2015-12-30 16:53:00

ለጤናማ ምኅዳር ጥበቃ የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ጥሪ


እ.ኤ.አ. ታህሳስ 15 ቀን 2015 ዓ.ም. መሎር የሚል መጠሪያ የተሰጠው ዝናብ አዘል ኃይለኛው ዓውሎ ነፋስ በፊሊፒንስ 40 ሰዎች ለሞት አደጋ ሰፊ የእርሻ መሬትና በብዙ ሺሕ የሚገመቱ መኖሪያ ቤቶች አውድሞ 750 ሺሕ የሚገመት ሕዝብ አለ መጠለያ ማስቀረቱ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁንም በብዙ ክልሎች የመብራት ኃይል አገልግሎትና የስልክ ግኑኝነት መቋረጡ ሲታወቅ፣ ያ እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. ተከስቶ የነበረው የሰባት ሺሕ ሰዎች ሕይወት ለሞት የዳረገው ከተሞችና መንደሮችን ያወደመው ኃይለኛው አውሎ ነፋስ የሚያስታውስ መሆኑ የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳኣሳት ምክር ቤት ባወጣው ልዩ መግለጫ በማስታወስ፦

ተፈጥሮ መንከባከብ ግብረ ገባዊ ኃላፊነትና ግዴታ ነው

የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት በአገሪቱ በተደጋጋሚ የሚታየው የተፈጥሮ አደጋ ከሞላ ጎደል ጠንቋሹ የሰው ልጅ የሚከተለው የልማት እቅድና ያኗኗር ስልት ነው በማለት ከዚህ ሁሉ ችግር ለመላቀቅ የሚደግፍ የተፈጥሮና የምኅዳር ጤንነት መንከባከብ መሆኑ አበክረው። በቅርቡ ማለትም እ.ኤ.አ. በ 2015 ዓ.ም. ታህሳው ወር መግቢያ በፈረንሳይ ሥነ ምኅዳር ዙሪያ የመከረው ዓለም አቀፍ ዓውደ ጉባኤ በማስታወስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ይሴባሕ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ጠቅሰው፣ በዓለማችን የሚታየው ያየር መለዋወጥና ያካባቢ አየር ብከላ እያስከተለው ያለው አደጋ መንስኤው ዓለም የሚከተለው የልማት እቅድ መሆኑ በሁሉም ዘንድ የተስተዋለ ጉዳይ ሲሆን፣ ግብረ ገባዊና ሥነ ምግባራዊ ኃላፊነት በመወጣት የተፈጥሮ አደጋ ከወዲሁ እንዳይከሰት ለሚደረገው ጥረት መሠረት መሆኑ በዚያ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ባስተላለፉት ስልት ያለው ሚዛን የሚያውክ ማኅበራዊ ፍትህ ያውካል

የምንኖርበት መሬትና ባጠቅላይ የምኅዳር ጤንነት የመንከባከቡ ጥሪ ለሁሉም ሕዝቦች የግብረ ገባዊ ትእዛዝ ነው። የተፈጥሮ ሥነ ምኅዳራዊ ሂደት የሚያውክ የሥነ ሕይወት ብዙህነት የሚያናጋ ተቀባይነት የሌለው የልማት እቅድ ውጉዝ ብቻ ሳይሆን ጸረ ማኅበራዊ ፍትህ ጭምር ነው፣ ስለዚህ በምኅዳር ላይ የሚጣለው አደጋ ድኾችና በማደግ ላይ ለሚገኙት አገሮች ብቻ ሳይሆን በድሎት የመኖር ፍላጎታቸውን በማርካት ላይ የሚገኙት የበለጸጉ አገሮች ጭምር ለአደጋ የሚጋልጥ ነው። የሁላችን ቤት የሆነውን ምኅዳራ መንከባከብ ግዴታችን ነው እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አመለከተ።

ጤንነተ የተካነው አካባቢ ለሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር መሠረት

የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ባስተላለፈው መልእክት ክርስቲያናዊ የምኅረት መልእክት የእውነተኛው ብልጽግና ሚዛን ግብረ ገባዊና ሥነ ምግባራዊ ክብር የሚያመላክት ነው።  የሚያስብለው እጅግ በድኽነት የተጠቁትና ድኾች ተብለው የሚገለጡት ማአከል ሲያደርግ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ አዝማሚው ወደ ጥፋትና የማኅበራዊ ፍትህ መጓደል የሚዳርግ ለሥነ ምኅዳር አቢይ ጠንቅ ይሆናል። ድኾች የሃብታሞች ድሎት የሚከፈሉ ዋጋ ሆነዋል፣ ሃብታሙም ሰው እንዲደኸይ የሚከፍል ዋጋ መሆኑ ማብራራታቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
All the contents on this site are copyrighted ©.