2016-01-13 16:27:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የቤተ ክርስቲያን ልብ የሚለውጥ ጸሎት እንጂ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት አይደሉም


ተአምር የሚሰራውና ልብን እንዳይደነድን የሚያደርገው ጸሎት እንጂ ሃይማኖተኛነት አይደለም፣ የሚል ሃሳብ ላይ በማተኰር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥር 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ሁሌ እንደ ተለመደው ማለዳ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት መሥዋዕተ ቅዳሴ ኣሳርገው በዕለቱ ምንባብ ተንተርሰው በለገሱት ስብከት ቤተ ክርስቲያን የሚለውጥና ወደ ፊት እንድትል የሚያደርጋት የምእመናን ጸሎትና ቅዱሳን እንጂ እኛ አርእስተ ሊቃነ ብፁዓን ጳጳሳት ወይንም ካህናት አይደለንም፣ የእምነት ሰዎች ልንሆን እንችላለን በፈራጅነት ተግባር ሌላውን በመተቸትና በማማትና በማጥላላት አመድ ሥር በማስቀመጥ የሃይማኖተኛነት ትርጉሙን ልናጠፋ እንችል ይሆናል ያሉት ቅዱስ አባታችን፣ በላቲን ሥርዓት የዕለቱ ምንባብ ከአንደኛው መጽሐፈ ሳሙኤል ምዕ. 1 ከቁ 9 እስከ 20 የተወሰደው ላይ በማነጣጠር፦ ሃና በመካንነቷ እጅግ የተማረረች ልቧ ክፉኛ የታወከባት እግዚአብሔር ወንድ ልጅ ይሰጣት ዘንድ ትጸልያለች፣ ነቢዩ ኤሊም በእግዚአብሔር ቤተ መቀደስ መቃን አጠገብ በወንበር ተቀምጦ በቀልበ ማዶ ይመለከታት ነበር።

የጸሎት ፍቱንነት

ከቀዳሜው የሳሙኤል መጽሓፍ የተነበበው ቃል የሃና ጥርት ያሉ ቃላት ያሰማናል፣ እርሷ ከንፈሯን በማንቀሳቀ በልቧ የምትለውን ሁሉ ያላወቀ ጥልቅ ባልሆነ አመለካከት ሰክራ ነው ሲል ኤሊ ይፈርድባታል፣ በኋላ ግን ያንን በልቧ ከንፈሯን በማንቀሳቀስ ለእግዚአብሔር የጸለየቸው መልስ ያገኛል፣ እግዚአብሔር የጸለየቸው ተአመር ይሁን አለ። ሃና ከንፈሯን በማንቀሳቀስ ትጸልይ ነበር ድምጿን ሳታሰማ እያነባችን እግዚአብሔር ጸጋው ይሰጣት ዘንድ ትለምናለች፣ እንደ ሃና የእምነት ጀግኖች የሆኑ ብዙ  ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሉ፣ ያንን ስለ ልጅዋ ቅዱስ አጐስጢኖስ መለወጥ የጸለየቸውን ቅድስት ሞኒካን እናስብ፣ እንደ ሃና የመሰሉ ብዙ ጸላያን ሴቶች አሉ።

ጉልበትን አጥፎ መታገል

ካህኑ ኤሊ ያሳዝናል፣ በእውነቱ አንዳንዴ እርሱን የሚያመሳስለኝ ግድፈቶች በእኔ ውስጥ አያለሁ፣ እንደ ኤሊ አለ ምንም ማሰላሰል ለመፍርድ እንራወጣለን፣ አዛኝነት በሌላው ስቃይ ካለ መሳተፍ አይ እርሱ ምን እንደሚል የማውቀው ነገር የለም እያልን እንዳውም እንደ ኤሊ ሃናን ሰክራለች ብሎ እንደፈረደባት ሁሉ እኛም እንደ እርሱ እንፈርዳለን። በእውነት የሚጸልይ ሰው የሚጸልየውን ለመረዳቱ ያዳግታል። ሃና በሃዘን በምሬት የልብዋን ከበድ ለእግዚአብሔር ታቀርባለች፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽ አይነቱ ጸሎት እጅግ ልቡ ክፉኛ በሃዘን ተነክቶ በነበረበ ወቅት ገለል ብሎ ለአባቱ በመጸለይ ኑሮታል። በአባቱ ላይ አላማረረም እንዳውም አባት ሆይ ፈቃድህ ከሆነ መራራውን ጽዋ ከእኔ አርቅ ነገር ግን ያንተ ፈቃድ ይሁን ነው ያለው፣ አስተዋይነት የኖረ፣ ሃናም ይኸንን አስተዋይነትን ነው የገለጠችው፣ ብዙውን ጊዜ ወደ ጌታ እንጸልያለን፣ ሆኖም ከእርሱ ጋር እስከ መታገል የሚያደርስ በእንባ የተሸኘ የጸጋው ልመና እናቀርብም።

ቅዱሳን ምእመናን እንጂ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት አይደሉም

ቅዱስ አባታችን በለገሱት ስብከት ገና የቦኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት እያሉ የሚያታውሱት እርሱም አንድ የዘጠኝ ዓመት ልጁ የታመመችበት አባት በቦኖስ አይረስ ወደ ሚገኘው ቅድስተ ማሪያም ዘሉኻን ቤተ መቀድስ በመሄድ ሌሊቱን በሙሉ እዛው በቤተ መቅደሱ በር ውጭ ሆኖ ስለ ልጁ የፈውስ ጸጋ ይጸልያል፣ እዛው ሲጸልይ አድሮ በጧቱ ልጁ ወደ ምትገኝበት ማከሚያ ቤት ይሄዳል እዛው እንደደረሰም ልጁ ድና ያገኛታል፣ በእውነቱ ጸሎት ተአምር ይሰራል፣ የምእመናን ጸሎት እንጂ እኛ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ደናግል አይደለንም ቤተ ክርስቲያን ወደ ፊት እንድትል የምናደርገው፣ ቅዱሳን እነዚያ በጽናት ጌታ ምንም ነገር የሚሳነው እንደሌለ ታምነው ወደ እርሱ የሚጸልዩ ናቸው በማለት የለገሱት ስብከት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.