2015-12-30 16:48:00

የጠፋው ልጅ መመለስ የኢዮቤልዩ ቅዱስ ዓመት ኒሻን


እ.ኤ.አ. ከጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የምኅረት ዓመት ይፋዊ ልዩ ኒሻን በአገረ ቫቲካን የሐዋርያዊ መንበር ንብረት መስተዳድር ጽሕፈት ቤትና በተለያዩ የአገረ ቫቲካን ማተሚያ ቤት ቤተ መጻሕፍት ዘንድ በይፋ እንደሚቀርብና የዚህ ልዩ የምኅረት ዓመት ኒሻን መለያ ባህርያት ምን ተመስሎ በማስመልከት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ኣለሳንዶ ጂሶቲ ባጠናቀሩት ዘገባ፦ በዚያ የምሕረት ዓመት ኒሻን ገጽ ጠፍቶ የተገኘው ልጅ ምስል የተኖረበት ጠቅላላ ትልቁ አውታር ማለትም ዲያመትሩ 50 ሚሊሜትርና የሚለካ ለእያንዳንዱ ክርስቲያን እጅግ ወሳኝ የሆነ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የምኅረት ዓመት በማወጅ ለምን እንዳወጁና ያለው ጥልቅ ትርጉሙን የሚገልጥ ቃል የተኖረበት ሰላሳ ሦስት ዓመት ዕድሜ ባላት በኢጣሊያዊት የሥነ ቅብና ስነ ንድፍ እንዲሁም ስነ ሐወልት ሥራ ሊቅ ማሪያንጀላ ክሪሾቲ የተሠራ፣ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የታወጀ ልዩ ኢዮበልዮ የምኅረት ዓመት ከአገረ ቫቲካን የሚል ጽሑፍና በኒሻኑ ጥግ የክሪሾቲ ስምና የኒሻኑ መለያ ቁጥር የተኖረበት መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።

ጠፍቶ የተገኘው ልጅ ምሳሌት የኒሻኑ ማእከላዊ ምስል

በሉቃስ ወንጌል ምዕ. 15, 11-32 ጠፍቶ የተገኘው ልጅ ምሳሌነት የሚያወሳ ወደ አባቴ ቤት ብመለስ ይሻለኛል ያለው ጠፍቶ የነበረው ልጅ በአባቱ ሲታቀፍ የሚያሳይ በሌላ መልኩም የአብ ምኅረት በቤተ ክርስቲያን ምሥጢር የሚያልፍ በአንስት ጾታ የሚገልጥም ምህረት የሚያበክር ነው፣ በዚህ ምስል ዙሪያ In Aeternum Misericordia Eius-ምኅረቱ ዘለዓለማዊ ነው የሚል ከምዘሙረ ዳዊት ምዕ. 136/137 የተወሰደ ቃል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በብራና በተጻፈው የእጅ ጽሑፍ አማካኝነት የምኅረት ዓመት አዋጅ ሰነድ ሦስቴ የጠቀሱት ቃል የተኖረበት መሆኑ ጂሶቲ አስታውቀዋል።

የኒሻኑ ውጫዊ ዙሪያ በተለያዩ ክርስቲያናዊ ምልክቶች ያሸበረቀ ነው

ለኒሻኑ ዋስትና እንዲሆን ማለትም ቅጅ አለ መሆኑ የሚለየው የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ማሕተም የተኖረበት የኢጣሊያ መንግሥት የጥሬ ገንዘብ የማተሚያ ቤት ተቋም ማሕተም ጭምር የሰፈረበት የገዛ እራሱ መለያ ቁጥር ያለው መሆኑ ጋዜጠኛ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.