2015-12-31 09:25:00

ር.ሊ. ጳጳስ፦ ህፃኑ ኢየሱስ እርሱ በሚፈልገበት ቦታ እንድንገኝ ይጋበዘናል


ር. ሊቃን ጳጳስ ፍራንቸስኮስ በዛሬው እላት ማለትም እ.አ.አ በታህሳስ 30. 2015 ለዕለት ረቡዕ ትምርተ ክርስቶስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙት ምዕመናን እንደገለፁት በዚህ በያዝነው የፈረንጆቹ የገና ሳምንት ልማዳዊ በሆነ መልኩ ብዙ ክርስትያኖች የመኖሪያ ቤቶቻቸውን በገና ዛፍ የማስጌጥ ልምድ እናዳላቸው አስታውሰው ይህ ልምድ ደግሞ የተወለደልንን ህፃኑን ኢየሱስን በደስታ እንድናመልከውና ቃል ሥጋ የለበሰበትን ታላቅ የደህንነት ምስጢር በማሰላሰል የእግዚአብሔርን የማዳን ፍቅር እድናስታውስ የሚረዳን ቁሳዊ ምልዕክት በመሆኑ ከሁሉም በላይ በመንፈሳዊ ጎኑ ልናስታውሰው ይገባዋል ብለዋል።

ለህፃኑ እየሱስ የምንሰጠው ክብር ስለ እምነታችን ብዙ ነገርን ያስተምረናል ብለው ቅዱስ አባታችን፣ ምንም እንኳን ቅዱስ ወንጌላችን ስለ ኢየሱስ የህፃንነት ህይወት ብዙ ነገር ባያወሳም ከልምድ እንደምንረዳው ግን አንድ ህፃን በሚወለድበት ወቅት በቤተሰብ ወስጥ የሚመጣውን ደስታ መገመት  ግን ቀላል ስለሆነ የኢየሱስ መወለድም ደግሞ ለኛ ለክርስትያኖች ታልቅ ደስታን እና ምህረትን ያመጣልን በመሆኑ ደታችንን እጥፍ ደርብ ያደርገዋል ብለዋል። በመሆኑም የህፃኑን ኢየሱስ መወለድ ማሰላሰል እርሱ ሁል ጊዜ ከኛ ጋር እንደሆነ እንድንረዳ ይረዳናል ብልው ልክ እንደ ማንኛውም ህፃን ኢየሱስም ትኩረት እንድንሰጠው፣ እንድንከባከበው እና እንድንጠብቀው ይፈልጋል ካሉ ብኋላ በአንፃሩም ደግሞ እንደምንኛውም ህፃን ፈገግታን እንድናሳየው፣ በርሱ ደስተኛ መሆናንችንን እንዲንገልፅና ፍቅሩን እንድንካፈል ይፈልጋል ብለዋል።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን አስተምሮዋቸውን ስያሳርጉ ህፃኑ ኢየሱስ እርሱ በሚፈልገበት ቦታ እንድንገኝ እና ከእርሱ ጋር እንድንደሰት እየጋበዘን እንደ ህፃናት የዋህ እንድንሆንና እርሱን እንድናስደስተው አደራ ይለናል ብለዋል። በዚህ በገና በዓል ወቅት ትኩረታችንና ደስታችን  ልሆን የሚገባው በህፃኑ ኢየሱስ መወለድ ቢቻ ላይ በተመረኮዘ ደስታ ሳይሆን፣ ሊከበር የሚገባው ግን ኢየሱስን ወደ ህይወታችን በመጋበዝ ደስታን እንዲሰጠን፤ በእግዚአብሔር ምህረት እና ፍቅር ዳግመኛ እንድንወለድ እንድያግዘን በመጋበዝ ጭምር መሆን አለበት ብለው አስተምዕሮዋቸውን አጠቃልለዋል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.