር እማኔ በሁሉም ሃይማኖት ተቀባይነት ሊያገኝ ይገባዋል ሲሉ አቢይ መምህር ሪካርዶ ሰኚ በበኵላቸውም ያለፈው በሃይማኖት መካከል የተፈጸመው ስሕተት ዛሬ ካለ ማመንታት አብረን በማውገዝ የተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል መከባበርና ኃላፊነት የተካነው የጋራው ውይይትና ግኑኝነት ዕለት በዕለት ማነቃቃት ያስፈልጋል እንዳሉ ቸራዞ ገለጡ።

አይሁዳውያን ካቶሊካውያንና ሙስሊሞች በጋራ ለበለጠው ዓለም ግንባታ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስደመጡት መልእክት፦ በተለያዩ ሃይማኖትች መካከል በሚደረገው ውይይትና ግኑኝነት በፈጣሪ ፊት እንደ ወድማማቾችና እህታማቾች ስንገናኝ በእያንዳንዳችን መካከል በምንመሰክረው መከባበርና ትብብር አማካኝነት ለርሱ ምስጋና እናቀርባለን፣ በአይሁድና በክርስትና መካከል ያለው ግኑኝነት የክርስትናው መሠረት የአይሁድ ሃይማኖት መሆኑ ላይ የጸና ነው። ይኽ ደግሞ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ያለንበት ዘመን በተሰኘው ድንጋጌው  ቁጥር አራት ዘንድ ተብራርቶ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

የወቅታዊው ዓለም ተግዳሮት ምሉእ ስነ ምኅዳር ሰላምና ፍትህ ነው

ያ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ባሰመረበት እረሱም የጋራው ውይይት ዘንድ ያለው ቲዮሎጊያዊ ገጽታ በሚገባና በጥልቀት ሊጠን ይገባዋል፣ ዛሬም በሁለቱ ሃይማኖቶች መከወን ይገባዋል። የዛሬ 30 ዓመት በፊት ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያንን ሙክራብ ጎብኝተው ባስደመጡት ንግግር የእምነት የበኽር ወድሞቻችንና እህቶቻችን በማለት ለአይሁድ ሃይማኖትና ምእመናን የሰጡት መለያ ቅዱስ አባታችን ዳግም በማስታወስ እያንዳንዳችን ለሮማ ከተማ የሚጠበቅብን ኃላፊነት ወቅታዊው የዓለም ተግዳሮትን ሳንዘነጋ እንወጣው ዘንድ ተጠርተናል፣ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቃለለው ያንን ምሉእ ስነ ምኅዳር ካለ ምንም መግደርደር ተቀዳሚ ጉዳይ ነው። ከዚህ ጋር በማያያዝም ሰላምና ፍትህ ለማስፋፋት ያለው አስፈላጊነት ሲያመለክቱ፦ “ሰው በሰው ላይ የሚፈጽመው ዓመጽ ከሁሉም ሃይማኖቶች ጋር የሚጻረርና ሃይማኖት ለሚለው መለያዊ ስያሜ የተገባ አይደለም፣ በተለይ ደግሞ በእነዚያ በአንድ እግዚአብሔር በሚያምኑት ሦስቱ አበይት ኃይማኖቶች ዘንድ ሕይወት እግዚአብሔር የጸገወው የተቀደስ መሆኑ እጅግ ሊስተዋል ይገባዋል።

በዚያ የፍቅርና የሕይወት እግዚአብሔር በሆነው አብ ፊት አመጽ ሞት የመደምደሚያ ቃላት አይሆኑም፣ በኤውሮጳ በቅድስት አገር በመካከለኛ ምስራቅ በአፈሪቃ ባጠቃላይ በዓለም የሰላም የእርቅ የምህረትና የሕይወት አመክንዮ እንዲኖር ጌታ እንዲረዳን እንጸልይ።

በታርክ አይሁድ ላይ የተፈጸመው ዕልቂት ለወቅታዊውና ለመጪው ዓለም ትምህርት ነው

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአይሁድ ላይ የተፈጸመው ዕልቂት ልብን በሚነካ ቃላት በማስታወስ ያንን እግዚአብሔርን በሰው ለመተካት ያለመው ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለም የከወነው አሰቃቂው ኢሰብአዊ ተግባር አንርሳው በማለት ሁነኛ ጥሪ በማቅረብ ለወቅታዊውና ለመጪው ዓለም ትምህርት ነው። ያ የተፈጸመው አሰቃቂው ተግባር ተመሳሳይ ዕልቂት እንዳይከሰት ባስቸኳይ ፈጥቶ የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብርና ሰላም ለመንከባከብ ከወዲሁ ለመግታት እንዲቻል እጅግ የላቀ ጥንቁቁነት እንዲኖረን ያስገነዝበናል ካሉ በኋላ ቅዱስ አባታችን ያስደመጡት ንግግር ሲያጠቃልሉ፣ በጋራ የበለጠውን ዓለም ለመገንባት የምናደርገው ጉዞና ወደ መጪው ያቀናው እርምጃችን ጌታ ይምራው እርሱ ለእኛ የድሕነት እቅድ አለውና ብለው በእብራይስጥ ቋንቋ ሻሎም አለከም ትርጉሙም ሰላም በናንተ ላይ ይሁን እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አስታወቁ።    








All the contents on this site are copyrighted ©.