2016-01-16 10:09:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ የበላይ መስተዳድር ውስጥም ብዙ ቅዱሳኖች አሉ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ጧት ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ የአርጀንቲና የካህናት ተቋም አለቆችና የመናብርተ ጥበብ ተማሪዎ ካህናት ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ መርሰደስ ደ ላ ቶረ ገለጡ።

ስለ ተካሄደው ግኑኝነት አስመልተው ጳጳሳዊ የአርጀንቲካ ተቋም ዋና አለቃ አባ አንገል ሄርናንደዝ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ግኑኝነቱ እጅግ ደስ የሚያሰኝ አባታዊና ውሉዳዊ መንፈስ የተካነው ነበር። ተቋሙ ቀደም ብሎ ካህናቶቹን ወደዚህ ተቋም ከሚልኩት የአርጀንቲና ሰበካዎች ውስጥ የሦስት ሰበካዎች ብፁዓን ጳጳሳት ጉብኝት መታደሉ አስታውሰው፣ ከቅዱስ አባታችን ጋር ለመገናኘት ያቀረብነው ውሉዳዊ ጥያቄ ቅዱስነታቸው አወንታዊ ምላሽ በመስጠት ሲቀበሉንና መሪ ሲለግሱ በእውነቱ የነበውን ሐሴት ድርብ እድርጎታል ብለው ቅዱስ አባታችን በጽሑፍ ያዘጋጁት መልእክት ሳይሆን ከካህናቱ የቀረበላቸው ጥያቄ በማሰባሰብ ነበር ቀጥተኛ ምዕዳን  የለገሱት ብለዋል።

አንድ ለትምህርት ወደ ሮማ የሚመጣ አርጀንቲናዊ ካህን በሮማ እንዴት መኖር አለበት፣ ትርምህርቱን በሚገባ አጠናቆ ወደ አርጀንቲና ሲመልስ ምን ዓይነት መመለስ ይሆናል ሲል ላቀረበላቸው ጥያቄ ለምሳሌ አስታውሰው፣ ቅዱስ አባታችን ሲመልሱ፣ ቅዱስ ጴጥሮስና ደቀ መዛሙርት በዙሪያቸው በወንጌላዊ ተልእኮና በቅዱስ ማዕድ አብሮአቸው የሚያገለግሉ ዲያቆናት ከሕዝብ ይመርጣሉ፣ ይኽ ደግሞ ደቀ መዛሙርት የጸሎት ጊዜ እንዲኖራቸው ደግፎአቿል፣ ስለዚህ አንድ ካህን በአገልግሎቱ የሚተባበሩት ጋር በመሆን ሲያገለግል በእውነቱ ለጸሎትና ለአስተንትኖ ጊዜ ይኖረዋል፣ ካልሆነ ግን ሁሉን ለብቻዮ ላድርግ ቢል የጸሎትና የአስተንትኖ ጊዜ አይኖረውም፣ ይኽ ደግሞ ምንም ላለ ማገልገል ፈተና ያጋልጣል። ስለዚህ ወደ አርጀንቲና ስትመለሱ አደራ የጸሎትና የአስተንትኖ ጊዜ እንዲሁም ለንባበ ቅዱስ መጽሐፍ ጊዜ ይኑራችሁ ብህለው በቤተ ክርስቲያንና በየሮማዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ ሐዋርያዊ መስተዳድር ውስጥ ብዙ ቅዱሳኖች እንዳሉ እትዘንጉ እንዳሉ ገለጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.