2016-01-16 10:34:00

የሰማይ አባታችው ይቅርባይ እንድሆነ እናንተም የይቅርባይነትን መንፈስ ይዛችሁ እደጉ


እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር ከሚያዚያ 23-25 2016 በአብዛኛው ከ13-16 የእድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ መጣቶች በተዘጋጀው ልዩ የምህረት አመት ኢዩቤሊዩ በዓልን አስመልክቶ ቅዱስ አባትችን ር.ሊ.ጳጳስ ፍራንቸስኮስ ባስተላለፉት የቅድመ ዝግጅት መልዕክት ላይ እንደገለፁት “አሳባችሁን በጣም ግሩም እና ገንቢ በሆኑ ነገሮች ላይ በማድረግ የሰማይ አባታችው ይቅርባይ እንድሆነ እናንተም የይቅርባይነትን መንፈስ ይዛችሁ እደጉ” በሚል አርስት ላይ ተመርኩዞ እንደሚከበር ገልፀዋል ስትል ሮቤርታ ጂዞቲ ዘግባለች።

“የይቅርባይነትን መንፈስ ይዞ ማደግ” ማለት አሉ ቅዱስ አባታችን ፍቅርን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጥ ፍቃድ ማድረግ ማለት ነው ካሉ ቡኋላ በውጫዊ የአካላችን ከፍል ማደግ ቢቻ ሳይሆን የሚጠበቅብን በፍቅርና በይቅርታ አድራጊነት መንፈስ ማደግ ጭምር ማለት ነው ብለዋል። በተጨማሪም እናንተ እየተዘጋጃችሁ ያላችሁት ለውደፊቱ ለሚገጥሙዋችሁ አስቸጋሪ የሕይወት ገጠመኝ እንደ አንድ ክርስቲያን ጥንካሬ እና ብስለትን በተላበሰ መልኩ ትክክለኛውን የሕይወትን ምርጫ የመምረጥ ችሎታ እንድታዳብሩ በመሆኑና በየቀኑ እንደየ ችሎታችሁ ለአለም ሰላም የራሳችሁን አስተዋጾ እንድታበርከቱ ስለሆነ ጠንከራችሁ በዚህ መንፈስ እንድታድጉ አደራ እላለሁ በለዋል።

በተጨማሪም አሁን እናንተ የምትገኙበት የጉልምስና እድሜ “ሁሉንም ነገር ማከናወን እንችላለን” በሚል ስሜት የታጀበና በተቃራኒው ደግሞ ብዙ መፈፀም የማትችሉት ነገር በሚያጋጥሟችው አስገራሚና አስደንጋጭ ምህበራዊ ለውጦች በሚታዩበት አወዛጋቢ ወቅት ላይ በምሆናችን በእመነታችሁ ፀንታችሁ እስከዛሬ ይህንን ወቅታዊ ችግር እንድትጋፈጡ ጉለበት ሆኖዋችሁ የረዳችሁ እርሱ በመሆኑ ተስፋችሁን በእግዚአብሔር ላይ ቢቻ አድርጋችሁ ነቅታችሁ ልትኖሩ ይገባል ምክንያቱም ጥሩ አስተሳሰብ ይዛችሁ ስኬትን በሕይወታችሁ ለማምጣት የምትችሉት ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ ቢቻ ነው በማለት አሳስበዋል።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ሓሳብቸውን ስያጠቃልሉ “በጦርነት፣ በከፋ ድህነት፣ በአስቸጋሪና በመጥፎ ሁኔታ ለሚኖሩና ተረስተው ለሚገኙ የአለምችን ወጣቶች ምልዕክታቸውን ስያስተላልፉ “ ተስፋ አትቁረጡ፣ በርቱ ተደጋግመው ወደ እናንተ የሚመጡትን ጥላቻንና ሽብርን የሚፈጥሩትን ቃላት በማስወገድ እግዚአብሔር ለናንተ ሊፈጽመው ያዘጋጄው እቅድ ስላለ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ያስፈልጋል ብለው በዚህ ዓይነት አስጨናቂ በሆነ ሁኔታ ለሚኖሩ ወጣቶች ሁላችንም በአንድነት ሠላም እና ፍትህ ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ይሆን ዘንድ የበኩላችንን ጥረት ልናደርግ ይገባል ብለዋል።

በንግግራቸው ማጠቃለያ ላይ በጉባሄው ለሚሳተፉ ወጣቶች እናዳሳሰቡት ለበዓሉ በምትመጡበት ወቅት ማዘጋጀት ያለባችሁ ቦርሳችሁንና መፈክሮችን ቢቻ ሳይሆን ከሁሉም በላይ ልባችሁን እና አምሮዋችሁን ለመክፈት መዘጋጀት ይኖርባችዋል በማለት ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.