2016-01-04 15:40:00

ብፁዕ ካርዲናል አብሪል፦ ቅዱስ በር በማርያም መንፈሳዊነት የሚሸኝ ነው


ሮማ ለሚገኘው የጳጳሳዊ አቢይ ባዚሊካ ቅድስተ ማርያም ሊቀ ካህናት ብፁዕ ካርዲናል ሳንቶስ አብሪል ይ ካስተዮ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የባዚሊካው ቅዱስ በር የከፈቱበት ዕለት ጥር አንድ ቀን የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማርያም አመ አምላክ ክብረ በዓል የምታከብርበት ቀን እንደነበር እንዲሁም ቅዱስ አባታችን የምኅረት ዓመት በይፋ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ቤተ ክርስቲያን ንጽሕት ድንግል ማርያም አለ የአዳም ኃጢአት መጸነስዋ ባከበረችበት ቀን እንደነበር አስታውሰው፣ በእውነቱ ይክ የምኅረት ዓመት በማርያም መንፈሳዊነት የሚሸኝ መሆኑ የሚያረጋግጥ ሁነት ነው ብለዋል።

ማርያም ቅዱስ በር ከፋች ወደ ኢየሱስ የምትሸኝ ነች፣ ይኽ ደግሞ የአቢይ ባዚሊካ ቅድስተ ማርያም ቅዱስ በር ለመክፈት የተካሄደው ሥነ ስርዓት ይመሰክረዋል። ቅድስት ድንግል ማርያም የምኅረት እናት ወደ መኃሪው እግዚአብሔር የምትሸኝ እመ አምላክ ነች፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያስደመጡት ስብከት ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ሲል ያቀረበው ጸሎት ማርያማዊ ጸሎት መሆኑ በጥልቀት ገልጠዉታል። እርሷም የዚህ ይቅር በላቸው የሚለው ጸሎት ታሳታፊ መሆንዋ የሚያብራራ ነው።

ቅዱስ አባታች የመጀመሪያ ቅዱስ በር በማእከላዊት ረፓብሊክ አፍሪቃ ነው የከፈቱት፣ ቅዱስ በሩን ሲከፍቱ ያቀረቡት የሰላም ጥሪ በእውነቱ በመካከለኛይቱ ረፓብሊክ አፍሪቃ የተደረሰው የቶክስ አቁም ስምምነት እስካሁን ድረስ እንዳይጣስ የሁሉም ኃላፊነት ያነቃቃ ሆኖ ነው የታየው፣ ባጠቃላይ ይላሉ ቅዱስ የምኅረት ዓመት የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ የሚስተነተንበት በመሆኑም በዚህ የማዳን እቅድ የቅድስት ድንግል ማርያም ሱታፌ ምን ተመስሎው ጭምር ይስተነተናል፣ ስለ የማዳን እቅድ ስንናገርና በዚህ ላይ ያለን እምነት ስንኖር ማርያም ማስታወስ ግዴታ ነው፣ በመሆኑም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የምኅረተ ዓመት በማርያማዊ መንፈሳዊነት የሚሸኝ መሆኑ ቅዱስ በር ሲከፍቱ በለገሱት ስብከት በጥልቀት እንዳብራሩት ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.