2016-01-04 15:32:00

በኢየሱስ እና በወንጌል አስተምሮ በመታገዝ ሓጥያትን ከመፈፀም ልንቆጠብ ይገባል


እ.አ.አ ጥር 3.2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ አስተምሮ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ር.ሊ. ጳጳስ ፍራንቸስኮስ እንዳሳሰቡት በኢየሱስ እና በወንጌል አስተምሮ በመታገዝ ሓጥያትን ከመፈፀም ልንቆጠብ ይገባል ብለዋል።

እለት በእለት በሕይወታችን የሚገጥሙንን ደስታ፣ ሃዘን፣ እርካታ እና ችግር ሁሉ፣ ኢየሱስ እንድባርክልን በአደራ ልንሰጥ ያሰፈልጋል ያሉት ቅዱስ አባታችን ማንኛውንም ሓጥያት፣ እኛን ለማዳን ሥጋ ለብሶ በመጣው በእግዚአብሔር ልጅ እርዳታ ከሕይወታችን አስወግደን የልባችንን በር ሁል ጊዜ ለምያንኳኳው ሓጥያት በመዝጋት፣ በአንፃሩም አዳኛችን ለሆነው ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢቻ መክፈት ይጠበቅብናል ብለው ይህንንም ልናሳካ የምንችለው አዘውትረን መጻሓፍ ቅዱስ ስናነብ እና ልባችንን ለእግዚአብሔር ቃል ስንከፍት ቢቻ መሆኑን አምልክተዋል ሲል ፋውስታ እስፔራንሳ ዘግቧል።

በማስከተልም ሓጥያት ዘወትር ሕይወታችንን ስጋት ላይ ለምጣል አድፍጦ ስለሚጠባበቅ ነቅተን ልንታገለው እና ከሕይወታችን ልናስወግደው ያስፈልጋል ያሉት ቅዱስ አባታችን፣ የልባችንን በር ልከፈት የሚገባው የእግዚአብሔር ልጅ ለሚያደርገን የእግዚአብሔር ቃል ቢቻ ነው ብለዋል።

የእግዚአብሔር ቃል ሥጋ ለብሶ የመጣው እኛን ለማዳንና ብርሃን ሊሆነን በመሆኑ በእግዚአብሔር ቃል ታግዘን የልባችንን በር እኛን ለማጥቃት አድፍጦ ለሚጠብቀው ላሓጥያት በመዝጋት፣ ጨለማን አስወግደን ብርሃንን መልበስ ይጠበቅብናል ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን አስተምሮዋቸውን ስያጠናክሩ፣ ለወንጌል ቅርብ መሆን እና የወንጌል አስተምሮን በማሰላሰል ከእለታዊ ኑሮችን ጋር ማጣመር ኢየሱስን በሕይወታችን ለማስገባት ከፍተኛ ሚና ስለ ሚጫወት በተለይም ደግሞ በዚህ በያዝነው የምህረት አመት ይህንን ታላቅ ምስጢር በመለማመድ በእግዚአብሔር ጥበብ እና ፍቅር በማደግ እርሱ መሓሪ እንደሆነ እኛም ደግሞ ምህረት አድራጊዎች እንድንሆን ይስተምረናልና ይህንን በተግባር እንድንፈጽም ያስፈልጋል ብለዋል።

ቅድስት ቤተ ክርስትያናችን እንደምታስተምረን የእያንዳንዱ ክርስትያን መንፈሳዊ ግዴታ እና ጥሪ ሊሆን የሚገባውም አሉ ቅዱስ አባታችን ክርስቶስ መሓሪ እንደሆነ እኛም መሃሪ እንድንሆን በመሆኑ፣ ከኢየሱስ የተቀበልነውን ምህረት እና ብርሃን እኛም ለሌሎች መስጠት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በስተመጨረሻም እለት በእለት የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ ኢየሱስን በሚገባ ለማወቅ፣ ልባችንን ለእርሱ እንድንከፈት እና ለሌሎችም እድናሳውቀው ስለሚረዳን ቃል ወንጌልን በእየለቱ ማንበብ አሰፈላጊ መሆኑን በድጋሜ  አስታውሰው በመልካም እና በችግራችንም ጊዜ ሁሉ በሱ ልንታመን ያሰፈልጋል ብለው በዚህ በያዝነው አድስ አመት ግዴለሽነትን አስወግደን ሁላችንም በእግዚአብሔር ፀጋ ተማምነን  ሰላምን ለማስፈን ጥረት ልናደርግ ይገባል ብለዋል። በስተመጨረሻም ከተለያዩ ቦታዎች የመጡትን ነጋድያን አምስገነው እና ባርከው እንተለምደው “ሁልጊዜ በፀሎታችው አስታውሱኝ” በማለት አስተምዕአቸውን አጠቃልለዋል። 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.