2016-01-16 10:18:00

በሁሉም ቁምሳናዎች ስደተኞች የማስተናገድ መርሃ ግብር


እ.ኤ.አ. መስከረም 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ዕለተ ሰንበት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እኩለ ቀን ይፋዊ የጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ ባቀረቡበት ወቅት፣ እያናንዱ ቁምስና ከሮማ ሰብካ ጀምሮ ተፈናቃዮችና ስደተኞች እንዲስተናገዱ አደራ በማለት አቅርበዉት የነበረው ጥሪ በሁሉም ቁምስናዎች እግብር ላይ እየዋለ ነው። የአገረ ቫቲካን ቁምስና ቅድስት ሃናና በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቆሞሶች ቅዱስ አባታችን ያቀረቡት ጥሪ እግብር ላይ በማዋል የአስተንግዶ መርሃ ግብር በመወጠን ከጳጳሳዊ የምጽዋት ጉዳይ ከሚከታተለው ቢሮ ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ኮንራድ ክራዠቪስኪና ከካቶሊካዊው የቅዱስ ኤጂዲዮ እንቅስቃሴ ጋር በመተባበር የጀመሩት ስደተኛ ቤተሰብ የማስተናገዱ ግብረ ሰናይ ባመርቂ ሁኔታ እየቀጠለ ነው።

የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቁምስና ሮማ በሚገኘው በጎዳና ግረጎሪዮ ሰባተኛ ክልል አንዲት ከኤርትራ የተሰደዱ እናት ከአምስት ልጆቻቸው ጋር እንዲሁም የቅድስት ሃና ቁምስናም በቫቲካን አቅራቢያ በሚገኘው ቦርጎ ክልል ከሶሪያ የተሰደዱ አባትና እናት ከሁለት ልጆቻቸው ጋር እንዲስተናገዱ ማድረጋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አመለከተ።

ከኤርትራ የተሰደዱ በግረጎሪዮ ሰባተኛ ክልል መስተንግዶ ያገኙት እናት ከአምሥት ልጆቻቸው ጋር የሚገኙ ሲሆን፣ ሌሎች ሁለት ልጆቻቸው በኢትዮጵያ የስደተኞች መጠለያ ሰፈር ውስጥ እንደሚገኙ ገልጠው ካቶሊካዊ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበርን እነዚያ በኢትዮጵያ ስደተኞች መጠለያ ሰፈር ውስጥ የሚገኙት ሁለቱን ልጆቻቸው ወደ ሮማ እንዲገቡ በማድረጉ ድጋፍ ከቤተሰብ ጋር ለመቀላቀል በሚል ምክንያት የሚሰጠው የመግቢያ ፈቃድ እንዲያገኙ ጥረት እየተደረገ መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ጠቁሞ አያይዞም በቅድስት ሃና ቁምስና መስተንግዶ ያገኙት የሶሪያ ስደተኞች ሁለት ልጆች ያሉዋቸው ሲሆን አንዱ ልጃቸው በኖርወይ የተወለደ ቢሆንም ቅሉ የዛሬ አንድ ወር በፊት በዱብሊን ስምምነት መሰረት ቀድሞው የገቡበት አገር ኢጣሊያ በመሆኑ ወደ ኢጣሊያ የተሸኙ መሆናቸው ያብራራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.